#አዳዲስ_መረጃዎች
“ #አደራ” የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በአቶ ብሉጽ ፍትዊ የተዘጋጀ የአዲስ ኪዳን ግሪክኛ - አማርኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፍ ሰኞ ጥቅምት 25 በድምቀት ይመረቃል።
አቶ ብሉጽ ፍትዊ ከማረፋቸው በፊት፣ ለዓመታት የደከሙበት የመዝገበ ቃላት ሥራ ለገርጂ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን በአደራ በሰጡት መሠረት፣ ተገቢውን የአርትኦትና የእርማት ኺደት በመከተል ለህትመት መብቃቱን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልፇል።
መዝገበ ቃላቱን ከ5,000 (አምስት ሺሕ) በላይ የአዲስ ኪዳን ግሪክ ቃላትን በቀጥታ ወደ አማርኛ የሚተረጉም ሲኾን፣ ለእያንዳንዱ የቃል ፍቺም ተዛማጅ የአዲስ ኪዳን ክፍሎችን ያጣቅሳል። አያይዞም የግሪክ አቡጊዳ፣ ሙዳየ ቃላትና አጠቃላይ የግሪክ ቋንቋን ታሪካዊ ዳራ ያቀርባል።
አዲስ ኪዳን በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ እንደ መኾኑ መጠን፣ መዝገበ ቃላቱ ቁልፍ የኾኑ የአዲስ ኪዳን ቃላትን ሥነ ጽሑፋዊና ታሪካዊ ዐውዳቸውን በጠበቀ መልኩ ለመረዳት የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል።
የምረቃ መርሓ ግብሩ ጥቅምት 25 ቀን፥ 2017 ዓ.ም የቤተ እምነት መሪዎች፣ የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎች፣ የነገረ መለኮትና ልዩ ልዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮችን ጨምሮ ከ 1,500 (አንድ ሺሕ አምስት መቶ) በላይ እንግዶች በተገኙበት በስካይላይት ሆቴል ያካሄዳል።
ክርስቲያን ቲዩብ
✨ @yeadoniamedia ✨