ፈጣሪ እና መልአክ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
33፥56 አሏህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ
"ሶለዋህ" صَلَوٰة የሚለው ቃል "ሶላ" صَلَّى ማለትም "ባረከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ቡራኬ" "ረድኤት" በሚል ይመጣል፥ ለምሳሌ፦

መላእክት ከአሏህ ጋር በመስተጻም ተጫፍረው እና ተዛርፈው መምጣታቸው ከአሏህ ጋር የማንነት እና የምንነት ልዩነት እንደሌላቸው አያመላክትም። ለምሳሌ በባይብል፦ ፈጣሪ ከፍጡር ጋር ስግደት የተቀበለበት ጥቅስ እንመልከት፦
1ኛ ዜና 29፥20 ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ። וַיִּקְּד֧וּ וַיִּֽשְׁתַּחֲו֛וּ לַיהוָ֖ה וְלַמֶּֽלֶךְ׃
ንጉሡ የተባለው ዳዊት ሲሆን "ሰገዱ" በሚል በአንድ ግሥ እና "እና" በሚል መስተጻምር ተጫፍሮ መጥቷል። በተጨማሪም፦
ምሳሌ 24፥21 ልጄ ሆይ! ያህዌህን እና ንጉሥን ፍራ። יְרָֽא אֶת־ יְהוָ֣ה בְּנִ֣י וָמֶ֑לֶךְ
ምሳሌ 24፥22 መከራቸው ድንገት ይነሣልና፥
ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል? כִּֽי־פִ֭תְאֹם יָק֣וּם אֵידָ֑ם וּפִ֥יד נֵיהֶ֗ם מִ֣י יֹודֵֽעַ׃ ס
ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ወደ ዋናው ነጥብ እንግባ! ያህዌህ አብርሃምን ከከለዳውያን ዑር ካወጣው በኃላ "እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ሂድ፥ ፍጹምም ሁን" አለው፦
ዘፍጥረት 15፥7 ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ ያህዌህ እኔ ነኝ" አለው። וַיֹּ֖אמֶר אֵלָ֑יו אֲנִ֣י יְהוָ֗ה אֲשֶׁ֤ר הֹוצֵאתִ֙יךָ֙ מֵא֣וּר כַּשְׂדִּ֔ים לָ֧תֶת לְךָ֛ אֶת־הָאָ֥רֶץ הַזֹּ֖את לְרִשְׁתָּֽהּ׃
ዘፍጥረት 17፥1 አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ ያህዌህ ለአብራም ተገለጠለትና፦ “እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ሂድ፥ ፍጹምም ሁን" አለው። וַיְהִ֣י אַבְרָ֔ם בֶּן־תִּשְׁעִ֥ים שָׁנָ֖ה וְתֵ֣שַׁע שָׁנִ֑ים וַיֵּרָ֨א יְהוָ֜ה אֶל־אַבְרָ֗ם וַיֹּ֤אמֶר אֵלָיו֙ אֲנִי־אֵ֣ל שַׁדַּ֔י הִתְהַלֵּ֥ךְ לְפָנַ֖י וֶהְיֵ֥ה תָמִֽים׃
"በፊቴ ሂድ" የሚለው ይሰመርበት! በመቀጠል ያህዌህ መልአኩን ወደ አብርሃም ሎሌ በፊቱ እንደላከ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 24፥7 ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ "ይህችንም ምድር እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝ እና የማለልኝ የሰማይ አምላክ ያህዌህ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይልካል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ። יְהוָ֣ה ׀ אֱלֹהֵ֣י הַשָּׁמַ֗יִם אֲשֶׁ֨ר לְקָחַ֜נִי מִבֵּ֣ית אָבִי֮ וּמֵאֶ֣רֶץ מֹֽולַדְתִּי֒ וַאֲשֶׁ֨ר דִּבֶּר־לִ֜י וַאֲשֶׁ֤ר נִֽשְׁבַּֽע־לִי֙ לֵאמֹ֔ר לְזַ֨רְעֲךָ֔ אֶתֵּ֖ן אֶת־הָאָ֣רֶץ הַזֹּ֑את ה֗וּא יִשְׁלַ֤ח מַלְאָכֹו֙ לְפָנֶ֔יךָ וְלָקַחְתָּ֥ אִשָּׁ֛ה לִבְנִ֖י מִשָּֽׁם׃
