አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የግማሽ በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ፡፡
የአንበሳ ባንክ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት፣ የዋና መ/ቤት የስራ ኃላፊዎች እና የዲስትሪክት ስራ አስኪያጆች በባንኩ የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ዙሪያ ዛሬ ጥር 17 ቀን 2017 ዓ. ም በአዲስ አበባ ሐርመኒ ሆቴል ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የባንኩ የ2016/17 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ ባንኩ በዋና ዋና የአፈፃፀም መለኪያዎች ስኬታማ ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በውይይቱ ላይ እንዳስገነዘቡት እስካሁን የተመዘገበው አፈፃፀም አበረታች ቢሆንም ለበጀት ዓመቱ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በተቀማጭ ገንዘብ ማሳደግ፣ በውጪ ምንዛሬ ግኝት፣ በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ማስፋፋት እና የባንኩን የተከፈለ ካፒታል በማሳደግ ዙርያ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
ስለሆነም የቀሪው ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ ለማድረግ አሁን የታዩ ጉድለቶችን አርሞ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል ዕቅድ ተነድፎ በትጋት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።
በስብሰባው የዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ የሦስት ሪጅኖች እና 13 ዲስትሪክቶች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!