መንሀጅ ፊርቀቱ ናጅያ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ወርቃማ ንግግሮችና አጫጭር የኦለሞችን ንግግር እንድሁም የነብዩን ﷺ ሶሒህ ሀድሶች ለማግኘት ይቀላቀሉ
ያልተመቸወት ነገር ካለ ወይም አስተያየት ካለወት በዚህ ያስፍሩልን
👇
👉 @Abdu_rehim_seid_bot 👈
👆
https://t.me/+vHPSKL9cFyxhNTY0
منهاج اهل السنة والجماعة

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




ከኢባዳ ሁሉ በላጩ ዋጂብ የሆነው ነው

قال عمر بن الخطاب رضي الله عنه:

*"لأن أشهد صلاة الصبح في جماعة أحب إلي من أن أقوم ليلة"*


📓[الأستذكار ( ٢/١٤٧) ].

https://t.me/abdu_rehim_seid


ልብ በል!!!


قال ابن القيم - رحمه الله (ت٧٥۱هــ) :
ومن الكبائر : الفرح بأذى المسلمين ، والشماتة بمصيبتهم

ሙስሊሞች አዛ ሲደርስባቸውና መከራ ሲነከቻው መደሰት ከትላልቅ ወንጀሎች ነው


ኢብኑል ቀዪም

#مدارج السالكين [٤۰٢/۱]

t.me/Abdu_rehim_seid


ለጥቆማ 👉@Abdu_rehim_seid_bot


قال الامام_مقبل_الوادعي رحمه الله-:

المرأة_لصالحة لا ترضى بأن يفضلها زوجها على ابويه الصالحين.

  المصدر: الـرِّحلَة_الأَخـِيرَة ص ٢


ደግ ጥሩ የሆነች ሚስት ባሏ ደጋግ ከሆኑ
ወላጆቹ  ሊያስበልጣት አትፈልግም


አልኢማም ሙቅቢል አልዋዲዒ الله ይዘንላቸው


ጥሩ ሴት ከመሆንሽ ምልክቶቹ አንዱ  ይህ ነው


@Abdu_rehim_seid


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
كيف حالكم?
በአንዳንድ ነገሮች ምክንያት ጠፍተን ከርመን ነበር. ከረጅም ጊዜ በኋላ ተመልሰን መጥተናል...... إن شاء الله ከአሁን በኋላ ልክ እንደ ድሮው የምንቀጥር ይሆናል።

የሚለቀቁትን ነገሮች #ሸር ማድረግ እንዳይረሳ


🌙🌙ዒድ ሙባረክ🌙🌙
🌙تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🌙
وعيد مبارك
أعاده الله عليكم وأنتم في صحة وعافية وإيمان

🌙እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል_ኣድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌙

በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እየተመኘን
ሁሌም በኢማን እና በአፊያ ጠብቆ እንዲያደርሳችሁ አላህን እንለምነዋለን።


  .            🌙عيد مبارك🌙
🌙EID MUBAREK🌙
                🌙ዒድ ሙባረክ🌙

🌠🌠🌠🌠🌠
🌠
🌠🌠🌠🌠🌠
🌠
🌠🌠🌠🌠🌠

    
🌠🌠🌠🌠🌠
           🌠
           🌠
           🌠
🌠🌠🌠🌠🌠


🌠🌠🌠🌠🌠
     🌠                 🌠
     🌠                    🌠
     🌠                       🌠
     🌠                     🌠
     🌠                 🌠
🌠🌠🌠🌠🌠


  MUBAREK


Forward from: መንሀጅ ፊርቀቱ ናጅያ
ከ"ሸዋል 6 ቀኖችን መጾም" በተመለከተ ጥቅል ጥቆማዎች‼
=======================================
①:  ከወርሃ ሸዋል 6 ቀናትን መጾሙ ሱንና ነው።
"ረመዳንን የጾመ፣ ከዚያም ከሸዋል 6 (ቀናትን) ያስከተለው:
አመቱን እንደመጾም ይሆናል።"
[ሙስሊም: 1984፣ 2/822
ሸርሑ ነወዊይ የሙስሊም: 8/56
አቡ ዳውድ: 2433
ቲርሚዚይ: 1164
አሕመድ: 5/417
ነሳኢይና ኢብኑ ማጃህም ዘግበውታል።]
ስለዚህ እንፁም።
መፆሙ ይጠላል የሚሉ አሉ።
ግን ትክክል አይደለም።
[ለጂነቲ ዳኢማህ: 10/389 ላይ ተመልከቱ።]