የሰማይ አምላክ ያህዌህ እና መልአኩ ሁለት ለየቅል ማንነት እና ምንነት እንደሆኑ እዚህ ጥቅስ ላይ ቁልጭ ብሎ ይታያል። አብርሃም አካሄዱን በፊት ያደረገለት ያህዌህ አምላክ እና መልአኩ በኑባሬ አሁንም ተለያይተዋል፦
ዘፍጥረት 24፥40 እርሱም አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት ያህዌህ መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል። וַיֹּ֖אמֶר אֵלָ֑י יְהוָ֞ה אֲשֶׁר־הִתְהַלַּ֣כְתִּי לְפָנָ֗יו יִשְׁלַ֨ח מַלְאָכֹ֤ו אִתָּךְ֙
"አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት ያህዌህ" የሚለው ይሰመርበት! አብርሃም እና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት አምላክ ያህዌህ ያዕቆብን ከታናሽነቱ ጀምሮ እስከ ትልቅነቱ ድረስ የመገበው አምላክ ነው፦
ዘፍጥረት 48፥15 ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት አምላክ፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ አምላክ። וַיְבָ֥רֶךְ אֶת־יֹוסֵ֖ף וַיֹּאמַ֑ר הָֽאֱלֹהִ֡ים אֲשֶׁר֩ הִתְהַלְּכ֨וּ אֲבֹתַ֤י לְפָנָיו֙ אַבְרָהָ֣ם וְיִצְחָ֔ק הָֽאֱלֹהִים֙ הָרֹעֶ֣ה אֹתִ֔י מֵעֹודִ֖י עַד־הַיֹּ֥ום הַזֶּֽה׃
አብርሃም እና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት አምላክ ያህዌህ ሲልከው የነበረው መልአክ በአመልካች መስተአምር "ሀ ማላኽ" הַמַּלְאָךְ֩ ተብሎ ከያህዌህ ጋር በነጠላ ግሥ ተጫፍሮ እና ተዛርፎ መጥቷል፦
ዘፍጥረት 48፥16 ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነዚህን ብላቴኖች "ይባርኩ"። הַמַּלְאָךְ֩ הַגֹּאֵ֨ל אֹתִ֜י מִכָּל־רָ֗ע יְבָרֵךְ֮ אֶת־הַנְּעָרִים֒
ያዕቆብ ያህዌህን እና መልአኩን በነጠላ ግሥ "ይቫሬኽ" יְבָרֵךְ֮ መባሉ በውስጠ ታዋቂነት "ይባርኩ" የሚል ፍቺ ይኖረዋል፥ "ይቫሬኽ" יְבָרֵךְ֮ ማለት "ይባርክ" ማለት ሲሆን ያህዌህ አምላክ እና የእርሱ መልአክ ሁለት ማንነት ናቸውና። "አምላክ እና መልአኩ ሁለት ማንነት ከነበሩ በብዜት ግሥ "ይትቫርኹ" יתברכו ማለትም "ይባርኩ" ለምን አልተባለም? የሚል ጥያቄ ከተነሳ ይህ በዕብራይስጥ ሰዋስው ውስጥ የተለመደ አወቃቀር ነው፦
ዘኍልቍ 12፥1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያም እና አሮን በእርሱ ላይ "ተናገሩ"። וַתְּדַבֵּ֨ר מִרְיָ֤ם וְאַהֲרֹן֙ בְּמֹשֶׁ֔ה עַל־אֹדֹ֛ות הָאִשָּׁ֥ה הַכֻּשִׁ֖ית אֲשֶׁ֣ר לָקָ֑ח כִּֽי־אִשָּׁ֥ה כֻשִׁ֖ית לָקָֽח׃