It's been a long long time !
[ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ]
ፅድ አናት ላይ የኮኮብ ዕድ ሳይ - በዝንፍ ቅርንጫፍ የተጥመለመለ ሲባጎ ብልጭ ድርግም ሲል - የሥጦታ ሙዳዮች ዙሪያው ሲቆለል - ዜማ ባየሩ ሲናኝ ፥
በዓመቱ ኦሜጋ ሁሉም ወደልጅነቱ ሲሰበሰብ - በቀለም ያሸበረቁ ሞሳዎች ተሰብስበው ሲዘምሩ - ኩርሽም ከረሜላዎች ከአፋቸው ሟሙቶ ሲወርድ - ህፃንነት ፍፅምና መሆኑን አምነው አዛውንቶች አሜን ሲሉ ፥
የበረዶ ጥጥ ብናኞችን አሳበው መላዕክት ሰብ'ን ሲስሙ - የከተማው ካቴድራሎች ስለግርግሙ ንጉሥ ብስራት ሲደውሉ - የተነጠፉ መንገዶች ሁሉ ወደቤት ሲወስዱ - በብልቃጥ የነበረ መንፈስ ተኖ ቤትን ሲሞላ ፥
የዛፉ ላይ ድቡል ኳሶች እየተብረቀረቁ ሲወዛወዙ - ቀያይ ሻማዎች ግለው የቤቱን ድባብ ሲለኩሱ - በቁር ቆፈን ውስጥ የነበሩ ጉንጮች ሲፈግጉ - ልጆቻቸው የታከቡላቸው እናቶች አይን እንደታጠበ ብርጭቆ ሲብለጨልጭ - ሳቆች ተርፈው ወለል ላይ ሲወዳድቁ ፥
በክፍት ልቦች ውስጥ የገባ ንዝረት መልሶ ሲፈስ - ፍልቅልቅ ብላቴኖች ጌታውን እንዳየ ውሻ ከግድግዳ ግድግዳ ሲዘሉ ። ምኞታቸውን ጦምረው የሚመጣውን ሽማግሌ በተስፋ ሲጠብቁ ፥
ቃጭል ያነገቱ አጋዘኖችን በየብስ ሠረገላ እየተጋለቡ ፥ በራማ ጋሪ እየከነፉ ሲመጡ - ጆንያ ተሸካሚው ሽማግሌ ሪዙን እየፈተለ ሲደውል - ቦቲውን እያማታ በየአጥቢያው ሆ'ሆይ ሲል …
ከአንቺ መሆን እመኛለሁ ። አድማስ ተሻግሮ የተኛ ልቤ ፥ ቀኑ ሲደርስ ጠብቆ ይቆሰቆሳል ። Carla Thomas ፥ እየዘፈነች ነው ፥
It's been a long long time ,
Cant' explain why you crossed my mind
I guess it's just to wish you ...
a merry Christmas ❄️