Natinael Mekonnen


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Shock content


ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
I blog about marketing and sales
Buy ads: https://telega.io/c/NatinaelMekonnen21

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጸመ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፦በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጽሟል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ስራ አስፈጻሚ አመራሮች አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በተገኙበት የቦንድ ግዢውን አስረክበዋል።

ኮሚዩኒቲው ከዚህ ቀደም በሀገራችን ለሚደረጉ የተለያዩ የልማት ጥሪዎች እና ማህበራዊ ድጋፎች ህዝቡን በማስተባበር ትልቅ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ዘንድሮም የ2 ነጥብ7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ የቦንድ ግዥ ለአምባሳደሩ በማስረከብ ድጋፋቸውን መግለጻቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመለክታል።


ኢትዮጵያ ስንዴን በገፍ አምርታ እነ WFP ሳይቀር ውጤቱን አድንቀው ሲያወሩ ያኔ የኛዎቹ ባንዳዎች ነጠላ አዘቅዝቀው በየሚዲያው ሲያጣጥሉ ነበር። ዛሬ ድሮን ማምረት ስንጀምር "ለምን ስንዴ አላመረትንም?" እያሉ እያለቀሱ ነው። በተነገረ ዜና ሁሉ ማልቀስ ምን የሚሉት ፖለቲካ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።

የአንድ ሐገር ጥንካሬ በብዙ መንገድ ይለካል። ከነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ ኢኮኖሚያዊ፥ ወታደራዊ፥ ፖለቲካዊ ጥንካሬዎች ናቸው። Military strength የሌላት ሐገር በርና ጥበቃ የሌለው የጌጣጌጥ ሱቅ ማለት ነች። ዱርየውም ቀማኛውም እንደጠላ ቤት ይረግጣታል። ወታደራዊ ጥንካሬ ደግሞ Advanced Technology መጠቀምና ማምረትን ያካትታል። ይሄን ደግሞ ማሳካት ችለናል።

አንድ የሮማ ፀሀፊ De Re Militari በሚል መፅሀፉ "ሰላም ከፈለግክ ለጦርነት ተዘጋጅ" ይላል። በጦር ሀይል ራስህን ምታጠናክረው ጦርነት ለማድረግ ስለምትፈልግ አይደለም። ጠላቶችህ ካንተ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባትን ከአጀንዳቸው ላይ እንዲሰርዙም ጭምር ነው። ምክኒያቱም እንደኢትዮጵያ ያለችን መቶ ሰላሳ ሚሊየን ህዝብና ድሮን የሚያመርት መከላከያ ሰራዊት ያላትን ሐገር መግጠም ከባድ consequence አለውና!!!!

ለማንኛውም ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ በመከራ ያገኘችውን ዶላር ተሸክማ ተተኳሽ ለመግዛት በየሐገሩ አትንከራተትም። በራሳችን እውቀትና አቅም ተተኳሾችን አምርተን በአጭር ግዜ በሚሊዮን ዶላሮች ሸጠናል። ይህ ተአምር ነው። በዚህ አልበቃንም ሚሊየን ዶላሮች የሚወጣበትን ድሮን እዚችው ሐገራችን ላይ አምርተን ራሳችንን አስታጥቀናል። ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ድሮን የታጠቀች ብቻ ሳትሆን ድሮን አምርታ ለአለም የምትሸጥ ሐገር ነች። ኢትዮጵያን ከነችግሯ የምትወዱ ውድ ልጆቿ እንኳን ደስ አላችሁ። አልቃሾችና ባንዳዎች እግዜር ፅናቱን ይስጣችሁ


ሰበር ዜና ‼️

ጆን መዲድ እና ወድምቤተይ የተባሉት ታጣቂ አመራሮች አዲግራት አከባቢ የአስተዳደሩን ማህተምና ቢሮ በኃይል በመንጠቅ ለእነ ደብረፅዮንና መንጀሪኖ ቡድን ለማስረከብ ቀደም ብሎ ሶስት ጊዜ ሞክረው በህዝቡ በአጠቃላይና በተለይ በወጣቱ እምቢታ የተገቱ ሲሆን በዛሬው እለትም ህዝቡን በማሸበር ተኩስና ድብደባ እየፈጸመ ነው።

በአሁን ሰአት በተነሳው ችግር በርካታ ወጣቶችን በመደብደብና ወጣቱ ላይ ተኩስ በመክፈት አስተዳደሩን እየቀሙ ነው። ቀጣዩ ጉዞ በመቀሌ ዙሪያ ለመድገምና የድምፀወያኔ ቢሮ ለመቆጣጠር ነው። ቀደም ሲል በደቡባዊ ትግራይ ተመሳሳይ ሙከራ ተደርጎ በህዝብ ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። ይኸው ጉዳይ በዚሁ የሚቀጥል በመሆኑ አስተዳደሩ መፍረሱና ወደ ሙሉ ግጭት መሸጋገሩ የማይቀር ነው።


