በኢትዮጵያ የ5 ሺ የመንግሥት የጤና ሠራተኞች ውል መቋረጡን በተባበሩት መንግሥታት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሥርጭት መከላከያ ፕሮግራም (UNAIDS) ምክትል ኃላፊ ክሪስቲን ስቴግሊንግ አረጋገጡ።
ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠዉን የውጪ ዕርዳታ ስታቋርጥ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሥርጭትን ለመግታት የተዘረጉ መርሐ ግብሮች እንዳይካተቱ የተላለፈ ውሳኔ ቢኖርም “ከፍተኛ ግራ መጋባት” መፍጠሩን ኃላፊዋ ተናግረዋል።
መድሐኒት ለማኅበረሰብ የማጓጓዝ ሥራ እና የማኅበረሰብ ጤና አገልግሎት ሠራተኞች የአሜሪካ መንግሥት ባስተላለፈው ውሳኔ ተጽዕኖ ውስጥ የወደቁ መሆናቸውን ኃላፊዋ ዛሬ አርብ በጄኔቫ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።
የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሐገራቸዉ ለዉጪ የምትሰጠዉን በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ዕርዳታ ለ90 ቀናት እንዲቆም ያዘዙት ወደ ዋይት ሐውስ እንደተመለሱ ነው። ከትራምፕ ትዕዛዝ በኋላ የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ትዕዛዙ ፔፕፋር (PEPFAR) ተብሎ በሚጠራው የኤድስ ሥርጭትን ለመከላከል የተበጀ የድጋፍ መርሐ-ግብር እንዳያካትት የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፎ ነበር።
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን እርምጃ በበጎ እንደሚመለከቱ የጠቀሱት ክሪስቲን ስቴግሊንግ ይሁንና ሁኔታው አሁንም በውዥንብር የተሞላ እንደሆነ ተናግረዋል።
(DW)
@PharmacyRxplus