እኔ #ኢትዮጵያዊያንን_አላምንም!
🗣እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። #በጭንብል_ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም #ሰምና_ወርቅ ነው ...
🗣በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት #መለኪያ የለንም፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን #የግል_ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው #ተንኮል_የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው።
ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው #መርህ_አንድ ብቻ ነው፤ #የግል_ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው...
🗣ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ #ህሊናችንን_ቅንጣት_ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል?
🗣ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን፤ የስጋ ዘመድን አይለይም #ቅናት_ባህላችን ነው።
🗣ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም?
በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው። በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው።
በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ፣ ከምቀኝነት፣ ከተንኮል፣ ከቅናት፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!
🗣 #በዓሉ_ግርማ_የቀይ_ኮከብ ጥሪ፥ ገፅ 234