⚡️⚡️⚡️ #ጫማህን_ታሪክ_ስራበት⚡️⚡️⚡️
✍አሚር ሰይድ
አሜሪካውያን “ኢራቅ” ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ደገፉ፣ ዋና ዋና የሚባሉት የሚድያ ተቋማት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ጦርነቱ እንዲጀመር ቆሰቆሱ። በመጨረሻም የአሜሪካ ኮንግረስ ጦርነቱን (ወረራውን) አፀደቀ።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ እና ፖላንድ ወታደሮች ወደ “አራቅ" ዘመቱ። ጦርነቱም ተጀመረ። “ኢራቅ” ላይ ቦንብ ዘነበ፣ ጥይት ተርከፈከፈ....
☞ከ189 ሺህ በላይ የሚሆን የንፁሀን ዜጎች ሕይወት ተቀጠፈ፣
☞ከ 4 ሺህ በላይ የአሜሪካ ወታደሮች ሞቱ፣
☞ከ 32 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ ቆሰሉ።
☞ ከ 3 ሚልዮን በላይ ኢራቃውያን ከቀያቸው ተፈናቀሉ።
☞ ጦርነቱን ለመዘገብ የሄዱ 154 ጋዜጠኞች ተገደሉ፣ በታሪክ ብዙ ጋዜጠኞች የሞቱበት ጦርነትም ሆነ።
የሰዎች ሀብት ንብረት ተዘረፈ፣ ወደመ፣ መሠረተ ልማቶች አመድ ሆኑ። ፕሬዝዳንት "ቡሽ" ጦርነቱ "cakewalk" ነው ብለው አቅለውት የነበረ ቢሆንም 9 ዓመት ሙሉ ፈጀ (ከ2003 አስከ 2011 ድረስ) ።
መጨረሻ ላይ "ሳዳም ሑሴን” ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ። በአሰቃቂ ሁኔታም ተገደሉ። አሜሪካውያን ለመንግስት በታክስ መልክ የከፈሉት "1 ትሪልዮን ዶላር" በቀጥታ ለጦርነቱ ውሏል። ይህ ማለት እያንዳንዱ አሜሪካዊ በአማካይ ለጦርነቱ 3200 ዶላር አዋጥቷል። በዚህ አሰቃቂ ጦርነት የወጣው ገንዘብ ለውሀ መሰረተ ልማት ቢውል ዓለም ላይ ለሚገኙ እያንዳንዱ መንደሮች አስከወድያኛው ውሀን ማቅረብ ይችል ነበር።
ብዙ ሚድያዎች ጦርነቱ እንዲጀመር በመገፋፋታቸው ተፀፀቱ። ዓለም አፈረች፣ ተሸማቀቀች። እነዚህ ሰዎች ሳዳም ሑሴንን ከስልጣን አንስተው፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውና ሀገሪቷን እንደዛ አንኮታኩተው ሄዱ።
ጊዜው በፈረንጆቹ አቆጣጠር ታህሣስ 14, 2008 ነው። የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት “ጆርጅ ቡሽ” ስልጣኑን ሊለቅ ጥቂት ሳምንታት ነበር የቀረው። ቡሽ ወደ “ኢራቅ” ተጉዞ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር በነበሩት "ኑር -አል መሊክ” ቤተ-መንግስት ውስጥ በጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጠ ነው። ቤተ መንግስቱ ውስጥ ብዙ ጋዜጠኞች ተሰይመዋል።
ጆርጅ ቡሽ ወሬውን መቅደድ ጀመረ። በዚህ መሐል አንድ አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ። "ሙንተዘር አልዘይድ" የተባለ የ28 ዓመት ኢራቃዊ ጋዜጠኛ ጫማውን አውልቆ ፕሬዝዳንት “ቡሽ” ላይ
هذا هدية الوداع من شعب العراق ياكلب
" #ይህ_ከኢራቅ_ሕዝቦች_የተላከልህ_የስንብት_ሰላምታ_ነው_አንተ_ውሻ..." ብሎ ወረወረው፡፡ ወድያውኑ የቤተ መንግስቱ ጥበቃዎች ጋዜጠኛውን እየመቱና መሬት ላይ እየጎተቱ ወሰዱት።
....ፍርድ ቤት ቀርቦም የሶስት ዓመት እስራት ተፈረደበት። ነገር ግን በእስር ቆይታው ጥሩ ፀባይ በማሳየቱ በዘጠኝ ወሩ ተለቀቀ።
ይህ ልጅ በዓለም ሙስሊሞች ዘንድ “ጀግና” ተባለ። ብዙ ዐረቦች ልጆቻቸውን ሊድሩለት እንደሚፈልጉም ጭምር ተናገሩ። ስጦታዎች ተዥጎደጎዱለት።
አንድ የሳዑዲ ባለሀብት ጫማውን 10 ሚልዮን ዶላር ከፍለው ገዙት። ኢራቃውያን እነዚህን ታሪካዊ ጫማዎች የሀገሪቱ ሙዝየም ውስጥ በክብር እንዲቀመጡ አደረጉ።
ይህን ጋዜጠኛ ጫማውን ፕሬዝዳንቱ ላይ ለምን እንደወረወረ ሲጠየቅ እንዲህ ይላል : -
"... ፕሬዝዳንቱ የኢራቃውያንን ደም ጠጥቷል። ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል የዳረገን እሱ ነው። ወደ ኢራቅ ሲመጣ የአበባ ጉንጉን ይዘን እንድንቀበለው ነበር አንዴ የጠበቀው? ጫማዬን ያስወረወረኝ ውስጤ የነበረው የተከማቸ ንዴት ነበር። ይህንን በማድረጌ ልገደል እንደምችል አውቃለው። በኛ ባህል ጫማን መወርወር የመጨረሻው የጥላቻ ማሳያ ነው። ጥላቻዬን የምገልፅበት ብቸኛው መሳርያዬ ጫማዬ ነበር! ይህንን በማድረጌ ብዙ ስቃይ ደርሶብኛል። እስር ቤት ውስጥ ተደብድቤያለሁ፡ ቶርች ተደርግያለሁ ጥርሴን አውልቀውታል። ነገር ግን ድጋሜ እድሉን ባገኝ እንኳን አሁንም ጫማዬን እዚህ ግፈኛ ሰው ላይ ከመወርወር ወደ ኃላ አልልም፡፡ ብሎ መለሰላቸዉ
ምን ለማለት ነው ወንድሜ አንተም ጫማህን ታሪክ ስራበት!
#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group