ሰበር ከመቀሌ‼️

በእነ ደብረፂዮንና መንጀሪኖ የሚመራ ታጣቂ መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ በዛሬ ቀን የከቲት 30 ዝግጅቱን እንደጨረሰ መረጃዎች ያመላክታሉ። ከዛሬ ሌሊት 6:00 ሰዐት ገደማ ጀምሮ እስከ ጠዋት መቀሌ ከተማ ጨምሮ ምስራቃዊ ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች ጨምሮ በሀይል ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

ይህ የመፈንቅለ መንግስት ኦፕሬሽን የእነ ደብረፂዮንና መንጀሪኖ ቡድን አገልጋዮች ከሆኑት #ጆን_መዲድ፣ #ማሾ_በየነ፣ #ምግበይ እና #ወዲ_እምበይተይ የተባሉት ጥቂት አዛዦች ታጣቂዎች እያሰማሩ መሆናቸን ታውቋል።ይህ የፕሪቶሪያ ስምምነት በማፍረስ የጦርነት አዋጅ እየተጀመረ ይገኛል።የትግራይ ወጣቶች ለዚህ የክፋት ሴራ ህገወጥ ቡድን በመኮነን ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ትግል እንደጀመሩ ይታወቃል።


"ከሞት በላይ እንሙት፤ደማችን ሺህ ጊዜ ይፍሰስ" 🇪🇹🇪🇹

የአበው የአርበኝነት ቅርስ ፤ የነፃነት ገድል ፋና፣
ወደ ትውልድ ተሸጋግሮ ፤ ወርሶት ፀንቷል እንደገና።
ምድራዊ ፈተናው በዝቶ ፤ ዙሪያው ቢነድ ቢጎመራ፣
ጥሰነው እናልፋዋለን ፤ የማይሞት ታሪክ ልንሰራ።

ህዝብ ነው ሃያል ክንዳችን ፤
ሰላም ልማት ነው ቋንቋችን፣
የመፈቃቀድ አንድነት ፤ እኩልነት ነው ዜማችን፣
የማንጨበጥ ነበልባል ፤ እሳት ነን ለጠላታችን፣
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል ፤ ብረት ያቀልጣል ክንዳችን።

ኢትዮጵያ በኛ ደም ደምቃ ፤ ባፅማችን ፍላፅ ተማግራ፣
እንደታፈረች እንድትኖር ፤ ከዘመን ዘመን ተከብራ።
ከመሞት በላይ እንሙት ፤ ደማችን ሺ ግዜ ይፍሰስ፣
አየር አፈሯ ይባረክ ፤ ምንግዜም ስሟ ይታደስ።"

ክብር ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ የገጠሟትን የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎች በአንፀባራቂ ድል እንድትሻገር ለሚዋደቁ ጀግኖች ልጆቿ ይሁን‼️🙏🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ክብር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ‼️


Made in Ethiopia ‼️

የSkyWin Aeronautics Industry ምርቃት ለአገሪቱ ትልቅ ምዕራፍ ሲሆን ይህም በሀገር ውስጥ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ እየታዩ ያሉትን እመርታ ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወታደራዊ አቅምን ከማስፋፋት ጀርባ ባለው ሰላማዊ ዓላማ ላይ አጽንኦት መስጠቱ አንድ ወሳኝ ትረካ አጉልቶ ያሳያል፡ አላማው ግጭት መቀስቀስ ሳይሆን መረጋጋትንና ደህንነትን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የመከላከያ ዘዴ መገንባት ነው።

በተለይም ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ለእንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂዎች በውጭ ምንጮች ላይ ትተማመናለች የሚለውን ግምት ውስጥ በማስገባት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የመንደፍ እና የማምረት ችሎታው አስደናቂ ስኬት ነው። ይህ እድገት እራስን መቻልን ከማጎልበት ባለፈ ብሄራዊ ኩራት እና የቴክኖሎጂ እድገትን ያሳድጋል። በምርምር ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ስማርት ሴንሰር ቴክኖሎጂዎችን በአገር ውስጥ በማምረት መንግስት እራሱን በኤሮኖቲክስ ዘርፍ መሪ አድርጎ ለግጭት መከላከል ሰፋ ያለ አላማ የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል።

