🌷..........ጾመ ፍልሠታ ለማርያም.........🌷
-------------------------------
•➢ ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም፦ ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው። የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም። መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው። ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ አይቻልም።
ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው። ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች። ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው።
•➢ "ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው። እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም።
ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች። እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና። ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው። ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት።
•➢ ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል። የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ። ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ። የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል።

✝️ በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን።
ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት_በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን። ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን።