ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ እና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢዎች በኢትዮጵያ የዲጂታል የጤና ክፍያ ስርዓትን ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተፈራረሙ ።
ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ከኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር የፈጸሙት ስምምነት ደህንነቱ የተጠበቀ እና በቀጣይም በአገር አቀፍ ደረጃ የዲጂታል ክፍያ አማራጭ ለማቀረብ የሚያስችል ነው። ይህ አጋርነት የፋይናንስ አካታችነትን እውን ለማድረግ፣ የጤና አገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈጸም እንዲሁም አገልግሎቶችን በአገር አቀፍ ደረጃ አሻሽሎ ለማዳረስ የሚያስችል ነው።
ኤም-ፔሳ የሚያቀርበው የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን ተጠቅመው የጤና ፋቺሊቴስ ሥራቸውን ለመከወን፣ የወረቀት ገንዘብ ዝውውርን ወደዲጂታል አማራጭ ለማዘመን፣ የኢንሹራንስ ክፍያዎችን በቀላሉ ለመፈጸም እኒዲሁም ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የደሞዝ ክፍያን በጊዜው ለመክፈል የሚያስችል ይሆናል።
ይህ ትብብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በፋይናንስ ሚኒስቴር፣ በጤና ኢንሹራንስ አገልግሎቶች እንዲሁም በዩኤንዲፒ ቤተር ካሽ አላያንስ በጋራ የሚደገፍ ሲሆን የሙከራ ትግበራው በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ የጤና አገልግሎት ማዕከላት የሚጀመር እና ለጤና አገልግሎት ሰጪዎች እና ለተጠቃሚዎች የፋይናንሻል እውቀት ማሻሻያ ስልጠናንም የሚያካትት ነው።
ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የጤናውን ዘርፍ በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ከማዘመን በተጨማሪ አካታች፣ ግልጽ እና ፈጣን አገልግሎቶችን በማቅረብ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራዕይ መሳካት ሁልጊዜም ይተጋል።