ፈቀደ ይሆን ዘንድ፤ የሚሸጠው አገልግሎት ግልፅና የታወቀ እንዲሁም ከሀራም ነገር የፀዳ መሆኑ መስፈርቶች ናቸው። በዚህኛው የቴሌ ግብይት የሚሸጠው ሀላልና ግልፅ ጥቅም (መንፈዓ) ያለው የስልክ አገልግሎት ነው።
ለምሳሌ፤ ቴሌ የሚሸጠው ባላንስ ወጋው 10 ብር ቢሆን፤ ተጠቃሚው በዱቤ ገዝቶት ከሆነ ባለ 20 ብር ካርድ ሲሞላ 11 ብር ሊቆርጥበት ወይም በደወለ ቁጥር የደቂቃ ሂሳቡ ላይ በመጨመር ጭማሪዋን 1 ብር ከተገልጋይ ሊወስድ ይችላል። ተገልጋዩ ባላንሱን ሲገዛ ወደፊት በሚከፍልበት ግዜ የሚኖረው ጭማሪ የታወቀ እና ከቆይታ ጋር የማይጨምር ስለሆነ የተፈቀደ ነው።
አንድ ሰው ባለ 10 ብር የቴሌ ካርድ ከቴሌ የሽያጭ ቢሮ ሌላ ግዜ እከፍላለው ብሎ በዱቤ 11 ብር ቢገዛ ላይደናግር ይችላል። ሆኖም በተጨባጭ እጁ ላይ ሳይገባ የቴሌ አካውንቱ ላይ 11 ብር ገቢ ሲሆን እንደ ገንዘብ ብድር ያስበውና መደናገር ውስጥ ይገባል።
ወለድ የምንለው በብድር ምክንያት የሚመጣ ቀጥተኛ ጭማሪ ሲሆን ገንዘብን በገንዘብ መሸጥ ነው። ይህ የ 1 ብር ልዩነት የዱቤ ሽያጭ ስለሆነ የተከሰተ ጭማሪ እንጂ የብር "ብድር" ላይ የሚደረግ ጭማሪ ቢሆን ወለድ በመሆኑ የሚፈቀድ አይሆንም።
ለብዙ ሰዎች መደናገር ምክንያቱ የቴሌኮም ድርጅቶች ይህ አይነቱን አገልግሎት ክሬዲት ወይም የብር ብድር ብለው መሰየማቸው ነው። በተለምዶ ሰዎች ዘንድ ብር ከፍሎ አገልግሎት ማግኘት እንደ ግዢ አለመታሰቡም ሌላኛው ምክንያት ነው።
ወላሁ አዕለም
https://telegram.me/nesihablog