አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የትግራይ የኢንዱስትሪ ማሽነሪ ማምረቻ ማሕበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አደረጉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የትግራይ የኢንዱስትሪ ማሽነሪ ማምረቻ ማሕበር ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የፊርማ ሰነ- ሰርአት ስምምነት ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አካሂደዋል። የፊርማ ስነ-ስርአቱ በባንኩ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ እና በማሕበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ሳምሶን ግርማይ ተካሂዷል።
ባንኩ ከማሕበሩ እና በስሩ ከሚተዳደሩ ተቋማት የሚቀርቡለትን ወቅታዊ የገንዘብ ፍሰት ጥያቄዎች፣የብድር አቅርቦት፣ የምክር አገልግሎት እና ተያያዥ ሰልጠናዎችን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል ሁኔታ ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ ማህበሩ እና የማህበሩ አባላትም ያላቸውን የሂሳብ እንቅስቃሴ በባንኩ እንደሚያደርጉ ማህበሩ ገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ ባንኩ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ከምንጊዜውም በበለጠ መልኩ በስፋት እንደሚሰራ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከሰተ የገለፁ ሲሆን፤ ከዚህ ጎን ለጎንም የማህበሩ አባላት የባንኩን አክሲዮን በመግዛት የባለቤትነት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ እና ባንኩ በፋይናንስ ሴክተሩ ላይ በሚያደርገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!