②: መቼ መጀመሩ ይበልጣል?
====================
በዒድ ማግስት ማለትም ሸዋል 2 መጀመሩ ይበልጣል።
ስለዚህ ነገ እንጀምር።
ከነም ውጭ መጀመሩ እንዳለ ሁኖ‼
[ለጂነቲ ዳኢማህ: 10/391 ላይ ተመልከቱ።]

③: በተከታታይ መፆሙ ይሻላል?
=====================
አዎ! በተከታታይ መፆሙ ይበልጣል። ወደ ኸይር ነገር መሽቀዳደም ስላለብን።
ወሩ እስካላለቀ ድረስ አፈራርቆ መፆሙ ፍቁድ መሆኑ እንዳለ ሁኖ‼
[ለጂነቲ ዳኢማህ: 10/381፣
ፈታዋ ኢብኑ ዑሠይሚን: ኪታቡ ዳዕዋህ: 1/52–53፣
ሶሒሑ ተርጉብ ወት’ተርሂብ: 1/421፣
መጅሙዑል ፈታዋ የኢብኑ ባዝ: 15/390–391 ላይ ተመልከቱ።]

④: ከረመዳን ቀዷ ያለበት እንደት ያድርግ?
===========================
የሸዋል ወር ሳያልቅበት ከረመዳን ያለበትን ቀዷውን ለማውጣት ከቻለ፣
የሸዋልን ከመፆሙ በፊት ቀዷውን ያውጣ።
ምክንያቱም ሐዱሡ የሚለው "ረመዳንን የፆመ፣ ከሸዋል 6 ያስከተለ" ስለሆነ‼
የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰው "ረመዳን ጹሟል!" ሳይሆን የሚባለው፣
"ከረመዳን ጹሟል!" ነው የሙባለው ስላላሟላ።
ስለዚህ ቀዷውን ያስቀድም።
[ መጅሙዑል ፈታዋ የኢብኑ ባዝ: 15/392፣
ሀይተሚ: ቱሕፈቱል ሙሕታጅ: 3/457 ላይ፣
ኡብኑ ሙፍሊሕ: አል ፉሩዕ: 3/108 ላይ፣
እና ሌሎችንም ተመልከቱ።]

ለሌችም መልዕክቱን ብታስተላልፉት መልካም ነው።


@Abdu_rehim_seid
@Abdu_rehim_seid
https://t.me/abdu_rehim_seid/1813


እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ

عيد مبارك!

تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال!


ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን!
الله ከኛም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን!


ጨረቃ ባለመታየቷ ኢድ እሮብ መሆኑ ተረጋግጧል።


Forward from: መንሀጅ ፊርቀቱ ናጅያ
​​★﷽★
☞ለይለቱል ቀድር

﴿لَیۡلَةُ ٱلۡقَدۡرِ خَیۡرࣱ مِّنۡ أَلۡفِ شَهۡرࣲ﴾ القدر ٣

ለይለቱል ቀድር ከ አንድ ሺህ ወር ትበልጣለች

قَالَ الْمُفَسِّرُونَ: مَعْنَاهُ: عَمَلٌ صَالِحٌ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ خَيْرٌ مَنْ عَمِلِ أَلْفِ شَهْرٍ لَيْسَ فِيهَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ

📮 ይህም ማለት ሙፈሲሮች እደገለፁት ትርጉሙ< መልካም ስራ በለይለተል ቀድር ከሚሰራውና ለይለተል ቀድር ከሌለባቸው ሌሊቶች ከሚሰራው መልካም ስራ በ አንድ ሺ ወር ይበልጣል ማለት ነው>

