Forward from: Rev. Tezera Yared (GloriousLifeChurch)
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
... ዓለሞች...
“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”
— ቆላስይስ 1፥15-16
✍️ የሚታይ ውጤት የሚያመጡት የማይታየውን የሚያዩ ሰዎች ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ሰብአዊ እምነት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት እንዳለ በግልጽ ያስተምረናል።
የሰብአዊ እምነት ምሳሌ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ቶማስ ግን በአለማመን ብዙ ትምህርትን የወሰድንበት ነው። ሰብአዊ እምነት የሚመሰረተው በአምስቱ የስሜት ህዋሳቶች ላይና በአእምሮ ላይ ባለው መረጃ ልክ ነው።
እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም አብርሃም ግን የእምነት አባት ነው። በእምነት ሕይወቱም ብዙ ለእምነት ሕይወት የሚሆን መልህቆችን ያስተምረናል።
የሚታየው ነገር ከሚታየው ነው ብሎ ማመን ሰብአዊ እምነት ሲሆን፤ የማይታየውን ነገር ለሚታየው ምክንያት ነው ብሎ ማመን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ነው።
በመጨረሻም መጽሐፍ ቅዱስ ተፈጥሮአዊ፣ስጋዊ እና ግዑዛዊ አለም ማለትም የሚታየውና የሚዳሰሰው አለም፤ እንዲሁም መንፈሳዊ አለም ማለትም የማናየውና የማንዳስሰው አለም እንዳለ ይነግረናል።
ስለዚህ የማናየው አለም የሚታየውን አለም ስለሚገዛ ከማይታየው አለም ጋር የጠበቀ ግንኙነት በቃሉ እና በመንፈሱ በማድረግ በዚህ በሚታየው አለም ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር እንበርታ!
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 06/04/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!