አባ-ጨጓሬም አባ ነው አትታለል እሽ
👉በኮፍያቸው ስር‼️
--------------------------
ማንም እየመጣ፤
ሁሌም አይዝገንህ እንደ ሰፌድ ቆሎ፡
እንደ አህያ አይጫንህ፤
አትሁን በፍፁም መካን እንደ በቅሎ፡
አትቅር በአየር ላይ፤
አጨብጫቢ ሆነህ ሐሳብህ ተሰቅሎ፡
ራስህን አፅዳ፤
ዘላለም አትኑር ዘውግህ ተመሳቅሎ፡
ሁሉንም አትመን ግን በጣም ተጠንቀቅ፡
ሰማይ ቤት ለሚልህ ምድርህን አትልቀቅ፡
ለአፍህ ልጓም አብጅ ለስሜትህም ልክ፡
ተዓሱብ አስክሮህ ዑስታዝክን አታምልክ፡
ይልቅስ ነብስ እወቅ፤
ሁሉም ሸህ አይደለም እየፈታ እሚያስር፡
ቅዱስ ነኝ እያለ፤
ፊትና እሚያነፈንፍ ፊርቃ የሚያበስር፡
ስንቶች በዑስታዝ ለምድ፤
እባብ ተቀምጧል በኮፍያቸው ስር፡
.....ኑረዲን አል-ዓረብ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
👉በኮፍያቸው ስር‼️
--------------------------
ማንም እየመጣ፤
ሁሌም አይዝገንህ እንደ ሰፌድ ቆሎ፡
እንደ አህያ አይጫንህ፤
አትሁን በፍፁም መካን እንደ በቅሎ፡
አትቅር በአየር ላይ፤
አጨብጫቢ ሆነህ ሐሳብህ ተሰቅሎ፡
ራስህን አፅዳ፤
ዘላለም አትኑር ዘውግህ ተመሳቅሎ፡
ሁሉንም አትመን ግን በጣም ተጠንቀቅ፡
ሰማይ ቤት ለሚልህ ምድርህን አትልቀቅ፡
ለአፍህ ልጓም አብጅ ለስሜትህም ልክ፡
ተዓሱብ አስክሮህ ዑስታዝክን አታምልክ፡
ይልቅስ ነብስ እወቅ፤
ሁሉም ሸህ አይደለም እየፈታ እሚያስር፡
ቅዱስ ነኝ እያለ፤
ፊትና እሚያነፈንፍ ፊርቃ የሚያበስር፡
ስንቶች በዑስታዝ ለምድ፤
እባብ ተቀምጧል በኮፍያቸው ስር፡
.....ኑረዲን አል-ዓረብ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi