The Nation Post ️


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Politics


Join The Nation Post for fearless political reporting and engage in critical discussions on global politics, conflict, and change. Stay informed and stand up for democracy with us.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Politics
Statistics
Posts filter


#News
የትግራይ ነጋዴዎች ከሰሜኑ ጦርነት በፊት የወሰዱትን የባንክ ብድር ወለድ እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ቅሬታ አስነሳ።

በጦርነቱ ምክንያት ባንኮች በአዋጅ መዘጋታቸዉን ተከትሎ በነጋዴዎች መከፈል የነበረበት የባንክ ብድር ሳይከፈል በመቅረቱ ነዉ ተብሏል።

በዚህም የተጠራቀመዉ የብድር ወለድ ነጋዴዎች ካላቸዉ የጠቅላላ ሀብት መጠን በላይ ሆኖ መገኘቱን የትግራይ ክልል ንግድ እና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኘነት ዳይሬክተር ገልፀዋል።


ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸም የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው 178 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተለቀቁ።

ከአራት ዓመት ገደማ በፊት በትግራይ ክልል በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ "በክህደት መንፈስ ጥቃት" ከፍተዋል በሚል እስከ የሞት ቅጣት ድረስ ተላልፎባቸው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የሠራዊቱ አባላት በይቅርታ ተለቀቁ።

በእስር ላይ የነበሩት የሠራዊቱ አባላቱ ይቅርታ የተደረገላቸው አዲስ ዓመትን በማስመልከት እንደሆነ የመከላከያ ሠራዊት ትናንት ጷጉሜ 5/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
@TheNationPost


#መልካም_አዲስ_ዓመት

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የድል፣ የስኬት፣ ያቀድነው እና ያሰብነው ሁሉ የሚሳካበት ዓመት ያድርግልን


#NEWS:- ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት ተከሰሰች

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ተቃውሞ አለኝ የምትለው ግብጽ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ ኢትዮጵያን ከሳለች፡፡

ግብጽ በዛሬው ዕለት ለጸጥታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸችው ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለአምስተኛ ዓመት ውሃ ሙሌት አከናውናለች ይላል፡፡

በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስደተኞች እና ግብጻዊያን አርበኞች እንደተጻፈ የተገለጸው ይህ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የግብጻዊያንን ጥቅም በሚጻረር መልኩ የውሃ ሙሌት እያካሄደች ነው ብሏል፡፡
@TheNationPost


በግብፅ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ እንድታደርጉ።

የግብፅ መንግስት ከትላንት ጀምሮ ኢትዮጵያውያንን ማፈስ ጀምሯል አሰሳው በብዛት ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት አካባቢ እና በሚሰሩበት አካባቢ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለያቹ።

ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ሼር አድርጉ
@TheNationPost


እንኳን ወደ ቤተሰቦቻችሁ ተቀላቀላችሁ
@TheNationPost


#ለተማሪዎች


#ዜና: በኢትዮጵያ ሲሰለጠኑ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አባላት ስልጠናቸውን አጠናቀው መመረቃቸው ተገለጸ

ስልጠና ሲሰጣቸው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አዳዲስ ምልምል አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠናቸውን ጨርሰው መመረቃቸው ተገለጸ።

ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የተመረቁት የሶማሊንድ ወታደሮች በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ በተከታታይ ዙር የተጠናከረ ስልጠና ሲሰጣቸው ከነበሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት መካከል መሆናቸውን እና 8ኛ ዙር ሰልጣኞች መሆናቸውን ሆርን ዲፕሎማት በድረገጹ አስነብቧል።

በታላቅ ድምቀት በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መታደማቸውን የጠቆመው ዘገባው በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር አጉልቶ ያሳየ ነው መባሉን አስታውቋል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ በክብር ከታደሙት እንግዶች መካከል የሶማሌላንድ ብሄራዊ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኑህ እስማኤል ታኒ ይገኙበታል ያለው የድረገጹ ዘገባ የጦር አዛዡ በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ መገኘት ሶማሌላንድ ብሔራዊ የመከላከያ አቅሟን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ያሳየ ነው ነው ሲል ገልጿል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የሶማሊላንድ ወታደሮች በተከታታይ በኢትዮጵያ ስልጠና መውሰዳቸውንም አውስቷል።
@TheNationPost


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር ነው፡፡

ስለሆነም ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ ሲያደርግ የነበረውን በረራ እንደሚያቋርጥ አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
@TheNationPost


