Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊
[ † እንኳን ለአባታችን ቅዱስ አጋቢጦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ አጋቢጦስ † 🕊
+ ይህንን ዓለም ንቆ ለበርካታ ዘመናት በፍፁም ምናኔ የኖረ::
+ ምድራዊ ሃብትና ሹመት ሞልቶለት ሳለ ከሁሉ የክርስቶስን ፍቅር የመረጠ::
+ ከደግነቱ ብዛት የተነሳ ምግብ ሲያዘጋጅ ሽምብራውን ከክቶ ለሌሎች ከሰጠ በሁዋላ ለራሱ የሚመገበው ገለባውን [ አሠሩን ] ነበር::
ሌሊቱን በጸሎት ለመትጋት ማታ ማታ አመድ ይመገብ ነበር:: በዚህም ቅዱስ ዳዊት "አመድን እንደ እህል በላሁ" ያለው በዚህ ቅዱስ ሕይወት ላይ ተገልጧል:: [መዝ.፻፩፥፱] (101:9)
ቅዱስ አጋቢጦስ በዘመኑ ከሠራቸው ይህኛው እጅግ ይገርመኛል:: እርሱ በበርሃ የነበረበት ዘመኑ የሰማዕታት በመሆኑ ብዙ ክርስቲያኖች በርጉማን መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ ተገድለዋል:: ቅዱሱን ግን በአካባቢው የነበረ ሃገረ ገዢ ከበዓቱ አስወጥቶ ወደ ውትድርና ሥራ አስገብቶታል::
ሰይጣን በዚህ ከተጋድሎና ከቅድስና ሕይወት እንደሚያርቀው ተማምኖ ነበር:: ቅዱስ አጋቢጦስ ግን በወታደሮች መካከል ሆኖም ተጋድሎውን ቀጠለ:: የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ቢሾሙትም እርሱ ከበጐ ማንነቱ ፈጽሞ አልተለወጠም::
ክርስቲያን ማለት እንዲህ ነውና:: ክርስትና ሲመቸን : ሲመቻችልን : በአጋጣሚ ወይም በምክንያት የምንኖረው ሕይወት አይደለም:: ፍጹም ፍቅር የጊዜ : የቦታ : የሁኔታ ገደብ የለውምና አባቶቻችን በጊዜውም : ያለ ጊዜውም ጸንተው ክርስቶስ መድኃኒታችንን አስደሰቱ::
ከቅዱስ ዻውሎስ ጋርም እንዲህ ሲሉ ዘመሩ:- "መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ" [ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ! ]
ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና ቅዱስ አጋቢጦስ ለዘመናት ሰው ሳይገድል : ፈጣሪውን ሳይበድል : ከጾም ከጸሎት : ከምጽዋትና ትሕርምት ሳይጐድል ኖረ:: በዚህም ሰይጣንን አሳፈረ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::
በዚህ ጊዜም ወደ በዓቱ ለመመለስ መንገድን ይፈልግ : ይጸልይም ገባ:: እግዚአብሔርም ወደ በርሃ የሚመለስበትን መንገድ በቸርነቱ አቀናለት::
ነገሩ እንዲህ ነው:: ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ራትዕ [የቀና] ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: ስደት ቆመ:: የታሠሩ ተፈቱ:: አብያተ ክርስቲያናት ታነጹ:: ለክርስቲያን ቀደምቶቻችንም ታላቅ ተድላ ሆነ::
ጊዜው ለሁሉ ክርስቲያን የተድላ ቢሆንም አንድ ወጣት በደዌ ሰይጣን ያሰቃየው ነበር:: ወጣቱ የንጉሡ የቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ባለሟል : ባለብዙ ሃብት : መልኩ ያማረ ነውና ሁሉ ያዝንለታል:: ይልቁኑ ቅዱሱ ንጉሥ ተጨነቀለት::
አንድ ቀን ግን ከወታደሮቹ አንዱ ያን ወጣት "አንተንኮ አጋቢጦስ ይፈውስህ ነበር" ይለዋል:: ወጣቱ ግን አላወቀምና "ከመቼ ወዲህ የጦር አለቃ እንዲህ አድርጐ ያውቃል?" ሲል በጥያቄ ይመልስለታል:: ወታደሩ ግን ቀስ አድርጐ ምሥጢሩን ይነግረዋል::
ይህ ነገር ሲያያዝ ከንጉሡ ደርሶ ቅዱስ አጋቢጦስን አስጠርቶ "እባክህ ፈውስልኝ?" ይለዋል:: "ካዳንክልኝም የፈለግኸውን አደርግልሃለሁ" ሲል ያክልለታል:: ቅዱስ አጋቢጦስም ወደ ፈጣሪው ለምኖ ሰይጣንን ይገስጸዋል:: በቅጽበትም በክርስቶስ ኃይል ወጣቱ ይድናል::
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስም ከደስታው ብዛት "ምን ላድርግልህ?" ቢለው ቅዱሱ "ከሹመቴ ሻረኝ : ወደ በርሃ አሰናብተኝ" ብሎ መሻቱን ገለጸለት:: ቅዱሱ ንጉሥም በመገረም ቡራኬውን ተቀብሎ ወደ በርሃ ሸኝቶታል::
ወገኖቼ ! . . . በዓለማዊም ሆነ በመንፈሳዊው እርከን ስልጣንን የሚንቁ ሰዎችን ካላገኘን መፍትሔው ሩቅ ነው:: እኛም ከሥልጣን መሻት እንራቅ:: ማር ይስሐቅ እንደ ነገረን ሰይጣን ያደረበት ሰው ሹመትን [ሥልጣንን] በመሻቱ ይታወቃልና::
ቅዱሱ በፍፃሜ ዘመኑ እረኝነት [ዽዽስና] ተሹሞ ብዙ ኢ-አማንያንን ወደ ክርስትና መልሶ: ድውያንን ፈውሶ: እውራንን አብርቶ: በርካታ ተአምራትንም አድርጎ በዚህች ቀን አርፏል::
††† ልመናው በረከቱ ይደርብን::
🕊
[ † የካቲት ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አጋቢጦስ [ ጻድቅ ኤዺስቆዾስ ]
፪. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት [ዘጋዛ]
፫. ቅዱስ ሚናስ ዘቆዽሮስ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [ መምሕረ ትሩፋት ]
፪. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫. ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
፬. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፭. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮. ፳፬ቱ "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ ሱራፌል ]
† " የሚያሳድዷችሁን መርቁ . . . ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ:: እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ ::" † [ሮሜ.፲፪፥፲፬] (12:14-16)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