የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም እናት እንዴት ይሰራል?
ለእርግዝና ጊዜ የስኳር ቅድመ ምርመራ ለመስራት በጣም የተለመደው የምርመራ ዘዴ የሚበጠበጥ 75 ግራም ግሉኮስ ፈሳሽ/ሽሮፕ በመጠጣት (Oral Glucose Tolerance Test, OGTT) የሚሰራው ነው። ይህ ምርመራ ሰውነትዎ ግሉኮስን እንዴት እንደሚቁቋም ይፈትሻል።
መጀመሪያ በባዶ ሆድ (ለስምንት ሰአት ያክል ምንም ምግብ ሳይበላ) ያለውን የደም ግሉኮስ መጠን ለማወቅ ክንድ ላይ ካለው የደም ሥር የደም ናሙና ተወሰዶ ይመረመራል።
ቀጥሎ የሚጠጣ 75 ግራም ግሉኮስ የያዘ ጣፋጭ ሽሮፕ/ፈሳሽ ይወሰዳል።
ከዚያም ግሉኮሱን ከጠጡ በኋላ ከአንድ ሰአት እና በድጋሜ ከሁለት ሰአት በኋላ ክንድ ላይ ካለው የደም ናሙና ተወስዶ የደም የስኳር መጠን ይለካል።
በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የምርመራ መመዘኛዎች ከሚከተሉት የስኳር ምርመራዎች ውስጥ አንዱ ከተሟላ ስኳር አለ ለማለት ያስችላል።
1️⃣ የባዶ ሆድ የደም ስኳር መጠን፡ ≥92 mg/dL
2️⃣ ግሉኮስ ከተጠጣ ከ1-ሰዓት በኋላ ያለው የደም ስኳር መጠን፡ ≥ 180 mg/dL
3️⃣ ግሉኮስ ከተጠጣ ከ2-ሰዓት በኋላ ያለው የደም ስኳር መጠን፡ ≥ 153 mg/dL
ዛሬዉኑ የጂዲኤም ምርመራ ለማሰራት ከሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ።
ስለ ጂዲኤም ጥያቄዎች አሉዎት? አስተያየትዎትን ይጻፉልን።
https://youtu.be/yKMpgwgxZQg?si=3-FD4UYI8hIRtaib