🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰3️⃣0️⃣
ቤት ከደረስን ቡሀላ ቆንጆ እራት ከመሲጋ አዘገጃጅተን ልዑሌን ቤቱን ፏፏ አድርገን ጠበቅነው::
ቤት ሲገባ ልዑሌ እንደለመደው በደስታ ተሞልቶ ነበር የገባው ።
እራታችንን በላልተን ወደመኝታችን ሄድን ዛሬ እኔ ድክምክም ብሎኝ ስለነበር ባባን የማስተኛት ተራው የልዑሌ ነበር ።
እኔ እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው አይኔን ጨፍኜ ተሸፈንኩ ግን መተኛት አልቻልኩም ጭንቅላቴ ስለማክቤል ከማሰብ ማቆም አልቻለም ነገረ ስራው ሁሉ አሳዘነኝ ።
ቀን ፊቱ ላይ ያነበብኩት የመጎዳት የእውነት ልቡ እንዴት እንደተሰበረ ፊቱ ላይ ይታያል ድርጊቱ ከፊት ከፊቴ እየቀደመ አላስተኛ አለኝ ።
በፍቅር አለም የሆነን ሰው ማፍቀር መውደድ ያለ ነው መፈቀርም እንደዛው ግን በሁለት ሰው መሀል መሆን በጣም ከባድ ነው ካንዱጋ ሆኖ ስለሌኛው ማሰብ ህመም ነው አንድ ልብ ኖሮን ለሁለት ሰው እንደመስጠት ማለት ነው በጣም ያስጠላል ስሜቱ ከማክቤልጋ ስሆን ልዑሌ ያሳዝነኛል ይናፍቀኛል ከልዑልጋ ስሆን ደሞ ማክቤል ያሳዝነኛል🥺
ብቻ ማክቤል ከዛ ቀን ጀምሮ ሳይደውል text ሳይልክ ቆዬ አንዳንዴ ለመደወል ስልኬን አነሳና እራሴ ተወኝ ብዬ ለምኜው እንዴት እደውላለሁ ብዬ እተወዋለሁ ።
በ15 ቀን አንዴ እናቴጋ እንሄዳለን አሁንም መሲንም ጨምሮ ሰብሰብ ብለን ሄደን እሷጋ ዋልን እንደለመድኩት ሰፈር ላይ ማክቤልን አየዋለሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ላየው አልቻልኩም።
እህቴን ቀስ ብዬ ጠራዃትና ማክቤልን አይተሽው ታውቂያለሽ እንዴ አልኳት??
በፊት በፊት ሁሌ ከኛ በር ፊት ለፊት ይቀመጥ ነበር ሰሞኑን ግን አይቼው አላውቅም አለችኝ ።
በውስጤ በሰላም እንዲሆን እየፀለይኩ ሲመሽ ወደቤታችን ተመለስን ማታ ላይ ሁሉም ሲተኙ ስልኬን አንስቼ text ላኩለት
ሰላም ነህ ይቅርታ ከረበሽኩህ ድምፅህ ሲጠፋ እንዴት እንደሆንክ ልጠይቅህ ብዬ ነው አልኩት ።
ደና ነኝ ብቻ አለኝ
ከዛ እኔም ዝም አልኩት በቃ ከዛ ቡሀላ ለ1 ወር ከምናምን ምንም አይነት text ተላልከን አናውቅም በስልክም አናወራም ዝም አለኝ ዝም አልኩት።
ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ነገሮች እየተቀየሩብኝ ሲመጡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድኩኝ እንደገመትኩት እርጉዝ ነበርኩ ።
የመጀመሪያው እርግዝናዬ ላይ እንዳረገዝኩ ስሰማ ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ስፀልይ ነበር።
ባሁኑ ግን የደስታ ጥግ ላይ ነበርኩ ከሀኪም ቤት እንደተመለስኩ ለናቴ ደወልኩላት እና በጊዜ ወጥታ እኔጋ እህቴንም ይዛት እንድትመጣ ነገርኳት እሺ አለችኝ።
እኔና መሲ ቤቱን በአል አስመሰልነው መሲ አስሬ ምን አለ ዛሬ ምን ዛሬ ትለኛለች ማታ ለሁሉም የተዘጋጀ ሰርፕራይዝ እንዳለ ነገርኳት ።
ልዑሌንም ደውዬ ስንት ሰአት እንደሚመጣ ስላረጋገጥኩ ሰርፕራይዙ እንዳሰብኩት ሄደልኝ ።
ማታ ሁላችንም ቤት ተሰባሰብን ሁሉም አስሬ ምንድነው ዛሬ ምንድነው ይሉኛል ምን የረሳነው በአል አለ አንዴ ይጠያየቃሉ እናቴና ልዑሌ እኔ ከእራት ቡሀላ ነው ምነግራችሁ በቃ ተረጋጉ ብያቸው እራታችንን በላን ።
ሁሉም ልባቸው ተሰቅሎ እንዴት እንደበሉ ብታዩት እያሳቁኝ ነበር ከእራት ቡሀላ ቡናችንን እየጠጣን አሁን ሁላችሁም ተረጋጉና ሰርፕራይዙን ለማየት ተዘጋጁ አልኳቸው መጀመሪያ ግን ባባን ይዞት የነበረው ልዑል ስለነበር ለእህቴ ስጣት እሷ ትያዘው አልኩት ድንገት ስሜታዊ ሆኖ ቢጮህ እንኳን ባባ እንዳይደነግጥ ብዬ ነው እንደዛ ያልኩት ::
የዛኔ የምር ግራ እየተጋባ ባባን ሰጣት እኔ ተነስቼ ወደመኝታ ክፍላችን ገባሁና ቼክ ያደረኩበትን የእርግዝና ማስረጃዬን ይዤ መጣሁና መጀመሪያ ለልዑሌ ሰጠሁት
ቀስ ብሎ አየውና እኔን ቀና ብሎ አየኝ ምንድነው ምንድነው ይሄ አለኝ አይኑ እንባ እያቀረረ እርጉዝ ነኝ የልጅ አባት ልትሆን ነው አልኩት::
እናቴ እንዴት እንደተነሳች ባላውቅም ብድግ አለችና የያዘውን ተቀበለችው ።
ልዑሌ እኔን እያየ አላምንሽም ሰላም አውቀሽ ፕራንክ አደረኩህ ልትይኝ ነው አደለ ሰላም ማይልኝ እውነትሽን ነው አለኝ??
