መጥፎ በሆኑ በማይፈቀዱ ቪድዮዎች ፎቶዎች እና የወሲብ ፊልሞችን በመመልከት ለተፈተነ ትልቅ ምክር ‼️
بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ
الحمد الله رب العالمين
ሀይ እና ቀዩም የሆንከው ጌታዬ አላህ ሆይ!ሰማያትና ምድርን አስገኚ የሆንከው አላህ ሆይ!የአለማቱ ጌታ ሆይ!ልባችንን ከዚህ ፈተና አድንልን! አላሁመ አሚን
በመጀመሪያ ለኔና ለወንድሞቼ የምመክረው ነገር አይን ከአላህ የተቸረች ፀጋ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ነው።
ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች ውስጥ ነው። ከፀጋም በያሰከንዱ የሚደጋገም ፀጋ ነው። ስለሆነም አላህን በመታዘዝ ላይ መዋል ይኖርብናል። አላህን በማመፅ ላይ ልናውለው አይገባም። የአላህን ፀጋዎች አላህን በማመፅ ያዋለ ምንም እንኳን ፀጋዋ ብትኖርም ሊያጣት ደርሶዋል።
#ሁለተኛ! ረሳችንን ማስታወስ ያለብን ስለዚህች አይን አላህ ፊት የምንጠየቅ መሆኑን ነው። በክፍልህ ውስጥ ተቀምጠህ ማንም በሌለበት ማንንም ሰው አያይህም ከዛም ይህን ልታይ ስታስብ አላህ ፊት የምትቆም መሆንክን አስታውስ ስለዚህች አይን እንደምትተየቅ አስተውል።
ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል'ከናንተ ውስጥ በእሱና በጌታው መካከል አስተረጓሚ ሳይኖር ጌታው የሚያናግረው ቢሆን እንጂ የለም። ወደ ቀኝ ይመለከታል የሰራውን ስራ እንጂ ሌላን አይመለከትም ወደ ግራም ይመለከታል የሰራውን ስራ እንጂ ሌላን አይመለከትም ወደፊትለፊቱ ሲመለከት ⇝እሳትን እንጂ ሌላን አይመለከትም'ብለዋል። ይህ እንደሚጠብቀው ያስታውስ።
#ሶስተኛ አላህ አብሮት እንደሆነ ያስታውስ አላህ የይሃል አላህ እንደሚሰማውና አላህ እንደሚያውቅበት ያስታወስ አላህ በመስማቱ በማየቱና በእውቀቱ ከሱጋር መሆኑን ያስታውስ። ብቻህን ስትሆንና ይህን መጥፎ ቆሻሻ ፊልም ስትመለከት አላህ አሁን እያዬ መሆኑን አስታውስ"(በዚህ ሁኔታ ላይ ቢይዝህስ?)"አላህ በሁኔታህ አዋቂ ነው።'ብቻዬ ነኝ አትበል አላህ እያየህ መሆኑን ለነፍስህ አስገንዝባት። በመቀጠልም ወንድሜ ሆይ!አላህን በመታዘዝም አላህን በማመፅም ግዜ ያልፋል ግዜ አላህን ለሚታዘዙትም ለሚያምፁትም ቆሞ አያቅም። ይህችን ትንሽዬ ደቂቃ በመታገስ ካሳለፍካት ግዜህን ወንጀል ሳይፈፀምባት እንደምታልፍ ነፍስህን አስታውሳት። ግን ይህን ወንጀል ከፈፀምክባት ግዜዋ በወንጀል ታልፋለች። በልቦነህ ውስጥም መበላሸትን አውርሳህ ታልፋለች ህይወትህንም ጭንቅ ታደርግብሃለች የመጥፊያ ምክንያትም ልትሆንብህ ትችላለች። ልትሰጥ የነበረውንም ፀጋ ልትከለክልህ ትችላለች። ነፍስህን በዚህ አስታውሳት።
#በመቀጠልም...አይንህ ባንተ ላይ እንደሚመሰክርብህ አስታውስ ባየሃቸው ነገሮች አይንህ አላህ ፊት ትመሰክርብሃለች። ስለሆነም አላህን ፍራ የሱን(የአላህን)ጉዳይም አክብር ይህን ካደረክ በአላህ ሀይልና ፍቃድ ሸይጧንን ታሸንፋለህ።
#በመጨረሻም ዱዓ በማብዛትም አደራ እላለሁ በወንጀል የተፈተነ ሰው የለሊቱን መጨረሻ ላይ(ዘጠኝ ሰአት አከባቢ)አላህ ፊት ይቁምና ጌታዬ ሆይ!ማረኝ
ጌታዬ ሆይ!አንተ ሁኔታዬን ታውቃለህ ጌታዬ ሆይ!በዚህ በሽታ ተፈትኛለሁ እንድጠላው አድርገኝ ። አላህ ሆይ !ምስራቅና ምዕራብን እንዳራራከው ሁሉ በእኔ እና በሱ(በወንጀሉ)መካከል ሰፊ መረራቅን አድርግ እያለ መማፀን ይኖርበታል የምር ወደ አላህ መመለስ የሰውዬው ሁኔታ ከሚስተካከልባቸው መንገዶች ዋነኛው መንገድ ነው........።
ባረከላሁ ፊኩም በዱዓችሁ አትርሱኝ
ሼር ማድረግ አንርሳ የአንድ ሰው የመመለስ ሰበብ መሆን ትልቅ ነገር ነው ብዙ እህትና ወንድሞች ከዚህ ስቃይ ለመውጣት ተቸግረዋል የችግሩን መፍትሄም በግልፅ ለመጠየቅ ስለምንፈራ ለብዙ ግዜ ተጎጂ እየሆን ነው።
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇
@Lewetatoch_mekir@Lewetatoch_mekir