ጥር 30 2017
ኤች አይቪ ኤድስን መከላከል ላይ የሚከወኑ ስራዎች እየተቀዛቀዙ ነው ተባለ፡፡
ሀገራዊ የኤች አይ ቪ መከላከል ስራውም ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ እየተሰራበት እንደሆነ ይነገራል በተለይ በወጣቶች የኤች አይ ቪ መከላከል ላይ ግን የሚከወኑ ስራዎች ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አለመሆናቸው ተነግሯል፡፡
በወጣቶች ላይ አተኩሮ በተለያዩ ክልሎች ላይ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ላይ የሚሰራው ጣምራ ለማህበራዊ ልማት የተባለው ድርጅት እንደሚናገረው ከጥቂት አመታት ወዲህ ኤች አይ ቪን መከላከል ላይ የሚከወኑ ስራዎች ከወጣቶች ይልቅ ለቫይረሱ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ ሌሎች ዜጎች ላይ አተኩሯል ሲሉ የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ይርጋለም ተናግረዋል።
ወጣቶችም ከፍተኛ ተጋላጭ በመሆናቸው እነሱም ላይ ትኩረት ያደረገ ስራ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
ጣምራ ለማህበራዊ የልማት ድርጅት የተቋቋመውም የወጣቶች የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች ላይ በመሆኑ አሁንም በሚያገኛቸው ድጋፎች የወጣቶች የኤች አይ ቪን መከላከል ስራዎች ላይ ይሳተፋል ነገር ግን በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለው የኤች አይ ቪ መከላከል ስራዎች ወጣቶችን የተመለከቱት ቀንሰዋል ብለዋል።
ክልሎች በተለይም ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ ማህበሩ አብረውት ከሚሰሩ በአምስት ክልሎች ካሉ አጋሮቹ ጋር በወጣቶች የኤች አይ ቪ መከላከል ላይ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ለኤች አይ ቪ ተጋላጭናቸው ከሚባሉት ውስጥ የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች በወሲብ ንግድ ላይ ተሰማሩ ሴቶችና ሌሎችም ይጠቀሳሉ በነዚህ ዜጎች ላይ አተኩሮ መሰራቱ መልካም ቢሆንም ነገር ግን አሁንም በተለያዩ አጋጣሚዎች ለኤች አይቪ ኤድስ እጅግ ተገላጭ ወጣቶች ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 7 ሺህ ያህል አዳዲስ ሰዎች በኤች አይቪ የሚያዙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ በአፍላ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው በሀገሪቱ እድሜያቸው ከ15 በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል የኤች አይ ቪ ስርጭት ምጣኔውም 0.87 በመቶ መሆኑን የኢትዮጵያ ብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተገባደደው በጎርጎሮሳዊው 2024 ያካሄደው ሀገራዊ ጥናት ያሳያል፡፡
ምንጭ ፦ SHEGER FM
ምህረት ስዩም
@PharmacyRxplus