#ስለሒጃብ_የተከፈለ_መስዋዕትነት
✍ አሚር ሰይድ
ይህ ለሒጃባ ስትል የተሰዋችው ለጅልባቧ ስትል የሞተችው የአንደሉሷ ሙስሊም ሴት እውነተኛ ታሪክ ነው። ከስላና ተቃጥላ ስሰሒጃብ ስለክብሯ የወደቀች ድንቅ ሴት! ታሪኳ ሲደመጥ የብዙዎች ቀልብ አንብቷል። ስቃያቸው በስቃይዋ ተደምጧል። በሒጃባቸው ክብር ያልሰጡ አንስቶች ይገሰፁበት ዘንድ ታሪኳን እነሆ
ክስተቱን በአንደበቷ አንዲህ ትተርከው ይዛለች።
“የትውልድ ቀዬዬ አንደሉስ ምድር ነው። በሃያዎቹ የዕድሜ እርከን ውስጥ የምገኝ በሰውነት ቅርጼ ሞላ ደልደል ያልኩ ለግላጋ እንስት ወጣት ነኝ። ግና ይህን ሰውነቴን በጀልባብ ሸፍኜና ጠብቄ ሒጃቤን በአግባቡ እለብሳለሁ። የአንደሉስ ሙስሊሞች የስቃይን ፅዋ በመስቀላዊያኑ እጅ ሲጎነጩ እኔም አልቀረልኝም። ለሁለት ዓመታት የለበስኩትን ጅልባብ ሳላወልቅ ሳላጥብና ሳልቀይር እሥር ቤት ከረምኩ። በወታደሮች ግልምጫና ድብደባ መደፈርና መወገር ብዙ መከራዎችን አሳልፌ የመጨረሻዋ ቀን ላይ ደረስኩ።
የለበስኩት ጅልባብ ተሰብስቦ ጉልበቴ ጋር ደርሷል። ሰውነቴ በጭቃ ተለውሶ በእግረ ሙቅ ተጠፍሬያለሁ። እጄ የፊጥኝ ታስሮ አንገቴ ላይ በጠለቀው ሰንሰለት እየተጎተትኩ ወደፊት አነዳ ይዣለሁ። በብረት ፍርግርጉ ኋላ ሳልፍ ታሳሪዎቹ በሾሉ ዓይኖቻቸው አፍጥጠው እየተመለከቱኝ የስድብ ናዳ አወረዱብኝ ተፉብኝ። አፈር እየበተኑ ድንጋይ ወረወሩብኝ። የእሥር ቤቱ ጠባቂዎች ጅራፍ በእጃቸው ይዘው ከበቡኝ።
ቀሳውስቱ በአንድነት ቆመው መዝሙራቸውን ያሰማሉ። ባለሥልጣናትና ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው በሚደርስብኝ ስቃይ ለመደሰት ወደ እኔ በትኩረት ይመለከታሉ። ከአንድ ግንድ ጋር ታስሬ ማገዶ በዙርያዬ ተበትኗል። ዘይትና ጋዝ ተርከፍክፎበታል። ከቀሳውስቱ አንዱ ወደእኔ ተጠጋ። ሁለት ምርጫ አቀረበልኝ። ጀልባቤን አውልቄ በህዝብ ፊት ይቅርታ እጠይቅ ዘንድ ዓለይያም ተቃጥዬና🔥🔥ሰውነቴ ነዶ በመሞት መካከል ምርጫ ሰጠኝ። ሒጃቤን እንጂ ሌላን አልመረጥኩም። ከፈለጋችሁ አቃጥሉኝ አልኩ ስለሒጃቤ መሞቴ ለኔ ክብር መሆኑን አላወቁም። አልንበረከክም ፈፅሞ የጌታዬን ትዕዛዝ አልጥስም ብትፈልጉ ሰውነቴን ቆራርጡት በያሻችሁም አካሌን አንድዳችሁ አክስሉት። አዎ! በፍፁም በሒጃቤና በክብሬ አልደራደርም። የክብር መገለጫዬ በከፍታ የሚውለበለብ አስላማዊ ዓርማዬ ነው ብዬ መለስኩለት።
ቄሱ የእሳቱን ነበልባል አንስቶ እንጨቱን ለኮሰው። ሰውነቴ መቃጠል ጀመረ። በቀላሉ አንድሞት አልፈቀዱልኝም እሳቱን አጠፋዉ ። ወደ እሥር ቤቱ ወሰዱኝ። ይህ የእሥር ቤቱን አጥር ተደግፌ የፃፍኩት እውነተኛ ታሪኬ ነው
#ይህን ማስታወሻ የአስር ቤቱ ግርግዳ ላይ አስፈራው ተገኝ፡፡ አጀብ ለአኛ ክብር ስንቶች አልቀዋል።
በጋታው ጠዋት በተመሳሳይ ቦታ የፊጥኝ ታስራ ተሰቃይታ በእሳት ነደደች። ዛሬ ግን አንደ ትላንቱ አላጠፉላትም። ለዓመታት የኖረችበት ስቃይ እነሆ አበቃ። ግን ነፃነቷን አንደሰጧት አላወቁም።
#አላህ መልካም ስራዋን ተቀብሎ ቀብሯን ኑር ማረፊያዋን ፊርደውሰል አዕላ ያድርግባት።
⚠️የአሁን ዘመን ያለን ሴቶች አስተካክለን ሂጃብ የማንለብስ ነገ የዉመል ቂያማ ስንቀሰቀስ ለእስልምና ለሂጃባቸዉ ዋጋ የከፈሉ እንስቶች ጋር እንዴት አብረን እነሱ ጎን እንቆም ይሆን??
እስልምና በወንድ በሴት ሸሂዶች ደም ዋጋ ተከፍሎበታል...እኛስ ለእስልምና ለሂጃብ ምን ሰራን???
#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group