በተለይም ውጥረት በሚፈጠርባቸው ክልሎች ሰላምና መረጋጋት ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ የመከላከል አቅሟን በማጠናከር ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን በመከላከል ለውይይት እና ለትብብር ምቹ ሁኔታ መፍጠር ትችላለች። አለም በዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ ሀገራት ሰላምን በመከተል ሉዓላዊነታቸውን ለመጠበቅ መላመድ አለባቸው።

ውጥኑ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለአካባቢው የሰው ኃይል የክህሎት ዕድገት ማበረታቻ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። በዚህ መስክ ባለሙያዎችን ማሳተፍ ፈጠራን ማነሳሳት እና ለተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተጨማሪ እድገቶች መንገድን ሊከፍት ይችላል። በመጨረሻም የስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ በተሳካ ሁኔታ መመስረቱ ለሌሎች የቀጠናው ሀገራት አርአያ ሊሆን ይችላል፣ ይህም ኃላፊነት ያለበት የቴክኖሎጂ እድገት በማስመዝገብ ለደህንነት እና ለሰላም የጋራ ቁርጠኝነትን ያሳድጋል።


ሰበር ዜና‼️ “ዛሬ የስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪን መርቀናል። ከጥቂት አመታት በፊት በሀገር ውስጥ ድሮን ስለማምረት ማሰብ የማይታሰብ ነበር። ብዙ አይነት ችሎታ ያላቸው ድሮኖችን በራሳችን ባለሞያዎች ዲዛይን አድርጎ የማምረት አቅም ትልቅ የታሪክ እጥፋት ነው። ይኽን እድገት ለማዝለቅ ቀጣይነት ባለው የምርምር ሥራ ላይ፣ ገበያ በማስፋት ተግባር ላይ እና በሀገር ውስጥ የስማርት ሴንሰር ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ላይ መስራት ይገባናል።

እንደዚህ እና እንደሆሚቾ የተተኳሽ ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ ያሉትን አቅሞቻችንን የምናሳድገው ግጭትን ለማቀጣጠል አይደለም። ግጭትን ለማስቀረት እንጂ።ግጭትን በሚፈልጉ ተዋንያን ፊት ግጭትን ለማስቀረት የሚችል አቅም በመፍጠር ሰላም እና መረጋጋትን ለማፅናት ነው ፍላጎታችን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)


ገና ያልታየ ተዓምር አብረን እናያለን:: ኢትዮጵያ በልጆቿ ትኩሯ

በኢትዮጵያውያን እጆች የተሰሩ ባለ ዘጠኝ ተተኳሽ BM ሮኬት


ገና ያልታየ ተዓምር አብረን እናያለን:: ኢትዮጵያ በልጆቿ ትኩሯ

በኢትዮጵያውያን እጆች የተሰሩ ሰው አልባ የሰማይ በራሪዎች ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ይመረቃሉ።

የባዳ ተለላኪ ባንዳዎች “ድሮን ምን ይሰራል?” የሚል ጽሁፍ እያዘጋጃችሁ ጠብቁን


የአማራ ህዝብ በታሪኩ ሊያውም በገዛ ልጆቹ እንዲህ አይነት ግፍ ደርሶበት አያውቅም ወደፊትም አይደርስበትም:: ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ገዳይ የሆነው ተጠርጣሪ በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ክትትል በሕግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ከዚህ በፊት መግለጫ መሰጠቱ ይታወቃል።

ተጠርጣሪዉ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ፍርድ ቤት ቀርቦ የዕምነት ቃሉን ሰጥቷል።


ልዩ መረጃ‼️

የትግራይ ገቢዎች ዳይሬክተር አቶ ክብሮም ፍስሀየ ከሀገር ለመኮብለል ሲሉ በኢሚግሬሽን ድህንነቶች እንዲመለሱ ተደርገዋል። አቶ ክብሮም ትግራይ ውስጥ ባላቸው ስልጣን ተጠቅመው በተለይም ህገወጥ ጉባኤ ካደረገው ቡድን ጋር በመቀናጀት ከብዙ ባለሀብቶች ግብር ይነቀስባችሃል በማለት ገንዘብ ተቀብለው ብዙ ወንጀሎች መፈፀማቸው ይታወቃል።

አቶ ከብሮም ከትግራይ ፋይናንስ ሐላፊ የሆነችው ዶከተር ምህረት ጋር በመቀናጀት የመንግስት ሀብት መዝብረው ወደ ህገወጥ ቡድኑ የየከቲት በአል ለማክበር መስጠቻውን መረጃዎች አሉ። ዶክተር ምህረት በወንጀል ታስረው ከቅርብ ጊዜ በፊት ምክንያቱ ባልታወቀ ተፈትተው ድጋሚ ስልጣን መያዛቸው ይታወቃል። ዶ/ር ምህረት የተፈቱት በ #ታደሰ_ወረደ አማካኝነት መሆኑን ይታወቃል።


