የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት አባላት በድሬዳዋ ከተማ በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው ከሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
በባንኩ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ እና በዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ሰብሳቢ በዶ/ር አክሊሉ ገ/ሥላሴ የተመራ ቡድን በደሬዳዋ ከተማ የሚገኙ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን፣ፋብሪካዎችን እና አስመጪና ላኪዎችን በትናትናው ዕለት የጎበኙ ሲሆን፤ ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ በከተማዋ በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጋር በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው አዳነ ሆቴል ውይይት አካሂደዋል፡፡ የባንኩ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አክሊሉ ገ/ስላሴ የውይይት መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት የዚህ ስብሰባ ዋና አላማ አንበሳ ባንክና የድሬዳዋ የንግድ ማህበረሰብ ተቀራርበው በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ለመምከር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የንግዱ ማህበረሰብ አባላትም ቢመለሱልን ያሏቸውን ነጥቦች ያነሱ ሲሆን፤ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በበኩላቸው በደንበኞች የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ፤ የባንኩ ደንበኞች በሚያደርጉት የንግድ እንቅስቃሴ ላይ አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት ገልፀዋል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትም አሁን ላይ ከባንኩ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይም በዙሪያቸው የሚገኙ ሌሎች የንግዱ ማህበረሰብ አባላትን ከባንኩ ጋር አብረው መስራት እንዲችሉ የራሳቸውን ሚና እንደሚጫቱ እና እነርሱም ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከዚህ በበለጠ መልኩ አጠናክረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!