📙📔📗 تفسير البغوي


﴿لَیۡلَةُ ٱلۡقَدۡرِ خَیۡرࣱ مِّنۡ أَلۡفِ شَهۡرࣲ﴾ القدر ٣

ለይለቱል ቀድር ከ አንድ ሺህ ወር ትበልጣለች

والمراد بالخيريَّة هنا ثوابُ العملِ فيها، وما يُنْزِل الله تعالى فيها من الخير والبركة على هذه الأُمَّة

📭 በላጭ ( ኸይር) ነች ሲባል በዚህ አያ የተፈለገው የስራ ምንዳ ነው በዚህችም ኡማ الله የሚያወርደው ኸይር በረካንም ጭምር ነው

📗📘📕 تفسير بن عثيمين رحمه الله

🎁 ምን ያህል ለዚህች ለይል ታጠቀሀል??


عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ :

አቡ ሑረይራ رضي الله عنه ባስተላለው ሀዲስ ረሱል ﷺ እደዚህ ብለዋል

" مَنْ قَامَ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا ، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ، وَمَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ "

🪞 የለይለተል ቀድርን አምኖ እና ከ الله ምንዳን ፈልጎ የቆመ ( የሰገደ) ያሳለፈው ወንጀሉን ይማርለታል፣ የረመዷንን ወር አምኖ ከ الله ምንዳን ፈልጎ የፆመ ያሳለፈውን ወንጀሉን ይማርለታል።

📔📙📘 صحيح البخاري

📦 ለይለተል ቀድር ካጋጠመን የምናደርገው ዚክር👇

عَنْ عَائِشَةَ قَالَتْ : قُلْتُ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَرَأَيْتَ إِنْ عَلِمْتُ أَيُّ لَيْلَةٍ لَيْلَةُ الْقَدْرِ، مَا أَقُولُ فِيهَا ؟ قَالَ :
" قُولِي : اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ ؛ فَاعْفُ عَنِّي "

هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ

📙📒 سنن الترمذي


አሕሉ ሱና

من أول من استخدم مصطلح أهل السنة والجماعة؟

☞ይህንን ስያሜ አሕሉ ሱና ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው ማነው??

① አብዱሏህ ኢብኑ አባስ


كما روي عنه في تفسير قوله تعالى
يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ اسْوَدَّتْ وُجُوهُهُمْ أَكَفَرْتُم بَعْدَ إِيمَانِكُمْ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

ፊቶች የሚያበሩበት እንዲሁም ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን

እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ካመናችሁ  በኋላ ካዳችሁን ትክዱበት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ ይባላሉ

ይህን አንቀፅ ሲያብራራ ምን አለ?

↩فأما الذين ابيضت وجوههم: فأهل السنة والجماعة وأولو العلم

እነዚሃ ፊታቸው የሚያበሩት አሕሉ ሱናዎች እና የእውቀት ባለቤቶች  ናቸው ይላል

↩ 
وأما الذين اسودت وجوههم: فأهل البدع والضلالة

እነዚያ ፊታቸው የሚጠቁሩት ደግሞ የቢድኣ እና የጥመት ባለቤቶች ናቸው።

📕 تفسير ابن كثير

② ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን

قال إمام مسلم حَدَّثَنَا  أَبُو جَعْفَرٍ مُحَمَّدُ بْنُ الصَّبَّاحِ ، حَدَّثَنَا  إِسْمَاعِيلُ بْنُ زَكَرِيَّاءَ ، عَنْ  عَاصِمٍ الْأَحْوَلِ ، عَنِ  ابْنِ سِيرِينَ  قَالَ : لَمْ يَكُونُوا يَسْأَلُونَ عَنِ الْإِسْنَادِ، فَلَمَّا وَقَعَتِ الْفِتْنَةُ قَالُوا : سَمُّوا لَنَا رِجَالَكُمْ، فَيُنْظَرُ إِلَى أَهْلِ السُّنَّةِ فَيُؤْخَذُ حَدِيثُهُمْ، وَيُنْظَرُ إِلَى أَهْلِ الْبِدَعِ فَلَا يُؤْخَذُ حَدِيثُهُمْ.

