" ምን እየተደረገ እንደሆነ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ወሰደብኝ፡፡ ስለመደፈር ሲወራ እሰማለሁ፡፡ አንድ ቀን እኔ ላይ እንደሚደርስ አላስብም ነበር፡፡ ስዞር አፌን ለአፍታ ያክል ለቀቀኝ፡፡ ደግሜ ጮህኩ፡፡ ምን ነበረበት አቢ ቡና ቢጠጣ? ግራ እጁ በትከሻዬ ዞሮ መልሶ አፈነኝ፡፡ በአፍንጫዬ ከላይ ከላይ እተነፍሳለሁ። በቀኝ እጁ ሁለት እጆቼን አስሯል፡፡ በሰውነቱ ከግድግዳው ጋር አጣብቆ ያዘኝ። ሊያጠቃኝ የተዘጋጀ ደም የወጠረው ገላው ቂጤ ላይ ይሰማኛል፡፡ ምን ነበረበት ደስታ ዘመዶቿ ጋ በጠዋት ደርሳ ብትመጣስ? አፉ አንገቴ ላይ ነው። ያለከልካል። የዚህ ልጅ ድፍረቱ ሁለት ነው፡፡ ከግድግዳው ጋር በሰውነቱ አጣብቆ ያዘኝ፡፡ ደፍሮ ቤቴ ይገባል? ግራ እጁ አሁንም አፌን አፍኗል፡፡ ደፍሮስ እንዲህ ያደርገኛል? አየር እያጠረኝ ነው፡፡ በፈጠጠ ዐይኔ በጉንጬ የተደገፍኩት አረንጓዴ የግድግዳ ላይ አፍጥጫለሁ፡፡ ጠረጴዛው ላይ የእናቴ ፎቶ ይታየኛል፡፡ አባዬ ትዝ አለኝ፡፡ ላቤ ችፍ ብሏል፡፡ ልቤ ይደልቃል፡፡ አማራጭ አጥቼ እፈራገጣለሁ፡፡ ቀኝ እጁ እጆቼን ለቆ ወደ ደረቴ መጣ፡፡ የቀኝ ጡቴን በኃይል ጨበጠ፡፡ ሊፈርጥ ሁሉ መሰለኝ፡፡ የታፈነ የሕመም ድምፅ አወጣሁ። "
" መሐረቤን ያያችሁ "
የአጫጭር ትረካዎች ስብስብ
ሙሉጌታ አለባቸው
ሁለተኛ ዕትም
የአዳም ረታ ዓይነት የአጻጻፍ ስልት ለማንበብ የናፈቃችሁ ተደራሲያን ይኸው አዳም ራሱ አድንቆ የመሰከረለትን መጽሐፍ አንብቡ ::
ጃዕፈር መጻሕፍት
ፎቶ :- Gebrela Shewakena
" መሐረቤን ያያችሁ "
የአጫጭር ትረካዎች ስብስብ
ሙሉጌታ አለባቸው
ሁለተኛ ዕትም
የአዳም ረታ ዓይነት የአጻጻፍ ስልት ለማንበብ የናፈቃችሁ ተደራሲያን ይኸው አዳም ራሱ አድንቆ የመሰከረለትን መጽሐፍ አንብቡ ::
ጃዕፈር መጻሕፍት
ፎቶ :- Gebrela Shewakena