[ . . . አ ን ድ ል ጅ ነ በ ረ . . . ]
.
.
አንድ አባት ነበረ
አንድ ልጅ ነበረው
ከድህነቱ ጋ ፣ ታግሎ የሚያኖረው
ታዲያ ይሄ አባት
እህል ያልጠገበ ፣ ኮቴው ቶሎ ቶሎ
ጓዳው ያልተዋበ ፣ ልብሱ ዘባተሎ
ሕይወት አያጓጓው ፣ በስቃይ ሲገፋ
ዕድሜ ይለምናል ፣ እስከ ልጁ ተስፋ
.
ሁሌ ተማሪ ቤት
ይህን ልጅ ሲያደርሰው
በሸካራ እጁ እየደባበሰው
እንዲሁ በደምሳሳ
ይንበረከክና ፣ ከዓይኖቹ መሳ
እንደዚህ ይለዋል
“ልጄ ሆይ ሰው ሁን!”
.
ልጁ አይገባውም ፣ እንዲህ ያለ ተረት
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ፣ ሰው ለመሆን ጥረት
ከምን ይጠብቃል? ምን አለው ከለላ ?
ምንድነው ሰው መሆን ፣ ከሰውነት ኋላ ?
.
ይህን እያሰበ ይገባል ከክፍል
መምሕር ቆሞ ከነብሶቱ
“ለሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቱ
ምግብ ልብስ መጠለያ— እነዚህ ሦሥቱ”
ታዲያ በዚህ ሚዛን ፣ ይወድቃል አባቱ
ልጅ ግራ ይጋባል
ምኞቱ ይበልጣል ፣ ሰው ከሰውነቱ ?
.
በልጅ አእምሮው ውስጥ ፣ ሁለቱን ሲያጣጥም
መራብ፣ መጠማት፣ ሜዳ መውጣት
የሚኖረው ጠላት ፣ ከነዚህ አይበልጥም
እንደዚህ ያስባል
ጠግቦ መመገብ ፣ ይሆናል ሰው መሆን
አበባ መልበስ ፣ ይሆናል ሰው መሆን
የሳር ጎጆ መሥራት ፣ ይሆናል ሰው መሆን
እንዳባት አለመሆን ፣ ይሆናል ሰው መሆን
.
እንዲህ ያደገው ልጅ
አሁን ወደ ማምሻ
ቁርጥ ሥጋ በልቶ
ውስኪውን ጠጥቶ
ቶክሲዶውን ለብሶ
ከጥሻ ሥር ያድራል
ከሞት አስበልጦ ፣ ሲርበው ይፈራል
የወዙን ክፍያ ፣ መጠጥ ቤት ሲዘራት
`ሚስቅ ይመስለዋል ፣ አባቱ በኩራት
.
እንዲህ ዓይነት ስጋት የሚያንከራትተው
ምኞቱን ይሆናል ፣ ሰው መሆን ያቃተው
©Henock_B___ ✍
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
.
.
አንድ አባት ነበረ
አንድ ልጅ ነበረው
ከድህነቱ ጋ ፣ ታግሎ የሚያኖረው
ታዲያ ይሄ አባት
እህል ያልጠገበ ፣ ኮቴው ቶሎ ቶሎ
ጓዳው ያልተዋበ ፣ ልብሱ ዘባተሎ
ሕይወት አያጓጓው ፣ በስቃይ ሲገፋ
ዕድሜ ይለምናል ፣ እስከ ልጁ ተስፋ
.
ሁሌ ተማሪ ቤት
ይህን ልጅ ሲያደርሰው
በሸካራ እጁ እየደባበሰው
እንዲሁ በደምሳሳ
ይንበረከክና ፣ ከዓይኖቹ መሳ
እንደዚህ ይለዋል
“ልጄ ሆይ ሰው ሁን!”
.
ልጁ አይገባውም ፣ እንዲህ ያለ ተረት
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ፣ ሰው ለመሆን ጥረት
ከምን ይጠብቃል? ምን አለው ከለላ ?
ምንድነው ሰው መሆን ፣ ከሰውነት ኋላ ?
.
ይህን እያሰበ ይገባል ከክፍል
መምሕር ቆሞ ከነብሶቱ
“ለሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቱ
ምግብ ልብስ መጠለያ— እነዚህ ሦሥቱ”
ታዲያ በዚህ ሚዛን ፣ ይወድቃል አባቱ
ልጅ ግራ ይጋባል
ምኞቱ ይበልጣል ፣ ሰው ከሰውነቱ ?
.
በልጅ አእምሮው ውስጥ ፣ ሁለቱን ሲያጣጥም
መራብ፣ መጠማት፣ ሜዳ መውጣት
የሚኖረው ጠላት ፣ ከነዚህ አይበልጥም
እንደዚህ ያስባል
ጠግቦ መመገብ ፣ ይሆናል ሰው መሆን
አበባ መልበስ ፣ ይሆናል ሰው መሆን
የሳር ጎጆ መሥራት ፣ ይሆናል ሰው መሆን
እንዳባት አለመሆን ፣ ይሆናል ሰው መሆን
.
እንዲህ ያደገው ልጅ
አሁን ወደ ማምሻ
ቁርጥ ሥጋ በልቶ
ውስኪውን ጠጥቶ
ቶክሲዶውን ለብሶ
ከጥሻ ሥር ያድራል
ከሞት አስበልጦ ፣ ሲርበው ይፈራል
የወዙን ክፍያ ፣ መጠጥ ቤት ሲዘራት
`ሚስቅ ይመስለዋል ፣ አባቱ በኩራት
.
እንዲህ ዓይነት ስጋት የሚያንከራትተው
ምኞቱን ይሆናል ፣ ሰው መሆን ያቃተው
©Henock_B___ ✍
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA