ቀን 1፡
የመሲሑ ተስፋ
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን ያለው እቅድ ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ እየገለጠ አሳይቷል።
ዘፍጥረት 3:15 አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ፣ የሴቲቱ ዘር የእባቡን ጭንቅላት እንደሚቀጠቅጠው አምላክ ቃል ገባ። ይህ ሰይጣንንና ኃጢአትን የሚያሸንፍ አዳኝ እንደሚመጣ እግዚአብሔር የገለጠበት የመጀመሪያው ትንቢት ነው። የሰው ልጅ ውድቀት ኃጢአትን አስተዋወቀ፣ እግዚአብሔር ግን ፍጥረቱን አልተወም። ይልቁንም የመቤዠትን እቅድ ገለጠ።
ኢሳይያስ 7:14፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ምልክትን እና ተስፋ ሰጠ ድንግልም ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙም አማኑኤል(እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ) ይባላል ብሎ ተናገረ። ይህ የኢሳይያስ ትንቢት አምላክ ዓላማውን ለመፈጸም በተአምራዊ መንገድ እንደሚሠራ ያስታውሰናል።
ሚክያስ 5:2: ቤተልሔም የምትባል ትንሽ ከተማ የመሲሑ የትውልድ ቦታ እንድትሆን ተመረጠ፤ ይህም የአምላክን ያልተጠበቁ መንገዶች አሳይቷል።ይህም አምላክ ታላላቅ እቅዶቹን ለመፈጸም ብዙ ጊዜ ትንሽ የሚመስሉትን እንደሚጠቀም ጎላ አድርጎ ገልጿል። ድንቄ የሆነውን የእግዚአብሔር ምርጫም አሳይቶናል።
👉ድንግል ፀንሳ ታይቶ ባይታወቅም እሱ ግን ከብዙ ዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ ደግሞም ፈፀመው። ሁኔታዎች እርግጠኛ ያልሆኑ ወይም የዘገዩ ወይም ሊሆኑ የማይችሉ በሚመስሉበት ጊዜም እንኳ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል እርግጠኞች መሆን እንድንችል ጌታ ይህንን እንደምስክር አስቀምጦልናል።
👉 ምንም ያህል ትንሽ የሆንን ወይም ያልበቃን የሆንን ቢመስለን እግዚአብሔር አላማውን ለመፈጸም ሊጠቀምብህ እንደሚችል ልናስብ ይገባል ምክንያቱም የእርሱ ምርጫ በሰዎች መለኪያ ልክ ስላልሆነ እና እይታውም ልዩ ስለሆነ።
👉 እግዚአብሔር እኛን መውደዱ ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ሊያሳየን ስለወደደ ከብዙ ዘመን በፊት ተስፋን ሰጠ እና ሰዎች ያንን ተስፋ በመጠበቅ እንዲፅናኑ አደረገ። ያንን የከበረ እና ከሰው አዕምሮበላይ የሆነውን እቅዱን በመናገር ሊመጣ ያለውን መሲህ በተስፋ በመጠበቅ ያንን የብሉይ ዘመን ሰዎች በፅናት እንዲኖሩ አደረገ። በዚህም ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር እና አክብሮት እግዚአብሔር ገለጠ።
✍በአቢጊያ
💯 share 💯
✨ @yeadonaimedia ✨