ቀን 2፡
የመሲሑ ባህሪ እና ተልዕኮ
በብሉይ ኪዳን የመሲሑ ባህሪ እና ተልእኮ በሚገባ ተገልጿል ይህም ለተሰበረ አለም ተስፋን ገልጧል።
ኢሳይያስ 9፡6-7፡ መሲሑ ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት እና የሰላም አለቃ ተብሎ ተገልጿል:: የጽድቅንም መንግሥት ለዘላለም እንደሚመሰርት ተነግሯል። ኢሳይያስ መሲሑ እንደሚገዛ ብቻ ሳይሆን እንደሚመክር፣ እንደሚያጽናና እንዲሁም ለሰው ልጆች ሰላም እንደሚያመጣ አሳይቷል።
ኤርምያስ 23:5-6፣ መሲሑ ከዳዊት ዘር የመጣ ጻድቅ ንጉሥ ሲሆን ለሕዝቡ መዳንና ፍርድን የሚሰጥ ነው። ኤርምያስ ከምድራዊ ገዥዎች በተቃራኒ በጽድቅና በንጹሕ አቋሙ የሚመራ ንጉሥ እንዳለ አረጋግጦልናል።
ዘኍልቍ 24፡17፡ መሲሑ ከያዕቆብ እንደ ወጣ ኮከብ ተሥሏል፡ አገዛዙንና ብርሃኑን ለአሕዛብ አሳይቷል። የመሲሑ ተጽዕኖ በሩቅ እንደሚበራና አህዛብን ወደ መዳን እንደሚመራ ጎላ አድርጎ ይገልጻል።
👉 የሚወለደው መሲህ ሰው ብቻ ሳይሆን የዘለአለም አምላክም ነው። ሰውሆኖ የተገለጠ መለኮት ነው!
👉 ያ መሲህ ከዘር እና ከቋንቋ ህዝቦችን ዋጅቶ ለራሱ የሚያደርግ እና በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳ የሚያፈርስ ነው። የአይሁድ ብቻ ያልሆነ አህዛብንም የማዳን አቅም እና ፈቃድ ያለው ነው።
👉 የሚወለደው መሲህ ሀጢአትን የማያውቅ ወይም ሀጢአት የሌለበት ይልቁንም የሰዎችን ሁሉ ሀጢአት ማንፃት የሚችል ነው።
👉 የሚወለደው መሲህ የሚመክር የሚያፅናና ለደከሙት ብርታትን የሚሰጥ እና የማይታየው አምላክ ምሳሌ የባህርዩ ነፀብራቅ ነው በዚህም ሰዎች አምላክን በሚገባ እንዲያውቁ የማድረግ አቅም ያለው ነው።
✍በአቢጊያ
💯 share 💯
✨ @yeadonaimedia ✨