#የነፍሴን_ዝንባሌ_ጣልቃ_አላስገባም
✍ አሚር ሰይድ
በአንድ ውጊያ ላይ ዓሊ (ረ.ዐ) አንድን አይሁድ መሬት ላይ ጥለው ሊገድሉት በተዘጋጁበት ሰዓት ፊታቸው ላይ ምራቁን ተፋባቸው። በዚህ ጊዜ እንዳች ዓይነት የብቀላና ግላዊ ስሜትን የተንተራሰ ንዴት በውስጣቸው ተቀጣጠለ፡፡
የአላህ አንበሳ በመባል ለሚታወቁት ዓሊ (ረ.ዐ) ይህን ሰው በሰይፍ ቆራርጦ መጣል እንደ ህፃን ጨዋታ ቀላል ነበር። ሆኖም ግን ዓሊ (ረ.ዐ) ያን በማድረግ ፈንታ በወደቀበት ትተውት በመነሳት ዘወር አሉ ፡፡ ከዚያም ሰይፋቸውን ወደ ሰገባው መለሱ፡፡
በድንጋጤ ሞቱን ይጠባበቅ የነበረውና በውርደት መሬት ላይ በጀርባው የተንጋለለው ሰው በሁኔታዉ በጣም ተደነቀ፡፡ እርሱ ይጠብቅ የነበረው ዓሊ (ረ.ዐ) መጀመሪያም መሬት ላይ የጣሉት በመሆኑ ምራቁን ሲተፋባቸው የዚያ ንዴትና ለምን ተደፈርኩ ባይነት ተጨምሮ በቅፅበት እንደሚከታትፉት ነበር፡፡ ሆኖም ግን እርሱ እንዳሰበው ሳይሆን ቀረ፡፡ ያ ሰው ያንን የኢስላም ጀግና እንዲሁም በያንዳንዱ ሙስሊም ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን ሰው በጉጉት ጠየቀ፡-
⚡️⚡️⚡️“አሊ ሆይ! ልትገድለኝ እየቻልክ ለምን ይሆን የተውከኝ? ሀሳብህን እንድትቀይር ያደረገህ ነገር ምንድን ነው? ያን ከመሰለ አስፈሪ ሁኔታ በአንድ ጊዜ የቀዘቀዝከው ምን ሆነህ ይሆን…?''ብሎ ጠየቀ
ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት መልስ ሰጡት፡-
ይህን የነብዩን ﷺ ሰይፍ የምጠቀምበት በአላህ መንገድ ላይ ብቻ ነው፡፡
#የነፍሴን_ዝንባሌ_ጣልቃ_ላስገባ_አልፈልግም:: አንተ ምራቅህን ስትተፋብኝ ልታናድደኝ ፈልገህ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ በዚያ ሁኔታ ላይ እያለሁ ብገድልህ ለአላህ ብዬ ሳይሆን ለነፍሴ በማድላት ይሆንብኛል ብዬ ፈራሁ፡፡ ልጋደልህ የፈለግኩት ለአላህ ብዬ ሲሆን የራሴን ክብር በመከላከል እንዳልገድልህ በመስጋቴ ነበር የተውኩህ"
በዚህ ጊዜ በኢስላም ኃይማኖት ረቂቅ እሳቦትና ሕይወት ባላቸው አስተምህሮቶቹ ልቡ የተነካው ያ ሰው ኢስላምን ተቀበለ።
የዓሊ ረዐ ኢኽላስ ምን ያህል ጥልቀት ቢኖረዉ ነዉ ግን
በእሳቸዉ ኢኽላስ ሰዉየዉ እስከመስለም ድረስ የደረሰዉ??
እኛስ ያለን ኢኽላስ ፈትሸነዉ እናቃለን❓❓❓
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group