አላህ ለዋለልን ፀጋ አመስጋኞች እንሁን
አሁን ወደ ቤት እየሄድኩ ከሀይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ የሚሄደውን ታክሲ ለመሳፈር ወደ ታክሲ ተራ ስሄድ በጣም ረጅም ሰልፍ አለ። እና እዚህ ከምሰለፍ ቅርብ ስለምወርድ ለምን ወክ አላደርግም ብዬ በእግሬ ጉዞ ጀምርኩኝ።
ወደ ቶታል አከባቢ ስደርስ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከትኩኝ ጠጋ ብዬ ስመለከት አንድ ሰው መንገድ ላይ ወድቋል። በቦታው ያሉ ሰዎች ልያናግሩት ቢሞክሩም ምንም መልስ አይሰጥም፣ የሞተ ሰው ነው የሚመስለው። እዚያ የነበሩ ብዙ ሰዎች ቀስ በቀስ መበተን ጀመሩ። እዚያ የቀረነው ሶስት ሰዎች ትንፋሹን ለማየት ወደ አፉ ጠጋ ስንል ሎሊፖፕ (ባለ ዱላው ከረሜላ) አፉ ውስጥ አለ።
ከዚያ ከንፈሩን ስያንቀሰቅስ ተመለከትንና ጎንበስ ብለን ስንሰማው "ስኳር" "ስኳር" የሚል ድምፅ ሰማን። ከዚህ በፊት የዚህ ዓይነት ነገር አጋጥሞኝ ስለሚያውቅ ወደኋላ ሮጥ ብዬ ተመልሼ ካገኘሁት የጀቡና ቡና ሱቅ ትንሽ ስኳር ለምኜ ተመልሼ ወደ ሰውዬው በመሄድ ወደ አፉ ሳስጠጋለት ስኳሩን መላስ ጀመረ። ከጥቂት ሰከንዶች ብኋላ ሰውነቱ መንቀሳቀስ ጀመረ።
ከደቂቃ ብኋላ ድምፁም ትንሽ መሰማት ጀመረ። አጠገቡ ያለውን ፌስታል በእጁ እየጠቆመ ሚሪንዳ ስጡኝ አለ። ሚሪንዳውን ከፌስታል አውጥቼ ሰጠሁት። ትንሽ ቆይተን ሰውነቱ መፍታታት ሲጀምር አንሰተን በቂጡ አስቀመጥነው።
ከዚያ መውራት ጀመረ "በእጄ ከነበረኝ ብር ላይ እቺን ሚሪንዳና ሎሊፖፕ ገዝቼ እጄ ላይ የቀረኝ አስር ብር ብቻ ነው። በህይዎቴ ከሰው ገንዘብ ለምኜ አላውቅም እናም አስር ብሩ ለታክሲ ስለማይበቃኝ ከገላን ኮንዶሚኒየም በእግሬ ጉዞ ጀመርኩኝ። እየራበኝ ነበር ምግብ የምበላበት ብር ስለሌለኝ ዝም ብዬ ተጓዝኩኝ" አለን።
አስባችሁታል የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ምግብ ሳይበላ እየራበው ከገላን እስከ ጋርመንት በእግሩ ሲጓዝ። ደግሞኮ ወደየት ነው መዳረሻህ ስለው ገና አብነት ነው የምሄደው አለኝ። ለታክሲ የሚሆን ብር እንኳን ልንሰጠው ስንል በግድ ነው የተቀበለን። የሰው እጅ ማየት የማይወድ ሰው እንደሆነ በደንብ ያስታውቃል።
ታድያ ስንቶቻችን ነን አላህ ሙሉ ጤና ሰጥቶን በትርፍ ነገሮች የምናማርር? ስንቶቻችን ነን አላህ የመድሃኒት መግዣ ብር ሳያሳጣን አሳመምከን ብለን የምናማረው? ስንቶቻችን ነን ከኛ በላይ ስላሉ ሰዎች እንጂ ከኛ በታች ስላሉት የምናስበው?
"إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግና አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም"
ይላል አላህ በቁርዓኑ ላይ
ወላሂ ብዙዎቻችን አላህ የሰጠንን ፀጋ ብናውቀው ለሰከንድም ባላማረርን ነበር። አላህ ጤና የሰጠህ ወንድሜ ሆይ፣ አላህ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ያላሳጣሽ እህቴ ሆይ፣ አላህ የታክሲ ገንዘብ ያላሳጣን ሰዎች ሆይ እስኪ አልሃምዱሊላህ እንበል።
አልሃምዱሊላህ ረቢል ዓለሚን።
✍️Hassen Hidaya
በዚህ ቻናል⬇️👇
✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇
Youtube
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
Facebook page⬇️
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
ቴሌግራም⬇️👇
https://t.me/ZEKR_MENZUMA