ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:
፩
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን በእንተ ልደቱ ለእግዚእነ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ብፁዕ የሚሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ስለ መወለዱ የተናገረው ድርሳን ይህ ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ በሁላችን ላይ ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ዛሬ በፍጥረት ሁሉ ዘንድ ስለሆነው ስለዚህ ምሥጢር ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ዛሬ ሰማያዊው አምላክ በሥልጣኑ ክብር ተገለጠ፡፡ እነሆ ዛሬ እረኞች ማወቅ የማይቻለውን ምሥጢር ሲናገሩ እሰማቸዋለሁ፡፡ የሰው ልጅ ጥበብ ሊረዳው አይችልምና፡፡
ዛሬ ይህቺ ምሥጢር የማትታወቅ ሕፀፅ ያለባት አይደለችም፤ በታላቅ ኃይል የተገለጠች ሰማያዊ ክብር ናት እንጂ፡፡ ዛሬ መላእክት ያመሰግናሉ፤ የመላእክት አለቆችም ይዘምራሉ፤ ኃይላትም እልል ይላሉ፤ ሥልጣናትም ያመሰግናሉ፤ ኪሩቤልም ይቀድሳሉ፤ ሱራፌልም ይባርካሉ፤ እረኞች የምሥራቹን ይናገራሉ፤ ሁሉም ያመልካሉ ይሰግዳሉም፡፡
ዛሬ መላእክት ስለምን በፍጥነት ይሮጣሉ? ሰማያዊውን አምላክ በምድር ላይ አይተዋልና፡፡ የሰው ልጅም ወደ ሰማያዊ ክብሩ ተመልሷልና፡፡ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ልዑሉ ዝቅ ዝቅ አለ፤ ወደ ምድርም ወረደ፤ ትሑቱም ከፍ ከፍ አለ፤ ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡
ዛሬ ቤተ ልሔም ሰማይን መሰለች፡፡ ስለ ከዋክብት ፈንታ መላእክት እያመሰገኑ በውስጧ ታይተዋልና፤ ስለሚጠልቀው ፀሐይ ፈንታም ብርሃኑ የማይጠፋ የእውነት ፀሐይ ከእርሷ ወጥቷልና። ለፍጥረት ሁሉ የሚያበራ የእውነት ፀሐይን ስለ ወሰነችው፡፡ ስለ ቅድስት ድንግል እንናገር ዘንድ ቃል ይደክማል፤ ንግግርም መግለጥ ይሳነዋል፡፡ የሆነውን አልተረዳሁም፤ የተፈጠሩትንም አላወቅሁም። ነገር ግን አምላክ በፈቀደ ጊዜ ሰው ሆነ፡፡ ሰው ሁኖም የእጁን ሥራዎች አዳነን፡፡
ዛሬ ሁሉ ወደ እርሱ ፍቅር ፈጥኖ ይመጣል፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረ ሰማያዊ አምላክ ያለ መለወጥ ሰው ሆነ፡፡ ቀዳማዊ ቃል ያለ መለወጥና ያለመለየት ሥጋን ተዋሐደ፡፡ ዛሬ ከፍጥረት ሁሉ ሥውር የሆነ ድንቅ ምሥጢርን ዐየሁ፡፡
ዛሬ መላእክት በፍጹም ደስታ አመሰገኑ፡፡ እንዲህ እያሉ “እንዴት ሰማያዊ ንጉሥ ወደ ምድር ወረደ?” ከእርሱ ጋራም መላእክትን፣ ኃይላትን፣ መናብርትን፣ሥልጣናትን አላስከተለም፤ ይዞ አልወረደም፡፡ ማንም ሊሄድባት በማይችል ድንቅ መንገድ መጣ እንጂ፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያምም በሥጋ ተወለደ፡፡
በተገለጠም ጊዜ መላእክት ሰው መሆኑን አላወቁም፡፡ ሰው ከሆነም በኋላ ከመለኮቱ ክብር አልተለወጠም፡፡ የምድር ነገሥታት የኃይላት ጌታ ለሆነው ሰማያዊ ንጉሥ ሊሰግዱለት መጡ እንጂ፡፡ ሴቶች ኀዘናቸውን ወደ ፍጹም ደስታ ይለውጥ ዘንድ ከድንግል ወደተወለደው መጡ፡፡ ዛሬ ሴቶች ድንቅ ምሥጢርን ያዩ ዘንድ ወደ ተወለደው ሕፃን መጡ። ቀዳማዊ አዳምን ያድነው ከኃጢአት ቍስልም ይፈውሰው ዘንድ አምላክ ዛሬ በሥጋ ተገለጠ፡፡
ይቀጥላል......