አዎ እማዬ ትሙት የምሬን ነው እርጉዝ ነኝ አልኩት የዛኔ በቁሙ መሬት ላይ ውድቅ ብሎ ተንበረከከ እናቴ እልልታውን አቀለጠችው ።
ሄጄ ልዑሌን አቀፍኩትና ደስ አለህ አልኩት በእጁ ፊቱ ላይ ያለውን እንባ እየጠረገ ሰላም በህልሜ እየመሰለኝ ነው ደግመሽ ማይልኝ አለ።
ማልኩለት የዛኔ እንደለቅሶ ቤት ድምፅ እያወጣ መሬት ላይ ተደፍቶ ማልቀስ ጀመረ ከጠበኩት በላይ ሆነብኝ ልዑል በፈጣሪ ተረጋጋ እንጂ እንዴ አልኩት ።
እናቴም ልጄ ተው ደስታ ላይ እንዲህ አይኮንም ጥሩ አደለም ደስታውን በልኩ አድርገው አለችው።
የሱ እንባ ወይ ፍንክች አለ ዝም ብሎ ይፈሳል ።
አንስቶ አሽከረከረኝ ሰላም እውነት እኔም እንደሰው አባት ልሆን ነው እእእ ሰላም እውነት ፈጣሪ እያየኝ ኖሯል አረሳኝም አለ።
የዛኔ እናቴ ግራ ተጋብታ እንደዚህ ስትሆኑ ለሚያያችሁ ሰውኮ የመጀመሪያ ልጃችሁን ገና ልትወልዱ ነው ሚመስለው አለች ።
የዛኔ እኔ ደነገጥኩኝና ልዑሌን አየት አደረኩት ።
ያው እናቴ እሱ ወንድ ነው ቀጣዩ ደሞ ሴት ልትሆን ትችላለች ብሎኮ ነው እንዲህ ደስ ያለው ለሴት ልጅ ያለው ፍቅርኮ ይለያል አልኳት በሉ ተረጋጉና ቁጭ በሉ ልጆቼ ይህን ክብር ይሄን ደስታ ያሳየን አምላካችን ክብሩ አይጓደልበት።
እኔንም ከአንድም ሁለት የል ልጅ እንዳይ የፈቀደልኝ አምላክ ይመስገን የኔ ልጅ አሁንም እንዲሁ ከነፍቅራችሁ ጤናን ሰጥቶ በሰላም ያኑራችሁና ቤታችሁ በልጅ እንዲሞላ ያድርጋችሁ ።
በሉ እኛን ሸኙንና እናንተ ደሞ ደስታችሁን ከዚህ በበለጠ አክብሩ።
የኔ ልጅ እንዲህ በየጊዜው ደስታን እንዳይ እንድሰማ ስላደረግሽኝ አመሰግናለሁ
ፈጣሪ ያላሰብሽውን ፍቅር በረከት መትረፍረፍ ይስጥሽ ላንተም እንደዛው የኔ ልጅ በቃ ተረጋጋ አለችው ተነስታ በነጠላዋ እንባውን እየጠረገችለት::
በቃ ልዑሌ ተነስ እነማዬን እንሸኛቸው መሽቶባቸዋል አንተ እንደሆንክ በዚህ ሁኔታ መኪና መንዳት አትችልም አልኩት ሰውነቱን እራሱ በስርአት ችሎ መቆም አይችልም ነበር::
እነማዬን ሸኝተናቸው ወደ ቤት ተመለስን መሲ እንደታቀፈችው ባባ ተኝቶ ጠበቀን ተቀበልኳትና ቀስ ብዬ አስገብቼ አስተኛሁት ።
ከዛ ልዑሌን እንዲረጋጋ ወደ ማድረጉ ገባሁ እቅፍ አደረኩትና በቃ ተረጋጋ አባት ሆነሀል አባት ደግሞ ቆፍጣና ነው መሆን ያለበት አልኩት።
ሰላም እኔኮ ከዛ ሁላ ነገር ቡሀላ እንደዚህ አይነት ደስታ አለም እንዳለ አላውቅም ነበር አንድም ቀን አባት ስለመሆን ልጅ ስለመውለድ አስቤ አላቅም ::
ሰላም ይሄኮ ለኔ ምን ማለት እንደሆነ ስላልገባሽ ስሜቴን ሚገልፅልኝ ምንም ቃል ስላጣሁ ምንም ልልሽ አልችልም ግን ሰላም አስቢው እስቲ አባት ልሆን ነውኮ አባት አለኝ ፊቴን በሁለት እጆች ጥብቅ አድርጎ ይዞ እያፈጠጠብኝ ።
🔻ክፍል ሰላሳ አንድ ነገ ማታ 3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💗የፍቅር ማእበል💗