💬ለራስህ ያለህን አመለካከት የሚለውጡ አራት ነጥቦች
How to change your Self -image.
✍ሚስጥረ አደራው
🔘ኸርል ናይቲንጌይል በሰው ልጆች ባህሪ እና አስተሳሰብ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አበርክተው ካለፉ ተናጋሪ እና ጸሃፊያን መካከል ቅድሚያ የሚሰጠው አሜሪካዊ ነው። በብዙ ስዎች ዘንድ “The Strangest Secret” በተሰኘው ስራው ዛሬም ድረስ ይታወሳል። የናይቲንጌይል ስራዎች ሁሉም መሰረታቸው አንድ ነው “ሰው የራሱ ህይወት ፈጣሪ ነው” የሚል። በተለያየ ስራዎቹ ላይም፤ የሰው ልጅ አስተሳስበ በህይወቱ ላይ ያለውን እጅግ ትልቅ አስተዋጽዎ ሳይጠቅስ አያልፍም። ለዛሬም ከስራዎቹ መካከል የተወሰነውን እንዲህ አቀነባብሬ አቅርቤያለው
⚪️በምናብ እራስህን በትያትር መድረክ ፊት እንደተቀመጠ ተመልካች ቁጥረው። በመድረኩ ላይ የሚተወነው ቲያትር ስለ አንድ ጠቃሚ ሰው ነው። የዚህ ቲያትር ደራሲና አዘጋጅ አንተ ነህ። እንደ ተመልካች ቲያትሩን ስትመለከተው ፤ሊያስቅህ፤ ሊያሳዝንህ፤ ሊያስጠላህ አልያም ሊያሳፍር ህ ችላል። ጥሩ ነገሩ የቲያትሩ ደራሲ እና አዘጋጅ አንተ ስለሆንክ፤ ፍጻሜው እንዲያምርም ሆነ እንዲያስጠላ የማድረግ ጥበቡ እና ችሎታው አለህ። በቲያትር ምሳሌ የተመሰለው አንተ ለራስህ ያለህ አመለካከት ወይም ምስል ነው (self Image).
⚫️ስዎች ለራሳቸው ያላቸው አመለካከት፤ ካሳለፉት የህይወት ልምድ፤ ከውድቀታቸው፤ ከስኬታችው እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ከሚያሳርፉባቸው ተጽዕኖዎች በመነሳት የሚሳል ምስል ነው። ይህ ስለራሳችን ያለን ምስል የኑሮዋችን ሁሉ ቁልፍ ነው። ሁላችንም ኑሮዋችንን የምንመራው ስለራሳችን ከያዝነው ምስል በመነሳት ነው። ስለራሳችን መልካም ምስል ካለን፤ ህይወታችንን ቀላል ያድርገዋል። ብዙዎቻችን ግን የተሳሳተ የራስ ምስል ስላለን፤ በኑሮዋችን መኖር ከሚገባን ደረጃ በታች እንድንኖር ተገደናል። መልካሙ ነገር ግን፤ ስለራሳችን ያለንን አመለካከት በማንኛውም ጊዜ መለወጥ መቻላችን ነው።
⚪️ምናልባት ለራሳችን ያለንን ምስል እስከዛሬ አስበንበት የማናውቅ ከሆነ፤ ዛሬ ማሰቡ መልካም ነው። ልክ ቅድም እንዳነሳሁት፤ የራሳችንን ህይወት በምናብ በትያትር መድረክ ላይ መተወን ብንችል እራሳችንን እንዴት አድርገን መሳል እንችላለን? በራሱ የሚተማመን፤ አይናፋር፤ ፈሪ፤ ተናጋሪ ወይስ ምን? ስለራሳችን ሌሎች ያስባሉ ብለን የምንገምተው ግምትም ፤እኛ ለራሳችን ካለን ምስል ጋር ጥልቅ ቁርኝት አለው።
⚫️ታዲያ ሰዎች ስለራሳቸው ትክክለኛ እና ጤናማ ምስል እንዲኖራቸው እንዴት ማድረግ ይችላሉ?
