ምድርን ማሳመር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የተለያዩ የዳዕዋ እና ወቅታዊ ምስል , ፅሁፍ እና ቪዲዎች የሚለቀቁበት ቻናል

መጪው ግዜ የኢስላም ነው!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




ከቦታው ሆኖ የተመለከተውን የጀግንነት ትዕይንት ሊተርክልን ተዘጋጅቷል። "በዓይኔ ያየሁት ክስተት ነው ቦታው ላይ ተገኝቼ የተመለከትኩት" ሲል ንግግሩን ይጀምራል። "ስሙኝ የአላህን ተዓምር ትመለከቱበታላችሁ" እያለ ዓይኖቹን ያማትራል።
ይህ ጋዛ ውስጥ የተከሰተ እውነተኛ የፅናት ታሪክ ነው።

ከሙጃሂዶች አንዱ ያወጋውን እንካችሁ

"የጠላትን ጦር ለማደባየት ያሲን የተሰኘውን ሚሳኤል በትከሻችን ይዘን ጉዞ ጀመርን። በአሚራችን ቦታ ተመርጦ የጥቃት መዳረሻችን ተነገረን። ስትራቴጂያችን ወደተነደፈበት ስፍራ ወደ ሹጃዒያ አቀናን። ጠላት እስኪመጣ ጠበቅን። በልዩ ኃይል የታጀበ ሰራዊት ከቦታው ደረሰ። ዙርያ ገባውን ከቦ ያገኘውን ሁሉ በታንክ መነገለ። በከፍተኛ የተኩስ ሽፋን ቦታው ላይ ሊሰፍር ተዘጋጀ። የከባባድ መሳርያው ድምፅ ጀግንነትና ኩራት እንዲሰማን አድርጎ ለሸሂድነት አጓጓን።

አምስት ነን። አራታችን ወደ ጦሩ ከተቀላቀልን ገና አመታችን ነው። በጦርነቱ መሐል ነው የሰለጠንነው። መሪያችን ከኛ በዕድሜ የገፋና ከቀደምት ጦርነቶች የላቀ ልምድ አለው። ከፊታችን ቆሞ ለመጀመርያ ጊዜ በሰማናቸው ቃላቶች ያነሳሳን ጀመር።
"በምቾቱ ወቅት አላህን ያልዘነጋ በመከራው ጊዜ ያስታውሰዋል። ምን ትጠብቃላችሁ የአላህን ጠላቶች ለማጥቃት ጌታችን አክብሮ መርጦናል። የጂሃድ መንገድ በፅጌረዳ የተፈረሸ አይደለም" አለና ሰላም በልባችን ላይ እስኪሰፍን ድልና ፅናት አላህ እንዲወፍቀን ዱዐ አደረገልን። እኛም ተቀብለን አሚን አልን።

በብረት የተሸፈኑትን ነሚርና ሜርካቫን ጨምሮ በርካታ የጦር ተሽከርካሪዎች ዶግ አመድ አደረግን። ፍርስራሹን እየረገጥን ከቦታ ቦታ እያቀናን ጥቃታችንን ቀጠልን። በተምርና በአንድ ጉንጭ ውሀ ለሶስት ቀናት አሳለፍን። በመጨረሻው ቀን አንዲት ጥይት ብቻ ቀረችን። የተሻለውን መንገድ በመምረጥ ላይ ሳለን የተፈለገው ኢላማ ዓይናችን ውስጥ ገባ። ነሚሩ እየተምዘገዘገ ከሜዳው ሰፈረ። አምስታችንም የያሲንን ሚሳኤል ጨበጥን። ከጦር መሪው ጀምሮ ሁላችንም በትከሻችን አስደግፈን ልንተኩስበት ተሽቀዳደምን። እኔ እኔ የሚሉ ድምፆች ይሰሙ ጀመር። ወንጀሌ ይማርልኝ ዘንድ ይህን ዕድል አትንፈገኝ ይላል አንዱ። ቀበል አድርጎ ለጀነት ጓጉታለች ነፍሴ የሚገባኝ እኔ ነኝ ይላል ቀጥሎ ያለው። ሁሉም ለሌላው ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆን አልን። በዕጣ እንዲወሰን መሪያችን ትዕዛዝ አስተላለፈና ተስማማን። እጣው ተጣለ በልማዳችን መሰረት ሸሂድ ሆኖ አላህን የመገናኘት ዕድሉ ሰፊ ነውና የደረሰውን አቅፈን ተሰናበትነው። ግንባሩን እየሳምነው ሳለን ከመሐላችን አንዱ እንባውን እየዘረገፈ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።

