አስደሳች ዜና ለተማሪዎች
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስኮላርሺፕ
***
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የመጀመርያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ስርዓት ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል። በቅርቡም ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና እንደሚሰጥና ብቃትን፣ ብዝሃነትንና ፍትሐዊነትን ማዕከል አድርጎ እንደሚቀበል ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን በውድድር ነፃ የትምህርት እድል ከዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎት ጋር እንደሚሰጥ ሲገልጽ አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቃትና ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች መዳረሻ ለመሆን ያለውን ቁርጠኝነት ይገልጻል።