📘مقدمة صحيح مسلم

ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን እደዚህ ብሎዋል

ፊትና እስከተከሰተበት ጊዜ ድረስ ስለ ሀዲስ ሰንሰለት የሚጠይቁ አነበሩም ልክ ፊትና ሲፈጠር የናንተን የሀዲስ ሪጃሎቻችሁን ሰይሙልን አሉ።

ወደ አሕሉ ሱና ምልከታ ቢደረግ ሀዲሳቸው ተቀባይነት አለው።

ወደ ቢድአ ባለቤቶች ቢታይ ሀዲሳቸው ተቀባይነት አያገኝም።

③ አዩብ ኢብኑ አቢ ተሚማ አሰ ኽቲያኒይ

قال أيوب  إني أُخبر بموت الرجل من أهل السنة وكأني أفقد بعض أعضائي .

📗 اللالكائي : 1/60/29

እኔ የአንድን የሱና ባለቤት መሞቱ ሲነገረኝ
ልክ ከሰውነቴ አንዱን ክፍል ያጣሁኝ ያሕል ይሰማኛል

በዚህ ጉዳይ ላይ አሻኢራዎች ለመጀመሪያ  ጊዜ እደተጠቀሙት ተደርጎ የሚወራው ለእውነት የራቀ ነው አቡል ሀሰን አል አሽአሪ ከመወለዱ በፊት ኢብኑ አባስ ተጠቅሞታል።

من محاضرة فضلة الشيخ محمد بن مانع شفاه الله وحفظه

والله أعلم،


#መህዲ በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል።

ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››
(አቡ-ዳውድ 4282)

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል።
(አቡ-ዳወድ 11/373)

አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።
(አቡ-ዳውድ 4265)

መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።
(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49)

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።
(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)

መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።
(አል-ቂያማህ አስ-ሱግራ 275)

መህዲ ታላቅ ጦርነት አድርጎ ሙስሊሞችን የበላይ ቢያደርግም ጊዜው የቂያማህ ቀን መቃረቢያ በመሆኑ ከባባዶቹ ፊትናዎች ይከሰታሉ። ከእነዚህም መካከል ቀዳሚው የደጃል መነሳት ነው። እሱን ተከትለው የዕጁጅና መዕጁጆች ከጉድጓዳቸው ይወጣሉ። በዚህ ጊዜ አላህ ዒሳን (ዐሰ) ለእርዳታ ይልከዋል።

በሐዲስ እንደተጠቀሰው ዒሳ (ዐሰ) ወደ ምድር የሚወርደው በፈጅር ሰላት ወቅት ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) ስናገሩ ‹‹መህዲ ዒሳን አሰግደን ይለዋል። ዒሳም እናንተ መሪዎች መሆናችሁ ከቂያማህ ምልክቱ ነውና አንተ አሰግደን ይለዋል። ዒሳም ከመህዲ ኋላ ተከትሎ ይሰግዳል።›› ብለዋል።
(ሙስሊም 225)

ከዚያ በኋላ ዒሳ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን የዕጁጆችንና ደጃልን በመጋደል በአላህ ዕርዳታ ያጠፋቸዋል። ነቢዩ (ዐሰወ) እንደተናገሩት ‹‹ሙስሊሞች ለሰባት ዓመታት ያህል የየዕጁጆችን አጥንት ቀስትና ጋሻ ለማገዶነት ይጠቀሙበታል።

መህዲ በኸሊፋነት የሚቆይባቸው ዓመታት ‹‹ሰባት›› እንደሆኑ አብዛኛዎቹ የሐዲስ ምሁራን ይናገራሉ። ከእነሱ መካከል አንዱ የኢብኑ ማጃህ ሲሆኑ ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ ሰባት አጭር ጊዜያትን ይቆያል።›› ማለታቸውን ዘግበዋል።
(ኢብን ማጃህ 4039)