⚪️ሰዎች ለራሳቸው መልካም አመለካከት እና ምስል እንዲኖራቸው የሚረዱ አራት ዋና ነጥቦች እኒህ ናቸው። የሚከተሉትን አራት ነጥቦች በእለት ተዕለት ኑሮዋችን ማከናወን ከቻልን፤ ለራሳችን መልካም ምስል ከመያዛችን አልፎ፤ ከውጣችን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን እንዲሁም ከሌሎች ስዎች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንድንፈጥር ይረዱናል። እኒህ አራት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
፩) ያስቀየሙህን ሁሉ ይቅር በል
ያለምንም ቂም ሰዎችን ይቅር በል። ያስቀየሙህን ሰዎች በሙሉ ከልብህ ይቅር በላቸው፤ ይህንን የምታድረገው ለሌሎች ሰዎች ብለህ ሳይሆን፤ ለራስህ የአይምሮ ሰላም ስትል ነው። ቂም ለተያዘበት ሳይሆን ጉዳቱ ቂም ለያዘው ነው። ይህንን የመጀመሪያውን ትዕዛዝ ማክበር ከተሳነህ፤ ቀሪዎቹን ሶስት ነጥቦች ተዋቸው፤ ምክንያቱም ገና አልበሰልክም ማለት ነውና።
፪) እራስህን ይቅር በል-
እውነት ነው ሌሎችን ይቅር ከማለት በላይ እራስን ይቅር ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ከራስህ ጋርም ሆነ ከሌሎች ጋር ጤናማ ግንኙንት ለመፍጥር በመጀመሪያ እራስህን ይቅር ማለት አለብህ። ለሰራሃቸው ስህተቶች፤ ላጠፋሃቸው ጥፋቶች፤ ሌሎች ሰዎች ላይ ላደረግካቸው በደሎች ሁሉ እራስህን ያለምንም ቅራኔ ይቅር በለው። እራስህን በርህራሄ አይን ተመልከተው። ካንተ የሚወጣ ወቀሳ ከምንም በላይ በራስ መተማመንህን ዝቅ ያደርገዋል።
(፫) እራስህን በመልካም መነጸር ተመልከተው-
ቀንህን ስትጀምር ሁለት ምርጫዎች አሉህ፤ አንደኛ ቀንህን በጭንቀት መጀመሩ ሁለተኛው ደግሞ ቀንህን በራስ በመተማመን መጀመር። ሁሌም ሁለተኛውን ለመምረጥ ሞክር። በተቻለህ መጠን ቀንህን በብሩህ አይምሮ ለመጀመር ጣር።
፬) ከራስህ ጋር ብቻ ተፎካከር-
ያንተ የኑሮ አካሄድ ከአንዳንዶች ይፈጥናል፤ ከአንዳንዶች ይዘገያል። በምንም ተዓምር ያንተ ኑሮ ከሌላው ሰው ጋር ሊመሳሰል አይችልም። ስለዚህ ሌሎች ሰዎች ህይወታቸውን እንዴት እንደሚመሩ አያሳስብህ። የራስህን ኑሮ ኑር፤ ስለሌሎች ሰዎች ኑሮ ብዙም አትጨነቅ። በራስህ እርምጃ ተራመድ፤ ሌሎች ቀስ አሉ ብለህ አትዘግይ፤ ሌሎች ፈጠኑ ብለህ አትፍጠን። ጎዳናችሁም መድረሻችሁም ይለያያልና።
🔘እኒህን አራት ነጥቦች በእለት ተእለት ኑሮህ መተግበር ከቻልክ፤ በመጨረሻ ለራስህ መልካም ምስል ይኖርሃል፤ ያ ማለት ደግሞ በራስህ መተማመንህም አብሮ ይጨምራል ማለት ነው።
መልካም ጊዜ!!🙏
#ሼር ይደረግ
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence