Forward from: ሒዳያ ንጽጽር /Hidaya Comparative/
ወንድማችን ኡስታዝ ወሒድ ዑመር አዲሱን መጽሀፉን (አልገደሉትም፣ አልሰቀሉትም) ሶስት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ እህቶች ወጭውን እንዲሸፍኑ በማስተባበር 100 መጽሀፍትን ለሒዳያ ላይብረሪ አስረክቦናል። በተጨማሪም በራሱ በኩል የእሱን መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም 100 ፍሬ የለገሰን ሲሆን ኡስታዝ ጀማል ደግሞ የአህመዲን ጀበልን "ክርስቶስ ማነው?" መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም ስራውን 100 ፍሬ አበርክቶልናል። እያንዳንዳቸው 100 መጽሀፍ በድምሩ 300 መጽሀፍትን ተለግሰውናል። አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው፣ ከዚህ የበለጠ የሚተጉበትን ብርታትም ይወፍቃቸው።
© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
https://t.me/Hidayaic8212
© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
https://t.me/Hidayaic8212