Forward from: Nejashi Printing Press
የሸዕባን ዝግጅት
****
አነስ ረዐ እንዳሉት " የሸዕባን ወር ሲገባ ሙስሊሞች ቁርአን ላይ ተደፍተው ያነባሉ። ደካሞችና ድሆች በረመዷን ፆም ላይ ይበረቱ ዘንድ ዘካቸውን ያወጣሉ።"
ኢማም ኢብኑ ረጀብ እንዳሉት ሸዕባን የረመዷን መግቢያ ነው። ፆምም ሆነ ቁርአን መቅራት በረመዷን ውስጥ የሚወደዱ ተግባራት ሁሉ በሱ ውስጥም ይወደዳሉ። ነፍስ የረመዷን ዒባዳ እንዳይከብዳት ከወዲሁ መዘጋጀት ማለማመድና ማለስለስ ያስፈልጋል ።
የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ.
" ሸዕባን ብዙ ሰዎች የሚዘናጉበት በረጀብ እና በረመዷን መካከል የሚገኝ ወር ነው። በዚህ ወር ውስጥ ሥራዎች ወደ ዓለማት ጌታ ይቀርባሉ ። ፆመኛ ሆኜ ሥራዬ እንዲቀርብ እወዳለሁ ።"
ዓኢሻ (ረ.ዐ.)
" ከሸዕባን የበለጠ የትኛውንም ወር በብዛት ሲፆሙ አይቼ አላውቅም ።" ብላለች።
ደጋጎች ሸዕባንን የቁርአን ወዳጆች ወር ይሉ ነበር። በብዛትም ያነቡታል።
አላህ ሆይ ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን ደርሰው ፆመው፣ በፆማቸውም ተቀባይነት ከሚያገኙት አድርገን።
https://t.me/NejashiPP