የስኳር ህመም ሳይታወቅ የሚዘገየው ለምንድን ነው?
በአለማችን የስኳር ህመም ተጠቂዎች ከግማሽ ቢሊዮን በላይ አሻቅቧል።
በየአምስት ሴኮንዱ አንድ ሰው በስኳር ህመም ምክንያት ይሞታል።
በየሰላሳ ሴኮንዱ አንድ ሰው በስኳር ምክንያት እግሩ ይቆረጣል።
አጠቃላይ በምድራችን ላይ ለጤና ከሚመደበው በጀት ከ10 በመቶ በላይ ለስኳር ህክምና ብቻ ይውላል።
የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ በቀጣይ አመታት ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ ይገመታል። ምንም የመቀነስ አዝማሚያ ጭራሽ እያሳየ አይደለም።
ሌላው ገራሚ ነገር ደግሞ ስኳር ካለባቸው ግለሰቦች ግማሹ ስኳር እንዳለባቸው አያውቁም። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ላይ ይህ ስኳር እንዳለባቸው የማያውቁት ሰዎች ቁጥር ወደ 70 በመቶ ይጠጋል።
ለመሆኑ የስኳር ህመም ሳይታወቅ የሚዘገየው ለምንድን ነው?
የስኳር ህመም በተለይም ዓይነት 2 ለብዙ ዓመታት ሳይታወቅ ሊቆይ የሚችል በሽታ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በአመዛኙ ምልክት አልባ ስለሆነ ነው። ዝምተኛው ገዳይ (silent killer) የሚባለው ለዚያ ነው። አንደሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሁሉ ግልጽ መገለጫ ምልክቶች የሉትም።
አብዛኛዎቹ ስኳር ያለባቸው ሰዎች ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይሰማቸው ለብዙ አመታት ሊቆዩ ይችላሉ። ነገር ግን ስኳሩ ሰውነታቸዉን እየጎዳው እንደሆነ ማስተዋል ይገባል።
ስለዚህ ስኳር ህመምን ገና ሳይብስ ለማዎቅ ዋነኛው መፍትሄ በየጊዜው የስኳር ምርመራ በማድረግ ነው። ለዚህ ነው መደበኛ ምርመራ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው። በተለይም ተጋላጭነት ያለባቸው ሰዎች ቢያንስ በአመት አንዴ ስኳራቸውን መታዬት ያስፈልጋቸዋል።
በተለይ የስኳር መጠኑ በጣም ከፍ ሲል የሚታዩ ምልክቶች ለመጠቀስ ያህል የማያቋርጥና የማይረካ የዉሃ ጥም፣ ቶሎቶሎና አብዝቶ መሽናትና ሃይለኛ የድካም ስሜት ይገኙበታል።
ብዙውን ጊዜ የሚታዩት ምልክቶች ተጓዳኝ የጤና እክሎች አመላካች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህም የእይታ መደብዘዝ፣ የቁስል ቶሎ አለመዳንና ማመርቀዝ፣ የእግር መደንዘዝና መቆጥቆጥ፣ ስንፈተ ወሲብ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ።
ያስታውሱ፤ የስኳር ህመም ምንም አይነት የህመም ምልክት ላያሳይ ይችላል። ስለሆነም መደበኛ የስኳር ምርመራ በማድረግ ጤንነትዎን ይጠብቁ።
Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia