TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
የዘላለም ✞ ሕይወት||ETERNAL LIFE

28 Jan 2024, 12:57

Open in Telegram Share Report

🍙 ክርስቶስ አንድ አካል ነው፤ ያም አካል የማይለወጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ የአምላክነት አካሉ ወይም እኔነቱ ወደ ሰውነት አካል ወይም እኔነት አልተቀየረም።እንዲሁም ሰብአዊ አካልን/እኔነትን/ አልተቀበለም።ነገር ግን የሰውነትን ባሕርይ ወይም ፍጹም ሰውነትን ወሰደ።ይሄ የሰውነት ባሕርይ በተናጠል የግል አካል አልተመሠረለትም፤ ነገር ግን በወልድ አካልነት አካሊዊ ሆነ።ከዘላለም ጀምሮ አንድ የመለኮት ባሕርይ ብቻ ይዞ አንድ አካል የነበረው የሰውነትን ባሕርይ ወሰደ፤ ስለዚህ አሁን ሁለቱም ባሕርያት አሉት።የሰውን ባሕርይ ከወሰደ በኃላ ክርስቶስ በአካሉ ወይም በእኔነቱ መለኮትነት ብቻ ሳይሆን አምላክም ሰውም ነው።ያ ማለት አሁን እርሱ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው።ክርስቶስ አንድ ነጠላ አካል ነው፤ አንድ እኔነት አለው።ነገር ግን አምላክን አምላክ የሚያሰኙትን ሁሉ እንዲሁም ሰውን ሰው የሚያሰኙት ሁሉ በሙላት ይዟል።አንድ እኔነት ይኑሮው እንጂ እኔነቱ በአምላክነቱ ሆነ በሰውነቱ ባሕርያት ያለ ነው።አካሉም ደግሞ የመለኮትና የሰውነት ፈቃድ አሉት።ክርስቶስ ሁለት እኔነት የሉትም።ነገር ሁለት ባሕርያት በአንድ እኔነት ተገልጠዋል።በንግግሩ የሚገለጠው የመለኮት ሕልውናው ወይም የሰውነት ሕልውናው ቢሆንም፥ ተናጋሪው ያው አንዱ ክርስቶስ ነው።ታድያ ማስተዋል ያለብን የሰውነትን አካል አልተቀበለም ማለት ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ አዲስ እኔነትን አላገኘም ማለት ነው።ከመጀመርያ ገና በአምላክነት ይኖር ስለነበረ፤ ሰው ከሆነም በኃላ በዚያው እኔነት ቀጥሏል።ያም እኔነት መለኮታዊ እኔነት ነው።የሰውነት እኔነቱ እራሱን የሚገልጠው በመለኮትነት እኔነቱ በኩል እንጂ በሰውነቱ ተጨማሪ የሆነ ሌላ የራሱ እኔነት የለውም።የመለኮት ባሕርዩ የማይለወጥ ስለሆነ ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ የመለኮት ባሕርዩ መሠረታዊ ለውጥ አልደረሰበትም።ስለዚህ ክርስቶስ ሁለት አካላት ወይም ሁለት እኔነቶች የሉትም ማለት ነው።ክርስቶስ የፈጸመው የደኅንነት ተግባር የአንዱ የማይነጣጠለው የክርስቶስ ተግባር ነው።ክርስቶስ ሥራውን ሁሉ ያከናወነው በሁለቱ ባሕርያቱ ነው።ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አሉት ስንል ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ነው ማለታችን ነው፤ ከዚያም አንድ አካል ነው ስንል አምላክነቱና ሰውነቱ በአንድ አካል ወይም በአንድ እኔነት ተዋሕደዋል ማለታችን ነው።ኢየሱስ ሲጸልይ፣ ሲርበው፣ ሲጠማው፣ ሲያለቅስና ሲያዝን፣ ሲበላ ሰው መሆኑን እያስመሰለ ሳይሆን የፍጹም ሰው ባሕርይ መሆናቸውን የሚያሳዩ ናቸው።አለመገለጥም አይችሉም።እርሱ ፍጹም አምላክ መሆኑ፤ ያቀረበው መስዋአቱ ዘላለማዊና እንከን አልባ እንዲሆን አድርጎታል።
@ZoeLife123
✳️✳️  @Yezelalemhiywet✳️✳️
✳️✳️  @Yezelalemhiywet✳️✳️

1.1k 0 6 7
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot