እነማን እንደሚያስገርሙኝ ታውቃላችሁ…?
ሙስሊም ያልሆኑ ደንበኞቻችን ደስ እንዲላቸውና ዝም ካልን እንዳይከፋቸው በሚል እሳቤ፤ በነርሱ በዓላት ወቅት የ«እንኳን አደረሳችሁ!» መልዕክት የሚያስተላልፉ ሚዛናዊና አካታች መስሎ መታየት የሚሹ ሙስሊሞችና ባለቤትነታቸው የሙስሊም የሆኑ ተቋማት።
ልንገራችሁ… ወላሂ! ቢዝነሱ በዚህ አይፋጠንም። ይህን ማድረጋችሁ ደንበኛ ላለመሸሹ ዋስትና አይሆንም። ይህን ማድረግም ለደንበኛ መቀነስ ሰበብ አይሆንም። ቁም ነገሩ የምትሰጡት ሰርቪስ ታማኝ፣ አስተማማኝ፣ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ይሁን። ያኔ የሚጠላችሁ ሰው ሳይቀር በሌላ ሰው አስልኮም ቢሆን ሰርቪሳችሁን ይጠቀማል ወይም ምርታችሁን ይገዛል።
የእውነት እነርሱን የማስደሰትን አላማ ፈልጋችሁ ከሆነ፤ እምነታቸውን መከተል ብቻ ነው ያንን ጎል ማሳካት የሚችለው። ይህን ደግሞ እኔ በሪሰርች አጥንቼ ሳይሆን የፈጠራቸውን ፍጡሮች ቀልብና ውስጥ ሚስጥር ጠንቅቆ የሚያውቀው ረቂቁ ውስጥ አዋቂው ጌታችን አላህ በተከበረው ቃሉ ላይ ነግሮን ነው።
(وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ)
"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡"
[አል-በቀራህ: 120]
★
ታዲያ ከአላህ በላይ እውነት ተናጋሪ አለ እንደ⁉️ በጭራሽ!
(… وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا)
«… በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?!»
[አ-ን'ኒሳእ: 122]
*
(… وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا)
«… በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?!»
[አ-ን'ኒሳእ: 87]
★
አላህ ከፈለገ የቱንም ያክል ብታስደስታቸው እንኳን እነርሱን ሙስሊሙን ከስተመርህንም ይበታትነዋል። በመንገዱ ከሆንክ ግን አብሽር!
«من التمس رِضا اللهِ بسخَطِ الناسِ ؛ رضِيَ اللهُ عنه ، وأرْضى عنه الناسَ ، ومن التَمس رضا الناسِ بسخَطِ اللهِ ، سخِط اللهُ عليه ، وأسخَط عليه الناسَ!»
«ሰዎች ቢቆጡትም የአላህን ውደታ የፈለገ ሰው፤ አላህም ይወደዋል። (ምንም እንኳ ሰዎች ሊጠሉት ቢፈልጉም፣ የሰዎችን ልብ ቀያያሪ የሆነው አላህ ነውና) ሰዎችም እንዲወዱት ያደርግለታል። አላህን እያስቆጣ የሰዎችን ውደታ የፈለገን ሰው፤ አላህም ይጠላዋል። (ምንም እንኳ ሰዎቹ እንዲወዱኝ ብሎ የሚወዱትን ነገር ቢሠራላቸውም፤ አላህ ቀልባቸውን መቀያዬር ስለሚችል) ሰዎችም እንዲጠሉት ያደርጋቸዋል።»
[ሶሒሑ-ት'ተርጚብ: 2250፣
አ-ት'ቲርሚዚይ: 2414፣
ኢብኑ ሒባን: 277]
ከዚህ በኋላ ምርጫው የናንተ ነው።
||
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
ረጀብ 07, 1446 ዓ.ሂ.
↓↓↓
t.me/MuradTadesse