እኔና አንቺ እኮ እናሳዝናለን
መዋደድ ታድለን መፋቀር ታድለን
መች አንድ ላይ አለን
እኔና አንቺኮ እናሳዝናለን
ፍቅርን ያህል ትንፋሽ
ሲገፋኝ ሲገፋሽ
ጨዋታውን ትረካውን ላንችልበት
የዚህን አለም ሰው አንደበት
እንዲያው ዝም ተባብለን አለን
እኔና አንቺኮ እናሳዝናለን
የነበርነው
ያነበርነው
ነጌን ብለነው የፈሪ
ቆዳችንን ፈትገነው እስካይቀረን ፍርፋሪ
እስክናልቅ እስክንጠፈጠፍ
የልጅነታችን አበባ በናፍቆታችን ሲቀጠፍ
መች ልብ አልነውና
መችልብ አልነውና
ለእናት ለአባታችን ያልታዘዘን ጉልበት
እንደጨረስነው ተነፋፍቀንበት
መች ልብ አልነውና
የአፍ ቃላት ጨርሰን ተኝተን ተቃቅፈን
ነጌ ለሚወዱን አቤት ማለት እስኪያቅተን
መች ልብ አልነውና
ከቀትር እንደሚያቃጥል
ከረሀብ ከፍቶ እንዲጥል
ናፍቆትን መች አወቅን
ናፍቆት ስንት ይፈጃል?
ያረጃል ወይስ ያስረጃል?
ይገላል ወይስ ያስገልላል?
ናፍቆት ምን ያህላል?
ነገረ ህይወትን ወይስ የሰው ሞትን?
የቀጣፊን ምላስ ወይስ የሳራን ዳስ?
የጋሽ ጥላሁንን የረዘመ ትንፋሽ?
ማንን ነው ሚያከለው?
በናፍቆት የከፋኝ በናፍቆት የከፋሽ
እኔና አንቺ እኮ እናሳዝናለን
መነፋፈቅ መርገብ
ክብራችን መለገም
የት ያደርሰን እንደሆን ባናውቀውም እንጃ
ሰው ከራስ ሲጣላ የት ይኬዳል ምልጃ
እንጃ
የመናፈቅ መቅፀፍት አልፎ ላያልፍልን ያልቅብን ይመስል ገላ ተካፈልን
ገደልነው
ቀበርነው
የኔና የአንቺ ፍቅር ዳግም እድል የለው
መቃብር አይከፍትም ኮፈንን አይቀድም
የኔና አንቺ ፍቅር ትንቢትን አይወድም
ለወሬ ለአለም አልተረፈምና ነገርና ስሙ
አረገ አይባል መላእክት አልሰሙ
የት ገባ ይባላል?
ቀረ በነበረ
በነበረ ቀረ
እንደተነፋፈቅን
እንደተጠባበቅን
በሌላ ሰው ናፍቆት እንደተቃጠረ
በሰነፍ ኮረዳ እንደተጠበጠረ
የትም ተበተነ የትም ቦታ ቀረ
መናፈቅ መፈለግ ስንት ህመም ያድላል
በስንቱ ያስውላል
በስምቱ ያስማል
በስንቱ ያስምላል
ተጠባበቅን ያልን ቀን መአልት ቢፍለቀለቅ
እኔና አንቺ ላንላቀቅ
በቀረን እንደ ሀውልት ደርቀን
እስከ ጌታ ፍርድ ቀን
ስንቱን አወጣሁኝ
ስንቱን አወረድኩኝ
ስንቱን ቀባጠርኩኝ
ናፈቅሽኝ ስንት ሆንኩኝ
ቀጥረሽኝ በቆምኩኝ
ቀጥረሽኝ በቆምኩኝ
ሰበብ በሆንኩልሽ
ቀጥራኛለች ብዬ ሸማ ባዘዝኩልሽ ለክር ሸማኔ
ቀሚስሽ እስኪደርስ ባለቀ ዘመኔ
ሰበብ በሆንሽልኝ
ቀጥራው ቀረች ብለው ሰው በኔ እስኪያማሽ
መቃብር መግባቴን አግብተሽ በሰማሽ
መናፈቅ እንደ ልጅ እያንቀለቀለኝ
እንደሽማግሌ በቀን የገደለኝ
እንደ ጠዋት ፀሀይ አሰኘኝ ልሞቅሽ
እንደ ህይወት ስለት ስለቴ ባረግሽ
እንደ እናት ምርቃት ባልኩሽ አሜን አሜን
አቤት ስል በኖርኩኝ ሆነሽ ቅፅል ስሜን
ናፈቅሽኝ
።።
።።። ኤሊያስ
መዋደድ ታድለን መፋቀር ታድለን
መች አንድ ላይ አለን
እኔና አንቺኮ እናሳዝናለን
ፍቅርን ያህል ትንፋሽ
ሲገፋኝ ሲገፋሽ
ጨዋታውን ትረካውን ላንችልበት
የዚህን አለም ሰው አንደበት
እንዲያው ዝም ተባብለን አለን
እኔና አንቺኮ እናሳዝናለን
የነበርነው
ያነበርነው
ነጌን ብለነው የፈሪ
ቆዳችንን ፈትገነው እስካይቀረን ፍርፋሪ
እስክናልቅ እስክንጠፈጠፍ
የልጅነታችን አበባ በናፍቆታችን ሲቀጠፍ
መች ልብ አልነውና
መችልብ አልነውና
ለእናት ለአባታችን ያልታዘዘን ጉልበት
እንደጨረስነው ተነፋፍቀንበት
መች ልብ አልነውና
የአፍ ቃላት ጨርሰን ተኝተን ተቃቅፈን
ነጌ ለሚወዱን አቤት ማለት እስኪያቅተን
መች ልብ አልነውና
ከቀትር እንደሚያቃጥል
ከረሀብ ከፍቶ እንዲጥል
ናፍቆትን መች አወቅን
ናፍቆት ስንት ይፈጃል?