(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 33-53)
፪
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን በእንተ ልደቱ ለእግዚእነ
ዛሬ እረኞች በፍጹም ደስታ ስለ በጎቹ ነፍሱን ወደ ሰጠው ቸር እረኛ መጡ፡፡ ዛሬ ካህናት የመልከ ጼዴቅ ምሳሌ ወደ ሆነው ወደ ታላቁ ሊቀ ካህናት መጡ፡፡ ዛሬ ከኃጢአት ቀንበር በታች የነበሩ ባሮችን ነፃ ያወጣቸው ዘንድ በባርያ መልክ የተገለጠውን አምላክ ያመልኩት ዘንድ መጡ፡፡ ዛሬ ዓሣ አሥጋሪዎች ሰዎችን ከአምልኮተ ጣዖትና ከዲያብሎስ አገዛዝ ነፃ ያወጧቸው ዘንድ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ ሊማሩ ወደ ዓሣ አሥጋሪዎች አለቃ መጡ፡፡
ዛሬ ዘማ ሴቶች ዘማ ሴት የከበረ እግሩን ወደሳመችው፣ በዕንባዋ ወደ አጠበችው፣ በፀጉሯም ወደ ወለወለችው መጡ፡፡ ዛሬ ኃጥአን የዓለምን ኃጢአት ወደሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ መጡ፡፡ እንግዲህ ምን እላለሁ!? በፍጹም ደስታና በመንፈስ ቅዱስ ለኃይላት ጌታ ዛሬ በዓልን አደርግ ዘንድ ተገቢ ነውና፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ወዳጆች በዓልን ያድርጉ፡፡ እኔም ስለዚህ በፍጹም ደስታ ወደ አምላኬና መድኃኒቴ ወደ ረዳቴም እጆቼን እጸፋለሁ፡፡ በሰማይ ምስጋና ይሁን በምድርም ሰውን ለወደደ እያልሁ ከመላእክት ጋራ ለእርሱ ምስጋናን አቀርባለሁ፡፡
ዛሬ ወልድ በሚደነቅ ጥበቡ ከቅድስት ድንግል ተወለደ፡፡ ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ ቀዳማዊ አብ እንደ ወደደ፣ መንፈስ ቅዱስም በባለ ጠግነቱ ብዛት እንደ መረጣት በእኛ ባሕርይ ከቅድስት ድንግል ሰው ሆነ፡፡ ሰማያዊት ልደቱ ድብቅ ናት፡፡ ምድራዊ ልደቱ ግን ዛሬ ተገለጠች፡፡ ሰማያዊት ልደቱ ከአንዱ የተገኘች አንዲት ናት፡፡
ምድራዊት ልደቱም ከአባቱ ባሕርያዊ ክብር ሳይለይ ከድንግል የተገኘች አንዲት ናት፡፡ “መድኃኒት ከጽዮን ይመጣል ኃጢአትን ከያዕቆብ፣ አመፃንም ከእስራኤል ያስወግዳል” ብሎ መጽሐፍ ምስክር እንደሆነ፡፡ እነሆ ዛሬ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች አነቃቸዋለሁ፤ አስረዳቸዋለሁም፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢርም እተረጕምላቸዋለሁ፡፡ ጽዮን የተባለች ቅድስት ድንግል ናት፡፡ መድኅን የተባለውም ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ ከአብ የተወለደው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
በፊቱ ከሚቆሙ መላእክት የተሠወረውን ይህንን ድንቅ ምሥጢር ባሰብሁ ጊዜ ምን እላለሁ!? ምንስ እናገራለሁ! የሰው ልጆችን ያድናቸው ዘንድ ከዓለም አስቀድሞ የነበረ አካላዊ ቃል የቅድስት ድንግልን ሥጋዋን ተዋሐደ፡፡ ድንግል ማርያም በእውነት ቅድስትና ንጽሕት ናትና፡፡ ከመልአኩ ገብርኤል ከሰማቸው ቃል በቀር በእርሷ ላይ ስለሆነው ነገር ምንም ምን አላወቀችም፡፡
መልአኩ ገብርኤልንም “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” ብላ መለሰችለት፡፡ መልአኩም “መንፈስ ቅዱስ ወደ አንቺ ይመጣል፤ የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል፤ ይህ የሚወለደውም ቅዱስ ልዩ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል፤” አላት፡፡
ዛሬ ስለተገለጠው ስለዚህ ድንቅ ምሥጢርና ለድኅነታችን ስለ ሆነው መንፈሳዊ በዓል ምን እላለሁ!? ምንስ እናገራለሁ!? ዛሬ የእሥረኞች ማሠሪያቸው ተፈታ፤ ዛሬ ሰማያውያን ደስ ተሰኙ፤ ዛሬ መላእክት ከሰው ልጅ ጋራ ተደሰቱ፤ ዛሬ የረከሱ አጋንንት አፈሩ፤ ዛሬ ተድላ ደስታ ያለበት ገነት ተከፈተ፤ ዛሬ ሰይጣን ወደ ጥልቁ ተወረወረ፤ ዛሬ የብረቱ መዝጊያ ተሰበረ፡፡