ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዘመን ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ሻምፒዮኑ አርሰናል ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።
ባለፈው የውድድር ዓመት የሊጉን ዘውድ የተቀዳጀው የሰሜን ለንደኑ ክለብ በተከታታይ ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን በፍራንክ ላምፓርድ የሚመራውን ኮቨንትሪ ሲቲ በመግጠም ጉዞውን ይጀምራል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸውን ለማጠናከር በክረምቱ የዝውውር መስኮት እንደ ብሩኖ ጉማሬሽ፣ ክሪስቶስ ሶሊስ እና ኤዝሪ ኮንሳ ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።
በሌላ በኩል ማንቸስተር ሲቲዎች ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ከተለያዩ በኋላ በቀድሞ ምክትላቸው ኤንዞ ማሬስካ እየተመሩ አዲስ ምዕራፍ ይጀምራሉ።
የግብ ማሽኑን ኧርሊንግ ሃላንድን የያዘው ሲቲ፡ ኤሊዮት አንደርሰንን ጨምሮ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ለማስቀጠል ተዘጋጅቷል።
ሞሐመድ ሳላህን ጨምሮ ከወሳኝ ተጫዋቾቹ ጋር የተለያየው ሊቨርፑል በአንዶኒ ኢራኦላ እየተመራ የውድድር ዓመቱን ይጀምራል።
በማይክል ካሪክ የሚመራው ማንቸስተር ዩናይትድ በበኩሉ ባለፈው የውድድር ዘመን ያሳየውን መሻሻል ለማስቀጠል በሊጉ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች በመጨመር ወደ ፉክክሩ ይመለሳል።
ባለፈው የውድድር ዓመት ደካማ ጊዜ ያሳለፈው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአዲሱ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እየተመራ በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ፊት በመምጣት ጠንካራ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሀል ሲቲ ከማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከሊቨርፑል እና ፉልሃም ከቼልሲ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ ሌሎች የመጀመሪያ ሳምንት ተጠባቂ ፍልሚያዎች ናቸው።
በዮናስ ጌትነት