ያረጃል ወይስ ያስረጃል?
ይገላል ወይስ ያስገልላል?
ናፍቆት ምን ያህላል?
ነገረ ህይወትን ወይስ የሰው ሞትን?
የቀጣፊን ምላስ ወይስ የሳራን ዳስ?
የጋሽ ጥላሁንን የረዘመ ትንፋሽ?
ማንን ነው ሚያከለው?
በናፍቆት የከፋኝ በናፍቆት የከፋሽ
እኔና አንቺ እኮ እናሳዝናለን
መነፋፈቅ መርገብ
ክብራችን መለገም
የት ያደርሰን እንደሆን ባናውቀውም እንጃ
ሰው ከራስ ሲጣላ የት ይኬዳል ምልጃ
እንጃ
የመናፈቅ መቅፀፍት አልፎ ላያልፍልን ያልቅብን ይመስል ገላ ተካፈልን
ገደልነው
ቀበርነው
የኔና የአንቺ ፍቅር ዳግም እድል የለው
መቃብር አይከፍትም ኮፈንን አይቀድም
የኔና አንቺ ፍቅር ትንቢትን አይወድም
ለወሬ ለአለም አልተረፈምና ነገርና ስሙ
አረገ አይባል መላእክት አልሰሙ
የት ገባ ይባላል?
ቀረ በነበረ
በነበረ ቀረ
እንደተነፋፈቅን
እንደተጠባበቅን
በሌላ ሰው ናፍቆት እንደተቃጠረ
በሰነፍ ኮረዳ እንደተጠበጠረ
የትም ተበተነ የትም ቦታ ቀረ
መናፈቅ መፈለግ ስንት ህመም ያድላል
በስንቱ ያስውላል
በስምቱ ያስማል
በስንቱ ያስምላል
ተጠባበቅን ያልን ቀን መአልት ቢፍለቀለቅ
እኔና አንቺ ላንላቀቅ
በቀረን እንደ ሀውልት ደርቀን
እስከ ጌታ ፍርድ ቀን
ስንቱን አወጣሁኝ
ስንቱን አወረድኩኝ
ስንቱን ቀባጠርኩኝ
ናፈቅሽኝ ስንት ሆንኩኝ
ቀጥረሽኝ በቆምኩኝ
ቀጥረሽኝ በቆምኩኝ
ሰበብ በሆንኩልሽ
ቀጥራኛለች ብዬ ሸማ ባዘዝኩልሽ ለክር ሸማኔ
ቀሚስሽ እስኪደርስ ባለቀ ዘመኔ
ሰበብ በሆንሽልኝ
ቀጥራው ቀረች ብለው ሰው በኔ እስኪያማሽ
መቃብር መግባቴን አግብተሽ በሰማሽ
መናፈቅ እንደ ልጅ እያንቀለቀለኝ
እንደሽማግሌ በቀን የገደለኝ
እንደ ጠዋት ፀሀይ አሰኘኝ ልሞቅሽ
እንደ ህይወት ስለት ስለቴ ባረግሽ
እንደ እናት ምርቃት ባልኩሽ አሜን አሜን
አቤት ስል በኖርኩኝ ሆነሽ ቅፅል ስሜን
ናፈቅሽኝ
።።
።።። ኤሊያስ