የስምና የዝና ከርቸሌ
ከሚከተሉት መካከል የትኛውን ትመርጣለህ? በዓለም ላይ አንደኛ ጎበዝ ሆነህ እንደ አንደኛ ደደብ መታየት ወይስ የመጨረሻ ደደብ ሆነህ እንደ አንደኛ ጎበዝ መታየት?
ዋረን ቡፌት በሌላ አገላለፅ እንዲህ ያስቀምጠዋል። “ዓለም ሁሉ ማፍቀር የማይችል እያለህ ጎበዝ - አፍቃሪ መሆን ይሻልሃል ወይስ አንተ ፍቅር የማይገባህ ሰው ሆነህ - እያለ ዓለም በሙሉ ጎበዝ አፍቃሪ ቢልህ?” ይህንን በመመርመር ውስጥ ቡፌት ለጥሩ ሕይወት አንጓ ከሆኑ ነገሮች መካከል የሆነውን አንድ ነጥብ ያነሳል፡፡ ይህም በውስጥ ግምገማ (inner scorecard) እና በውጪ ግምገማ (outer scorecard) መካከል ያለው ልዩነት ነው፡፡
ላንተ ወሳኙ የትኛው ነው? “አንተ ራስህን እንዴት ነው የምታየው” የሚለው ነው። ወይስ “ሌሎች ሰዎች አንተን እንዴት ነው። የሚያዩህ” የሚለው?.. ትኩረትህ አንተ በራስህ ምን እንደምታደርግ በማስብ ፈንታ “ዓለም ስለኔ ምን ይላል” በሚለው ላይ ከሆነ የውጪ ግምገማ(outer scorecard) አፍቃሪ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ይህም ጥሩ ሕይወትን የማበላሻ አንዱ መንገድ ነው፡፡
የሌሎች ሰዎች አስተያየት ያለው ጥቅም አንተ “አለው” ብለህ ከምታስበው በታች የወረደ ነው። ይህ በድንጋይ ዘመን የቀረ ነገር ነው፡፡ ሰዎች አንተን በአድናቆት ሰማይ ቢያስነኩህ ወይም በትችት ከትቢያ ቢደባልቁህ ይህ በሕይወትህ ላይ የሚኖረው እውነተኛ ተፅዕኖ አንተ ለራስህ ከሚሰማህ ኩራትና ሀፍረት አንፃር በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
ስለዚህ ራስህን ነፃ አውጣ፡፡ ይህንን ማድረግ ያለብህ ደግሞ ስለ ሶስት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛ ይህ በስሜት የመዘፈቅ ሕይወት በአግባቡ እየመራህ የምትቀበለው አይሆንም፡፡ ወደድክም ጠላህም በጊዜ ሂደት ክብርና ዝናህን በአግባቡ መቆጣጠር አትችልም፡፡ ጂያኒ ኢጅኔሊን እንዲህ ይላል፡- “እያረጀህ ስትሄድ የሚገባህንና ትክክለኛውን ክብር (reputation) ታገኛለህ፡፡ ሰዎችን ለጊዜው ልታታልል ትችላለህ፤ በሕይወት ዘመን ሁሉ እንደሸወድክ መኖር ግን አትችልም፡፡”
ሁለተኛ በክብርና በዝና (prestige and reputation) ላይ ትኩረት ማድረግ (በትክክል ደስተኛ የሚያደርገን ነገር ምንድን ነው?› - የሚለውን አረዳዳችንን ይረብሻል፡፡ ሶስተኛ ያስጨንቀናል፡፡ ስለሆነም ይህ ለጥሩ ሕይወት ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነገር ነው፡፡
- እንደዛሬው ዘመን “ሰዎች ስለኛ ምን ይላሉ?” የሚለው ጭንቀት ጎልቶ የታየበት ወቅት የለም፡፡ ዴቪድ ብሩክስ እንዲህ ይላል “ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ሰዎችን ወደ ትንንሽ የብራንድ አስተዳዳሪነት ቀይሯቸዋል። ሰዎች ዛሬ ፌስ ቡክን፣ ቲውተርን፣ አጭር መልዕክትን እና ኢንስታግራምን እየተጠቀሙ የተጋነነ ውጫዊ ማንነትን ለመፍጠር ሲታትሩ ይውላሉ፡፡” ብሩክ
በፌስቡክ ላይ የምናገኛቸው የመጋራት (share) የመውደድ (like) እና ሌሎችም ግብረ መልስ መስጫዎች ሰዎች ለሰዎች ያላቸውን አረዳድ እንዲያንፀባርቁ የተቀረፁ ናቸው፡፡ በዚህ መንገድ ለሰዎች የምንሰጣቸው ግብረ መልሶች ደግሞ ፌስ ቡክ ላይ ባየነው መጠን እንጂ እውነተኛ ማንነታቸውን አውቀን የማይሆንበት እድል ሰፊ ነው፡፡ አንድ ጊዜ በዚህ መረብ ከተጠለፍክ ጥሰህ ለመውጣትና ጥሩ ሕይወትን ለመምራት ቀላል አይሆንልህም፡፡
#ትምህርት፡- ጭብጡ ምንም ይሁን ምን ሰዎች ስላንተ ሊፅፉና ሊያወሩ ይችላሉ። ከኋላህ እየተከታተሉ የሚያንሾካሹኩ ሰዎችም አይጠፉም። በውዳሴ ሊያሞካሹህ ወይም በትችት ሊኮንኑህ ይችላሉ። አንተ ይህንን መቆጣጠር አትችልም። ጥሩው ነገር ደግሞ መቆጣጠርም የሌለብህ መሆኑ ነው፡፡ ፖለቲከኛ ወይም ዝነኛ ሰው ካልሆንክ በስተቀር ገቢህ በማስታወቂያ ላይ የተመሰረተ አይሆንም፡፡ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ ስለዝናና ክብር (reputation) አትጨነቅ፡ ከመወደድና ከመውደድ ውጣ። ራስህን ጎግል ላይ አትፈልግ። ከዚያ ይልቅ የሆነ ነገር ሥራ።
ቡፌት እንዲህ ይላል- “እኔ ደስ የሚለኝን ነገር ግን ሌሎች ሰዎች የማይወዱትን ነገር ባደርግ ደስተኛ ነኝ፡፡ ነገር ግን እኔ የሰራሁትን ነገር ሌሎች ሰዎች ቢያደንቁልኝም፣ እኔ ግን የማልረካበት ከሆነ ደስተኛ አልሆንም።” ይህ የውስጥ ግምገማ (inner scorecard) ትክክለኛ አገላለፅ ነው። ስለዚህ በዚህ ላይ አተኩር። የውጪ አድናቆቶችንና ወቀሳዎችን ዝቅ ባለ ስሜት እያችው።
✍️ሮልፍ ዶብሊ
የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence