መጋቢት 24 2017
ኢትዮጵያ የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ፓርኮችን የማቋቋም ውጥን እንዳለት ተነገረ።
ፓርኮቹ የሚቋቋሙት ለአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምቹ ናቸው በተባሉ አካባቢዎች ነው ተብሏል፡፡
ዘጠነኛው አለም አቀፍ የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ኤክስፖ ትናንት በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።
ኢትዮጵያ የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለውጪ ገበያ ማቅረብ ከጀመረች ሃያ ዓመታት ተቆጥረዋል።
በእነዚህ ጊዜያት ጥሩ የሚባል ዕድገት ዘርፉ ማሳየቱ በተለያዩ ወገኖችይጠቀሳል።
የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት እንኳን ከቡና ቀጥሎ ዘርፉ ሁለተኛ ደረጃ ይዟል።
ከሁለት መቶ ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ ዘርፍ እንደሆነም ተነግሯል።
ኢትዮጵያ ካላት እምቅ አቅም አንጻር ግን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ደርሷል ለማለት እንደማያስደፍር የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ይናገራሉ።
የዘመነ የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ እንዲኖረን እየሰራን ያለውም ለዚሁ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ በዘጠነኛው አለም አቀፍ ፤
የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ኤክስፖ መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ተናግረዋል።
የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስትራቴጂ እንደ አገር መዘጋጀቱን የተናገሩት ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ መለስ መኮንን ናቸው።
ስትራቴጂው በአነስተኛ አርሶ አደሮች እና በትላልቅ ባለ ሃብቶች የሚመረተው አበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ በተሻለ መልኩ ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል የሚል እምነት እንዳለ ጠቅሰዋል።
እንደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አይነት የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ፓርኮችን የማቋቋም ውጥን እንዳለም ሚኒስትር ድኤታው ተናግረዋል።
ፓርኮቹ የሚቋቋሙት ለአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምቹ ናቸው በተባሉ አካባቢዎች እንደሚሆንም ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት መንግስትን ጨምሮ በዘርፉ ድርሻ ባላቸው ሁሉም ወገኖች እያደገ የመጣ ነው ያሉት ደግሞ ፤ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ነጋ መኳንንት ናቸው።
በሚሊኒየም አዳራሽ በተከፈተው እና እስከ መጋቢት 25 / 2017 በሚቆየው ኤክስፖ ላይ ከ140 ሀገራት የተውጣጡ ከ40 በላይ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሙሉ ዘገባውን…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/hjumkhyu/
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2