የብቃት ምዘና ፈተና ለሚመለከታችሁ አዲስ ተመራቂ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____
የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በነርሲንግ፤ ሜዲስን፤ ጤና መኮንን፤ አንስቴዥያ፤ ፋርማሲ ፤ሜዲካል ላቦራቶሪ፤ ሚድዋይፈሪ፤ ዴንታል ሜዲስን፤ ሜዲካል ራዲዮሎጂ፤ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ፤ ፔዲያትሪክ ኤንድ ቻይልድ ሄልዝ፤ ሳይካትሪ ነርሲንግ፤ ኢመርጀንሲ ኤንድ ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ ፤ ሰርጅካል ነርሲንግ፤ ኦፕቶሜትሪ፤ ፊዚዩቴራፒ እንዲሁም ሂውማን ኒውትሪሽን ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተመዝግባችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አዲስ እጩ ምሩቃን የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ጋር በጋራ ሰኔ 19/ 2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ፈተና ተመዛኞች መዘጋጀት እና በፈተናው ወቅት በጠዋትም በከሰዓትም ክፍለ ጊዜ አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳስባለን።
በተጨማሪም በሰርጅካል ነርሲንግ፤ ኦፕቶሜትሪ፤ ፊዚዩቴራፒ እንዲሁም ሂውማን ኒውትሪሽን ሙያዎች የምትመረቁ ባለሙያዎች ከሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሙያ ፈቃድ ለማግኘት የብቃት ምዘና ፈተና የሚጠበቅባችሁ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ከላይ በተጠቀሰው የፈትና ወቅት ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ፦ ለበለጠ መረጃ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የሚተላለፈውን ማስታወቂያ እንድትከታተሉ ለማሳሰብ እንወዳለን።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: twitter.com/FMoHealth
YouTube: @FMoHealthEthiopia
Tiktok: @mohethiopia