#ኢትዮጵያ
የሱማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ ሁሉም የሶማሊያ ዜጋ እና አመራር ለወታደራዊ ግዳጁ ይዘጋጂ ሲሉ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፈዋል ፡፡
ግብፅ በጎን በአባይ ጉዳይ ጦርነት ልገባ ነው እያለች ነው።
ኤርትራ የማይቀር ፍልሚያ አለብኝ እያለች ነው።
@TheNationPost


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ባንተ እንድደረግ የማትፈልገውን በሌላ አታድርግ።
@TheNationPost


" ሰራተኛው ኑሮውን እንዴት እንደሚመራ ግራ ተጋብቷል" ኢሰማኮ

በአሁኑ ወቅት በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ሰራተኞች ደመወዝ 5 ሊትር ዘይት እንኳን አይገዛም ፤ በተለይ የፋብሪካ ሰራተኞች ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን አብራርተዋል።
@TheNationPost


#ዜና
ኢትዮጵያ የጅቡቲን ወደብ እንድታስተዳደር ጥሪ መቅረቡ ተሰማ።

ኢትዮጵያ የጂቡቲ ንብረት የሆነውን የታጁራ ወደብ “ሙሉ በሙሉ እንድታስዳድር” አገራቸው አማራጭ ሃሳብ ማቅረቧን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ገልጸዋል፡፡
@TheNationPost


የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዞን አደረጃጀቱን መልሶ ለማዋቀርና ስያሜውንም ለመቀየር የሚያስችለው ጥናትና ውይይት እያደረገ ሰምተናል።

የዚህ የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ አንድ አካል የሆነው የወረዳና ቀበሌ አደረጃጀት ለውጥ ተጠናቆ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጿል ።
@TheNationPost


የግብፅ የዘመናት ምኞቷ ተሳካላት!

ከሶማሊያ ጋር ባደረጉት ስምምነት እስካፍንጫው የታጠቀ የግብፅ ጦር የኢትዮጵያ ድምበር አቅራቢያ የጦር ሰፈር ገንብቶ ሰፍሮዋል! ከዚህ በተጨማሪ በአፍሪካ ህብረት ፍቃድ በአሚሶም ስር የምታቀፉ ተጨማሪ ጦሯን ገና ወደ ሶማሊያ ልታስገባ እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል!

ያሳዝናል!
@TheNationPost


የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሞቃዲሾ መሣሪያ ጭነው መጡ።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሁለት የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች (አንቶኖቮች) ወደ ሞቃዲሾ አደን አዴ አለም አቀፍ ኤርፖርት መጥተዋል።

የጦር አውሮፕላኖቹ ክላሽ እና ስናይፐር የመሳሰሉ የጦር መሳሪያዎችን እንደዚሁም ተተኳሾችን ጭነው እንደመጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የመጡት የጦር መሳሪያዎች በ7 የጭነት ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ መከላከያ ሚኒስቴር መወሰዳቸውን የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

12 የሚደርሱ የግብጽ የጦር መኮንኖች መሳሪያውን ይዘው የመጡ ሲሆን ምናልባትም ለሶማሊያ ወታደሮች ስልጠና ለመስጠት ሊቆዩ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ አለ።
አንዳንድ ምንጮች በገለጹት መሰረት አውሮፕላኖቹ ከላይ ከተገለጹት የጦር መሳሪያዎች በተጨማሪ የግንኙነት መሳሪያዎችንም ጭነው መጥተዋል።

በቀጣዮቹም ቀናት ተመሳሳይ በረራዎች እንደሚኖሩ፣ ወደ ሂራን ክልል ብለደወይን ከተማ እንደሚጓዙ መረጃዎች አመላክተዋል።

አብዛኞቹ የሶማሊያ ግዛቶች የግብጽን ጦር መግባት ገብነት እየተቃወሙ ናቸው።
@TheNationPost


ሁለቱም በትግራይ የሚገኙ ህወሃታውያን ጉሩፖች በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በተገኙበት በመቐለ ስብሰባ ተቀምጠዋል።
@TheNationPost


ኢትዮጵያውያንን አሳፍራ ወደ የመን ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በመስጠሟ 13 ሰዎች ሲሞቱ 14ቱ ጠፍተዋል!
@TheNationPost


We stand with Pavel @Durov, privacy and truth.

Which is particularly important no
w.

#FREEDUROV


#FreeDurov #FreeSpeech #StandWithTelegram #PrivacyMatters
@TheNationPost

20 last posts shown.