የኢትዮ-ፓኪስታን የወንድማማችነት በዓል በእስላማባድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተከበረ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእስላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት እና ወንድማማችነት ለማጠናከር በሚል የኢትዮ-ፓኪስታን በዓል አከበረ።
“የኢትዮ-ፓኪስታን ወንድማማችነት ሻምፒዮኖች” በተሰኘው ስነ-ስርዓት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እውቅና መሰጠቱን እና የህዝብ-ለህዝብ ዲፕሎማሲ ተከናውኗል።
በፓኪስታን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እድገት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮ-ፓኪስታን ወንድማማችነት ሻምፒዮኖችን እውቅና የሚሠጥ እና በሀገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ግንኙነት የሚያድስ ነው ያሉ ሲሆን ሚዲያ እና የሲቪል ማህበረሰቦች ይህን ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ረገድ ያላቸውን ጉልህ ሚና ገልጸዋል።
ሁለቱም ሀገራት የተሳሳተ መረጃ ስርጭት በተመለከተ የሚያደርጉትን ተጋድሎ አንስተው በተለይም ስለ ኢትዮጵያ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ ዓለም አቀፍ ትርክቶችን አውግዘዋል።
በዲጂታል ዘመን የተሳሳተ መረጃን በመዋጋት እና ትክክለኛ መረጃን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ሚዲያዎች ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን በመግለፅ እውነታን በማካፈል አዎንታዊ ዓለም አቀፍ አመለካከት መፍጠር እንችላለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ መሪዎችን የምታስተናግድ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት አረንጓዴ ለውጥ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማራመድ ላይ የምትገኝ ፈጣን እድገት ያላት አገር ናት ብለዋል።