"ምን ነካህ ምን ሆነሃል?!" ብለን ጠየቅነው። ከለቅሶው ብዛት መናገር እንኳ ተሳነው። እስኪረጋጋ ጠበቅነው። ከወደቀው የቤት ምሶሶ አጠገብ ተደግፎ ቁጭ አለ። አጠገቡ ተሰብስበን ዕንባውን እየጠረግንለት ምን እንደገጠመው ዳግም ጠየቅነው።
"ዛሬ ቃል የተገባልኝን ጀነት ልትነፍጉኝ ፈለጋችሁ" አለን። ደነገጥም እርስ በርስ እየተያየን "ምን ነካህ" ስንል ጠየቅን። "ምን እያልክ ነው" አልነው
እሱም መለሰ እንዲህም አለ...
"ትናንት ማታ ከፍርስራሹ መሐል ልተኛ ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝና የአላህ መልዕክተኛን በህልሜ ተመለከትኩኝ። ነገ እኛ ጋር ምሳ ተጠርተሀል አሉኝ" አለና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ትንፋሹን ዋጥ አድርጎ ንግግሩን ቀጠለ:-
"በኔና በአላህ መካከል የነበረው ይህ ምስጢር እንዲገለጥ አልፈለኩም ነበር። ዕጣ ሲወጣ እንደማሸንፍ እርግጠኛ ነበርኩ ግና ለሌላ ሰው ወጣ" አለና ዳግም ተንሰቅስቆ አነባ።

በዕጣ የተመረጠው ተዋጊ ቀረብ አለና "በአንድ ቅድመ ሁኔታ የደረሰኝን ዕጣ ለአንተ አሳልፌ እሰጥሃለሁ" አለው።
ከተቀመጠበት ቆመና "የምትፈልገውን ጠይቀኝ አደርገዋለሁ" ሲል መለሰለት
"አላህ በሸሂድነት ካከበረህ ሰላምታዬን ለረሱል ታደርስልኛለህ የውመል ቂያማም አማላጄ ትሆናለህ" ሲል ተናገረ።

በቀላል ትጥቅ እየተዋጋን በችግር ቸነፈር መሐል ሆነን በዚህ ንግግር ህመማችንን ረሳን። አብዝተን አለቀስን። ተንሰቅስቀን አነባን። ሁላችንም ለደቂቃዎች ተቃቀፍን።
(ወንድሞቼ ምናል አብሬያችሁ ሆኜ ጀሰዴ ከጀሰዳችሁ በተዋሀደ)

ተራኪው ንግግሩን ቀጠለ...
ወንድማችን መሳርያውን ሸከፈ። በአላህ ይሁንብኝ ፊቱ በብርሃን ተሞልቶ ተመለከትነው። ጉልበትና ኃይልን ከአላህ ተችሮ አየነው። የቲሃማ ተራራን እንዲያንቀሳቅስ ቢጠየቅ ሊያንቀስበት የሚችልን ዓይነት ወኔ ተላብሶ አስተዋልነው። ተሰነባበትነው። ከመሄዱ በፊትም አላህ በሰማዕትነት ካከበረው የውመል ቂያማ አማላጃችን እንደሚሆን ቃል አስገባነው።

ወደ ውጊያው ሜዳ ተመለሰን ከአንዱ ጥግ አደፈጥን ... ትዕይንቱን በዓይናችን ለመከታተል ተዘጋጀን ... ጠላት ከመሸገበት ጦር ሜዳ ሰርጎ ገባ። የተነደፈውን እቅድ በትክክል አሳካ። ወደ ነሚሯ አነጣጥሮ ተኮሰ። አልሳተውም ከዒላማው አርፎ ተቀጣጠለ። የእሳት ነበልባሉን እያየን ተክቢራ አሰማን። ጥቃቱን ፈፅሞ ወድያው እንዲመለስ ታዟልና በፍጥነት ጀርባውን አዙሮ ሲመለስ ከሌላ አቅጣጫ ያደፈጠ የጠላት ልዩ ሃይል መኖሩን አስተዋለ። ከሩቅ እያየነው አካሄዱን ሲቀይር ተመለከትነው። ምን እየሰራ ነው!!?? ስንል ተጠያየቅን። ወደ ወራሪዋ ጦረኞች ነበር ያቀናው። ለእኛ መውጫ ለማመቻቸት በባዶ እጁ አቅጣጫ ቀይሮ ወደነርሱ ዚግዛግ እየሮጠ ለማዘናጋት ሞከረ። እንድናመልጥ ማመቻቸቱ ነበር። የጦር አውሮፕላን በቦታው ደርሶ ከሰማይ ቦንቡን እያርከፈከፈ አካባቢውን ሲያጋይ እኛ በሰላም ወጣን። ስለ እሱ ግን ምንም የምናውቀው ነገር አልነበረም።

ከሶስት ቀናት በኋላ ሠራዊቱ አካባቢውን ለቆ ሲወጣ ወደቦታው ተመለሰን እንፈልገው ጀመር። በደም ተነክሮ ንጹሕ ሥጋው ትኩስ ሆኖ አገኘነው። ወደ ሌላ ቦታ ጀናዛውን ለማሸጋገር ርቀት ስለነበረው አካባቢው ሰላም እስኪሆን ለጊዜው ከፈራረሱት ቤቶች መሐል ቀበርነው።

ከአንድ ወር በኋላ መቃብሩን ቆፍረው ወደ መቃብር ስፍራ ወስደን ለመቅበር ወደ ቦታው አቀናን።
ተራኪው የሚለውን አድምጡ፡-
"በአላህ እምላለሁ ቀብሩን ስንቆፍር ትኩስ በዚያች ሰዓት የተቀበረ ይመስል ከሰውነቱ ደም ይንጠባጠብ ነበር። አይተነው አነባን። ለአላህ ታመነ አላህም ለእርሱ ታመነለት። ይህ ወጣት የ19 አመት ታዳጊ ነበር.. አላህ ቀብሩን ኑር ማረፊያውንም ጀነተል ፊርደውስ ያድርግለት። የተመኘውን የሹሃዳኦች ደረጃ ይወፍቀው።

ለአላህ የገቡትን ቃልኪዳን የሞሉ ጋዛ ምድር ላይ አሉ። የጂሃዱን ባንዲራ የሚቀባበሉ። ከሜዳው የተሰለፈው ሸሂድ ለቀጣይ ወንድሙ የሚያስረክበው።

ይህ ጋዛ ነው
ከብዙ ታሪኮች ውስጥም ይህ አንዱ የጀግንነት ገድል ነው። አላህ ይቀበላቸው።
©Mahi Mahisho


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




خاتمة تستحقها يا من ايقظت الرجولة في امتنا. يا ضيف الله الحبيب.
ያለ ኢ*ስማዒል ሃኒያ
ያለ የሕ*ያ ሲንዋር
ያለ ሙሐመድ ደይፍ (ሸሂድ ከሆነ 7 ወራት አልፏል) ነው ቀሳምም ይሁን ሐማስ ወራሪቷን ለድርድር ጠረጴዛ ያስቀመጡት። ይህ የሚያሳየው ስብስቡ የመሪም ይሁን ስትራቴጂ ድርቀት እንደሌለበት ነው።

يارب على دربهم
©Abdurahman seid






ባለ የ9ነፍስ በመባል የሚታወቀው ወራሪዋ ከማንም በላይ የምትፈራው የጡፋን አቅሳ መሪ መሃመድ ደይፍ ሸሂድ ሆኗል !

ያ አላህ ! እዝነትህን መሪ አታሳጣን 😥


ሸሂዱል ኡማ 😥
መሀመድ ደይፍ (አቡ ኻሊድ)




ቁርኣንን በአደባባይ በማቃጠል የሚታወቀው ኢራቃዊው ክርስቲያን ሰልዋን ሞሚካ በስዊድን በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
©https://t.me/Yahyanuhe


አህመድ አሽ ሸርዕ የሶርያ የሽግግር ግዜ ዋና ፕሬዚዳንት ሆነው መሰየማቸውን ከምሽቱ የሶርያ ሚሊተሪ ኮማንድ ሃላፊው ገልፀዋል !


ሙጃሂድ ኡመር ሙኽታር
ሙጃሂድ የህያ ሲንዋር


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እኛ እጅ አንሰጥም
ወይ እና እናሸንፋለን
ወይ እንሞታለን


ካልተቆረቆረ ደም በነካው እጅ፣
መቼ ይከፈታል የነጻነት ደጅ።
©Fuad adem

ይህ ምስል "የተደበቀው የበለጠ ነው " በሚል አልጀዚራ በሰራው ዶክመንተሪ የህያ ሲንዋር በውግያ ወቅት ነፃነት ደም በነካው እጅ እንጂ አትገኝም ያለበት ን ምስል የያዘ ነው!


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በጡፋን አቅሳ ሸሂድ ከሆኑት ወንድሞች መሃል በጥዑም ነሺዳው የሚታወቀው ሙነሺድ ሃምዛ አቡ ቀይነስ ይገኝበታል !




ወራሪዋ ለቀሳም በመጀመሪያው ዙር በነበረው የእስረኛ ልውውጥ ላይ ቀሳም ያሳየችውን ትእይንት በድጋሜ እንዳላይ ብትልም 😛 ሁለተኛው ቀን ደረሰ 💥 ቀሳም በልዩ ትእይንት በሺዎች ጀግና ወታደሮች እልል ባለ ፕሮግራም የአሸናፊነት ባንዲራውን በማውለብለብ ለወራሪዋ 📌 መልእክትዋን በሚገባ አስተላልፋለች!


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram

20 last posts shown.