ልዩ መረጃ መቀሌ‼️ ጀነራል ታደሰ ወረደ በጊዚያዊ የትግራይ መስተዳደር የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።ይህ ማስጠንቀቂያ ዋና ይዘቱ መንግስት ለማፍረስ እየሰሩ ያሉት ጥቂት አዛዦች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የሚያስጠነቅቅ ነው።

ታደሰ ወረደ ሕገ ወጥ ጉባኤ ባደረገው ቡድን እና መንግስት ለማፍረስ እየሰራ ያለው ስራ እንዲያስቆሙ የመጨረሻ ትእዛዝ ነው የተሰጣቸው።

በትግራይ ያለው መንግስትን በማፍረስ የፕሪቶሪያ ውል እንዲጣስና ህዝቡ ወደ ጦርነት ለማስገባት ጉባኤ ያደረገው ቡድን ከጥቂት በጥቅም የተሳሰሩ አዛዦች ሴራ እንዳለ ይታወቃል።ሆኖም ይህ አካሄድ በተለይም ጀነራል ታደሰ የማስቆመው ከሆነ ተጠያቂ እንደሚሆን እና መንግስት በማፍረስ ሀላፊነት እንደሚወስድ ደብዳቤ ደርሶታል።


በተተኳሽ እራሱን ያልቻለ ሃገር ሃገር አይደለም:: ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን በጎበኙበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ


ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ ዐቅም አሳድጋለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎም ወደውጭ የመላክ አቅም ማሳደጓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካን በጎበኙበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ሀገር ራስን የመቻል ጉዞዋን በማጠናከር ስሉጥ የሆነ የትውልድ ቅብብሎሽ ማረጋገጥ እንደሚገባት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ብታደርግም፤ እስከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ድረስ ከውጭ በማስገባት ላይ ተመስርታ መቆየቷን አንስተዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ አቅም አሳድጋለች ብለዋል ።

ይህ ርምጃ በምሉዕነት የተገነባ እና በሚገባ የታጠቀ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከማረጋገጥ አንፃር አበረታች ሥራ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከመከላከያ ግብዓቶች ባሻገር ሀገር የራሷን ምግብ ፣ መድኃኒት እና አልባሳት በበቂ ሁኔታ በማምረት እውነተኛ በራስ ምርት መተማመንን ማረጋገጥ እንደሚገባትም ነው ያስገነዘቡት፡፡




የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአልሸባብ ወታደራዊ ይዞታዎችን ደበደበ


እያመመው እያመመው መጣ ‼️ሶማሊያ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለጎረቤቷ ኢትዮጵያ የወደብ መዳረሻ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር እየተነጋገረች መኾኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ሞሐመድ ኦማር መናገራቸው ተገለጸ።

እንደ ሃገር እንደ ጥሩ ጎረቤት ኢትዮጵያ የሌላትና ከሶማሊያ የምትፈልግው ሶማሊያ የሌላትና ከኢትዮጵያ የምትፈልገው ብዙ ነገሮች አሉ:: በሰጥቶ መቀበል መርህ አብሮ ማደግ መበልጸግ ነው የኢትዮጵያ መርህ!

ሶማሊያ በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለጎረቤቷ ኢትዮጵያ የወደብ መዳረሻ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር እየተነጋገረች መኾኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ሞሐመድ ኦማር መናገራቸው ተገለጸ።

ሁለቱ ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ አየመከሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒሰተር ዴኤታው እስከ መጪው ሰኔ ወር የስምምነቱን ማዕቀፍ ለማጠናቀቅ እየተነጋገሩ ነው ማለታቸውን ከብሉንበርግ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

“ማዕቀፉ ምን አይነት ወደብ እንደሚሰጥ ውሳኔ ይሰጣል፣ በትክክል የትኛው የህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ እንደሚሻል ምክረ ሀሳብ ያቀርባል እንዲሁም ለወደቡ ግንባታ አጠቃላይ ስለሚያስፈልገው የገንዘብ ወጭ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል” ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አመላክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሞቃዲሹ ማቅናታቸው ይታወቃል፤ የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ሶማሊያ ያመሩት ጠ/ሚ አብይ በሞቃዲሾ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ጋር የፀጥታ ትብብርን በማጠናከር፣ የንግድ አጋርነት በማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የአንካራውን ስምምነት ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን በወቅቱ ከ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ውይይት በማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመመለስ መስማማታቸውን ይታወሳል።


መልካም የአድዋ ድል በዓል!!!💚💛❤

18 last posts shown.