ሳይኮሎጂ | Psychology


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Psychology


በየቀኑ ስለ Psychology የሚለቀቅበት ቻናል ነው!
Owner : @BirukXL
Cross Promotion : @AmbaSupport

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Psychology
Statistics
Posts filter


🚀 ቴሌግራም ላይ ሊያመልጣችሁ የማይገቡ ቻናሎች:

1️⃣@PsychologyCentral✅ : የተለያዩ ሳይኮሎጂ መፅሐፎች እና ፅሑፎች የሚለቀቁበት ምርጥ ቻናል

2️⃣@Yemesahft_Alem✅ : ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ያሉ መፅሐፎች በPDF የሚለቀቁበት

3️⃣@PandoraPDF✅ : መፅሐፍት በPDF ብቻ የሚለቀቁበት ቻናል

4⃣@AmbaBooks☑️: የትኛውን መጽሐፍ ማንበብ ይፈልጋሉ? ልቦለድ ፣ ታሪክ ፣ሳይኮሎጂ ፣ቢዝነስ ሀይማኖታዊ ፣ሁሉንም አይነት በሽ በሽ ነው አሁኑኑ ይቀላቀሉን 🙏


ስለ ስምና ዝናህ ሳይሆን ስለ ባህሪህ ተጨነቅ ! ምክኒያቱም ባህሪ ማንነትህ ሲሆን ዝናህ ግን ሌሎች ስላንተ እሚያስቡት ነውና !

@PsychologyCentral✅

3.6k 0 21 15 144

ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ላይ ህይወትህን አትመስርት።

ሁልጊዜ ሌሎችን ለማስደሰት ስትሞክር፣ በቀስታ የራስህን ሕይወት መኖር ትረሳለህ።

አንድ ሰው ይወድሃል፣ ሌላው ይጠላሃል።
አንዱ ያደንቅሃል፣ ሌላው ይተችሃል።

ይህን ሁሉ ማስተካከል አትችልም።

የሌሎችን አስተያየት ሁሉ ለማስደሰት ስትኖር፣ ራስህን ማስደሰት የሚችል ሰው ለመሆን ግን ትረሳለህ።

📝 ከመጽሐፍ የወሰደ (The Courage to Be Disliked)
🔔 @PsychologyCentral✅

5.2k 0 23 6 118

ሰዎች ሁልጊዜ በቃላቸው እውነቱን አይናገሩም፤ ነገር ግን የቱንም ያህል ለመደበቅ ቢሞክሩ፣ የፊታቸው ገፅታ (Facial Expressions) እውነተኛ ስሜታቸውን እና ሀሳባቸውን አሳልፎ ይሰጣቸዋል።

​ሰዎች ምን እያሰቡ እንደሆነ ከፊታቸው ላይ ለማንበብ የሚረዱህን ጥቂት ቁልፍ የፊት ገፅታ ምልክቶች ልንገርህ፦

​ቅፅበታዊ የፊት መለዋወጥ (Micro-Expressions) ፡ አንድ ሰው ስሜቱን ለመደበቅ ሲሞክር፣ ለሰከንድ ክፍልፋይ ትክክለኛው ስሜቱ (ቁጣ፣ ፍርሃት፣ ወይም ንቀት) ፊቱ ላይ ታይቶ ይጠፋል። ይህን ቅፅበታዊ ለውጥ ማስተዋል ከቻልክ፣ ከፈገግታው ጀርባ ያለውን እውነተኛ ማንነቱን ወይም የተደበቀ አላማውን ማወቅ ትችላለህ።

​የውሸት ፈገግታ (The Fake Smile) ፡ እውነተኛ ፈገግታ አይን አካባቢ ያሉትን ጡንቻዎች ያጨማድዳል (የአይን ዳር ይሸበሸባል)። አንድ ሰው ከንፈሩን ብቻ በመጠቀም ፈገግ ካለ፣ ያ ፈገግታ የውሸት ነው። ወይ የሆነ ነገር እየደበቀህ ነው ወይም ስሜቱን ሸሽጎ አንተን ለማስደሰት ብቻ እያስመሰለ ነው።

​ከንፈርን መምጠጥ ወይም መሰብሰብ (Lip Pursing) ፡ አንድ ሰው አንተ ስትናገር ከንፈሩን ወደ ውስጥ ከሰበሰበ (ከመጠጠ)፣ በሀሳብህ አልተስማማም ወይም ሊነግርህ ፈልጎ የደበቀው ሚስጥር አለ ማለት ነው። ይህ ምልክት ብዙውን ጊዜ ተቃውሞን ወይም መረጃን መከልከልን ያሳያል።

​የአንድ በኩል ፈገግታ (The Smirk) ፡ የሰውየው የፊት ገፅታ በአንድ በኩል ብቻ ፈገግታ ካሳየ (አንዱ የከንፈር ጥግ ብቻ ከፍ ካለ)፣ ይህ የንቀት፣ የበላይነት ስሜት፣ ወይም አንተን አቅልሎ የማየት ትልቅ ምልክት ነው። ይህ ገፅታ ግለሰቡ በውስጡ "ከአንተ የተሻልኩ ነኝ" ብሎ እንደሚያስብ ያሳብቅበታል።

እነዚህን የፊት ገፅታ የማንበብ ጥበቦች ስትረዳ ሰዎች በቃላት ሊያታልሉህ አይችሉም። ከሚነግሩህ ውብ ቃላት ይልቅ፣ ፊታቸው ላይ የተፃፈውን እውነት ታነባለህ። ማንም ሰው በቀላሉ ስሜትህን አይጫወትበትም፤ ምክንያቱም እውነተኛውን የሰዎችን ማንነት እና አላማ አስቀድመህ ስለምትረዳ እርምጃህን በጥንቃቄ ትራመዳለህ!

​@PsychologyCentral ✅


🧠 PSYCHOLOGY የሰው አእምሮን ለመረዳት የሚያስችለን ሳይንስ

ሰው ለምን እንደሚያስብ ፣ ለምን እንደሚሰማው እና ለምን እንደሚያደርገው ለመረዳት ስንሞክር ወደ Psychology (ሳይኮሎጂ) እንመጣለን።

Psychology የሰውን አእምሮ፣ ስሜት እና ባህሪ በሳይንሳዊ መንገድ የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ ነው።

አንድ ሰው ሲደሰት ለምን እንደሚስቅ፣ ሲፈራ ለምን እንደሚሸሽ፣ ሲቆጣ ለምን የተለየ ውሳኔ እንደሚወስን እና አንዳንድ ጊዜ እያወቀ እንኳ ከሚፈልገው በተቃራኒ ለምን እንደሚሠራ ለመረዳት Psychology ይረዳናል።

በእውነቱ የሚገርመው ግን የሰው ባህሪ ሁልጊዜ ቀጥተኛ አለመሆኑ ነው።

Psychology ሰዎችን በፍጥነት ለመፍረድ የሚያስችል “ሚስጥራዊ መንገድ” አይደለም።

የሰውን ባህሪ ከጀርባው ያለውን ምክንያት በጥልቀት ለመረዳት የሚሞክር ሳይንስ እንጂ።

@PsychologyCentral✅


💬 የመወያያ ሀሳብ

Overthinking ችግር ነው ወይስ አእምሯችን ሊጠብቀን የሚሞክርበት መንገድ?


ችግሩ ገንዘብ፣ ምግብ፣ ውሃ ወይም መሬት ማጣት አይደለም። ችግሩ እነዚህን ነገሮች የሰውን ችግር ከመፍታት ይልቅ የራሳቸውን ሃይል ለማስከበር ይበልጥ ለሚጨነቁ ስግብግቦች እንዲቆጣጠሩት ስልጣን መስጠታችን ነው።


-- Bill Hics --

@PsychologyCentral✅

7k 0 14 2 113

The Subtle Art of Not Giving a Fck@PsychologyCentral.pdf
1.0Mb
በጥበብ_የመኖር_እሴት@PsychologyCentral.pdf
1.6Mb
📖 The Subtle Art of Not Giving a F*ck

ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር አትሞክር። ለሚገባህ ነገር ብቻ ጉልበትህን ስጥ፤ ለቀረው ሰላም ስጠው።

@PsychologyCentral✅

8k 0 85 1 57

📖 Mark Manson ‹‹The Subtle Art of Not Giving a F*ck››

ሕይወት ሁሌ እንደምንፈልገው አትሄድም። ሰዎች ያስቆጣሉ፣ እቅዶች ይበላሻሉ፣ ውድቀት ይመጣል፣ አንዳንዴም ያለንን ነገር ሁሉ በቂ እንዳልሆነ ይሰማናል።

ችግሩ ግን ችግር መኖሩ ብቻ አይደለም፤ ለምን ያህል ነገር እንደምንጨነቅ አለመምረጣችን ነው።

ማርክ ማንሰን በዚህ መጽሐፍ የሚያስተምረው “ምንም ነገር አይገድህ” ማለት አይደለም። ይልቁንም ለሚገባቸው ነገሮች ብቻ ጉልበትህን፣ ጊዜህንና ስሜትህን ስጥ የሚል ሀሳብ ነው።

ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም። ሁሉንም ችግር ማስወገድም አትችልም። ግን የትኛውን ችግር ለመቀበል እንደምትፈልግ መምረጥ ትችላለህ።
The Subtle Art of Not Giving a F*ck ስለ ግድ የለሽነት ሳይሆን፣ ስለ ትክክለኛው ነገር ላይ ግድ ስለመስጠት ነው።

📚 The Subtle Art of Not Giving a F*ck
✍️ Mark Manson

@PsychologyCentral✅


🪞 የራስ ማንነት

ብዙ ጊዜ ብቻችንን ስንሆን እና ከሰዎች ጋር ስንሆን ባህሪያችን ፍጹም ይለያያል። ከሰዎች ጋር ስንሆን ያልሆንነውን ሆነን ለመታየት እንጥራለን። ይህም ከትክክለኛ ማንነታችን ጋር የሚጋጭ ሊሆን ይችላል።
ለምን በራሳችን ማንነት እናፍራለን? ለምንስ በራሳችን መተማመናችንን እናጣለን? 🤔

ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ስለምንፈልግ ነው። “ባይቀበሉንስ?” ብለን እንፈራለን። በሌሎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን ስንል ግን የራሳችንን ዋጋ ያለውን ማንነት ትተን ያልሆንነውን መሆን እንጀምራለን።
ነገር ግን ሁሌም በመስታወት ፊት ስንቆም የምናየው ሁለት ገጽታ ያለው አንድ ሰው ነው። 🪞

ማስመሰላችንን ትተን ወደ እውነተኛ ማንነታችን ስንመለስ የሕሊና ሰላማችንን እናገኛለን። ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡት ሁሉ ሊያስጨንቀን አይገባም። ይልቁንም መሆን የምንፈልገውን ሰው ለመሆን እንጥር።

ራሳችንን ስንቀበልና በማንነታችን ስንተማመን፣ ሌሎችም ማንነታችንን ማክበርና መቀበል ይጀምራሉ።
“ባለቤቱ የናቀውን አሞሌ…” አይደል ተረቱ?
እኛ ራሳችንን እስካላከበርን ድረስ ሌላው እንዲያከብረን መጠበቅ ከባድ ነው። ስለዚህ በመልካም ባህሪያችን እንኩራ፤ ተቀባይነትን ለማግኘት ስንል አስመሳይና ዋሾ አንሁን።
አስመሳይነት የሚያምረው ለእስስት ብቻ ነው! 🦎

እኛ ግን ሰዎች ነንና እናቁም።
❤️
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ።

@PsychologyCentral✅

10.2k 0 42 25 159

የመወያያ ጥያቄ

ያልተገደበ ገንዘብ ቢኖራችሁ ፣ መጀመርያ የምታደርጉት ነገር ምንድን ነው ?


ስንቶቻችሁ ይህንን መፅሐፍ አንብባችሁታል ?

አንብቤዋለሁ ❤️ ፣ አላነበብኩትም 🤝 ፣ ጀምሬው ነበር
🔥


How To Win Friends and Influence People @PsychologyCentral.pdf
1.4Mb
ጠብታ ማር በዴል ካርኔጌ@PsychologyCentral.pdf
7.8Mb
📔How to Win Friends and Influence People ‹‹ጠብታ ማር››

ሰዎችን ለመቀየር ሁልጊዜ በትዕዛዝና በትችት መናገር አያስፈልግም። የሌላውን ፍላጎት ተረድተን ከእሱ እይታ ስንጀምር፣ የምንፈልገውን ለውጥ በቀላሉ ማምጣት እንችላለን።

“ሰውን ለመምራት መጀመሪያ እሱን መረዳት ያስፈልጋል።”

@PsychologyCentral✅


📔How to Win Friends and Influence People | የጠብታ ማር

አንድ ሰው ስህተት ሲሠራ ወዲያውኑ “ስህተት ነው የሠራኸው!” ብለን ብንነግረው ምናልባት ስህተቱን ከማረም ይልቅ ራሱን ለመከላከል ይሞክራል። ሰው ራሱን ትክክል ለማድረግ ሲጣር የሌላውን አስተያየት መቀበል ይከብደዋል። ስለዚህ ካርኒጌ ሰዎችን ለመለወጥ ከመኮነን ይልቅ ለማስተዋል መሞከርን ያስቀድማል።

አንድ አባት ልጁ የተሳሳተ ውሳኔ ሲወስን ሁልጊዜ “አንተ ምንም አታውቅም!” ብሎ ቢጮህበት፣ ልጁ የአባቱን ምክር ለመስማት ከመፈለግ ይልቅ ከእሱ ለመራቅ ሊጀምር ይችላል። ነገሩን በሌላ መንገድ ቢያይና “እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ አስተያየት አለኝ፤ እስቲ አብረን እንየው” ቢለው ግን ልጁ ራሱን እንደተከበረ ይሰማዋል። ከዚያም ምክሩን ለመስማት የበለጠ ይፈልጋል።

ይህ የካርኒጌ ዋና ሀሳብ ነው፤ ሰዎችን በግፍ መቀየር አይቻልም። ግን እነሱ ከሚያዩበት ቦታ ተነስተን ስንናገራቸው የምንፈልገውን ለውጥ ማምጣት ይቀላል።

ሰው ራሱን እንደሚወድ ሌላውም ሰው ራሱን ይወዳል። ስለዚህ ከሰዎች ጋር ስንነጋገር የእኛን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የእነሱንም ፍላጎት ማየት ከቻልን፣ ግንኙነታችን በግድ ሳይሆን በመግባባት ይገነባል።

@PsychologyCentral✅


ስለ አንድ ነገር ጥቂት እውቀት ያላቸው ሰዎች እራሳቸውን እንደ ትልቅ አዋቂ አድርገው የማሰብ እና ከመጠን በላይ በራስ የመተማመን አላቸው። በተቃራኒው ግን፣ ስለ ጉዳዩ በጥልቀት የሚያውቁ እና ባለሙያ የሆኑ ሰዎች ነገሩ ሰፊ መሆኑን ስለሚረዱ፣ በራሳቸው ላይ ያላቸው መተማመን ዝቅተኛ ባይሆን እንኳን "ብዙ የምቀረው ነገር አለ" የማለት እድላቸው ሰፊ ነው።

@PsychologyCentral✅


"የሕይወትህ ደስታ የተመሠረተው በአስተሳሰብህ ጥራት ላይ ነው።"

@PsychologyCentral✅


"መልካም ቃላት አጭር እና ለመናገር ቀላል ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን የእነሱ ማሚቶዎች በእውነት ማለቂያ የለሽ ናቸው።"

— Mother Teresa —

@PsychologyCentral✅


ወጣትነት ማለት...."

ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም!

ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም!

ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!

ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም!

ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!


ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም!

ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም!

ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም...!

ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው ።

ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው ።

ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው ።

ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ።


ወጣትነት ብርሃን ነው ። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ።

ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት እሳት ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ።

ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።

✍️አዘርግ

@PsychologyCentral✅

14k 0 145 29 334

"ሰው ትልቁን ትምህርት የሚያስተምር... ከተማረው ሳይሆን ከኖረው ካስተማረህ ነው!

@PsychologyCentral✅

11k 0 24 4 184

ጭንቅላት እንደሆድ አይደለም ሲጎድል አያስታውቅም!

- Arabic Proverbs

@PsychologyCentral✅

20 last posts shown.