በከንቲባ ጽ/ቤት እና በጊቢ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጋር በመሆን “ወርቃማዋ ሰኞ” ብለን ዘወትር ሰኞ የምናደርገውን የዉይይት ፕሮግራም አንደኛ ዓመት ዛሬ ማለዳ አክብረናል።
እነሱ ጨለማው ሰኞ (Black Monday ) የሚሉትን እኛ ወርቃማው ሰኞ ብለን ላለፉት 52 ሳምንታት ከጥዋቱ 2 እስከ 3 ሰአት ባለዉ ጊዜ የከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ የዋና ስራ አስኪያጅ፣ የኮሙዩኒኬሽን እና የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በጋራ በመሆን በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደ ቤተሰብ እየተማማርን እና እየተመካከርን ሳምንቱ ሙሉ ወርቃማ እንዲሆንልን መልካም ምኞት ተለዋዉጠን አብረን ቡና ጠጥተን ስራችንን እንጀምራለን።
ይህንን የምናደርገዉ የበለጠ ለተገልጋዮች ቅርብ ለመሆን እና አገልግሎታችንን ለማሻሻል እርስ በእርሳችን የምንመካከርበት፣ የምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት እንዲሁም እንደ መሪ ታች ካሉ ሰራተኞቻችን ጋር ጭምር ማህበራዊ ህይወታችንን ከስራችን ጋር በማስተሳሰር ለመቀራረብ እና ሃሳብ ለመለዋወጥ ሲሆን በዚህ ሁኔታ 52 ሳምንታትን አሳልፈናል። በዛሬዉ ፕሮግራማችን ደግሞ ዶ/ር ምህረት ደበበ ስለ ስራ እና ህይወት (work and life balance) ሚዛን መጠበቅ ትምህርት አካፍለውናል።
ፕሮግራሙ በከንቲባ ጽ/ቤት ይጀምር እንጂ ወደ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት እና መስሪያ ቤቶች የሚሰፋ ሲሆን እስከ አሁን የሄድንበትን የ52 ሳምንታት ቆይታችንን ጥንካሬ እና ድክመት ለይተን ወደ ሌሎች ቢሮዎቻችን የምናስፋፋው ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@subitime