አል-መህዲ እስኪመጣ ሙስሊሙ ጂሐድን በመተው መጠበቅ ይኖርበታል? ለሚለው ጥያቄ ሸይህ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ በፈትዋ ገፃቸው እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ከጂሐድ መዘንጋት ከከባባድ ወንጀሎች አንዱ ነው። አላህ ያዘዘው ሁሉም የራሱን ግዴታ እንዲሞላ ነው። መህዲ የራሱ ጂሐድ አለው። ይሄም ህዝብ የራሱን ጂሐድ ማድረግ ግዴታው ነው።

#አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-

وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ كُلُّهُ لِلَّهِ ۚ فَإِنِ انتَهَوْا فَإِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
[ ሱረቱ አል-አንፋል - 39 ]


🔴🔴የቤት ፈረሳ🔴🔴🔴

ቤት የፈረሰባቹህ ወንድሞችና እህቶች
አትዘኑ 

ለሞሮኮያዊንና ለሊቢያዊያን የደረሰባቸው ሲታይ የናንተው በጣም ቀላል ነው

ቤት ፈርሶ እናንተ ድናቹሀል


ሊቢያዊያን ባህር መጥቶ እነሱም ቤቶቻቸውም
አንድላይ ይዟቸው ሄዷል


ሞሮኮያዊያን ከነ ቤቶቻቸው አብረው ጠፍተዋል


አቡ መርየም


ደጃል መካ እና መድና አይገባም።


◾️ በድን ውስጥ ጥሩ ቢድዓ የሚባል ነገር የለም፤ በል እንደውም ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው። ሁሉም የተወገዘ ነው።

والنبي ﷺ قال: «كل بدعة ضلالة» فلا يجوز لأحد من المسلمين أن يقول: إن في البدع شيئًا حسنًا، والرسول ﷺ يقول: « كل بدعة ضلالة» لأن هذه مناقضة ومحادة للرسول ﷺ، وقد ثبت عنه أنه قال: «كل بدعة ضلالة» فلا يجوز لنا أن نقول خلاف قوله -عليه الصلاة والسلام

◾️ ነብዩ ﷺ " ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው" ብለዋል።  ለአንድ ሙስሊም ለሆነ ሰው "የቢድዓ ጥሩ አለው" ሊል አይቻልለትም። ይህ መልዕክተኛውን መቃወም ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ  "ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው" ማለታቸው ተረጋግጧልና።

◽️ የነብዩን ﷺ ንግግር ኸልፈን(ተቃርነን) ልንናገር አይፈቀድልንም።

وما يظنه بعض الناس أنه بدعة وهو مما جاء به الشرع فليس بدعة مثل كتابة المصاحف، مثل التراويح ليست بدع كل هذه مشروعة، فتسميتها بدعة لا أصل لذلك،

◽️ አንዳንድ ሰወች ደግሞ አድስ ነገር ሆኖ ( ሸሪዓ ያመጣው ነገር ነው)  እንጅ ቢድዓ አይደለም። ልክ ቁርዓን እንደመፃፍ፣ ልክ እንደተራዊሕ (እነዚህ የተደነገጉ ናቸው።) ይቺን ቢድዓ ነው ብሎ መሰየም መሰረት የለውም።

وأما ما يروى عن عمر أنه قال في التراويح:

«نعمت البدعة» فالمراد بهذا من جهة اللغة لا ليس من جهة الدين، ثم قول عمر لا يناقض ما قاله الرسول ﷺ ولا يخالفه قول الرسول مقدم -عليه الصلاة والسلام- لأنه قال: «كل بدعة ضلالة» قال: وإياكم ومحدثات الأمور وقال ﷺ في خطبة الجمعة: أما بعد فإن خير الحديث كتاب الله، وخير الهدي هدي محمد ﷺ، وشر الأمور محدثاتها، وكل بدعة ضلالة هذا حكمه -عليه الصلاة والسلام-، رواه مسلم في الصحيح.

🔘  ከዑመር (الله ስራቸውን ይውደድላቸውና)  በተራዊሕ ጉዳይ ላይ እንድህ ብለዋል:- "የቢድዓ ጥሩ"
ይህ የተፈለገበት ቋንቋዊውን ነው እንጅ ሸሪአዊውን ቢድአ አይደለም።

🔘 የኡመር ንግግር የረሱልን ጋር አይጋጭም፤  የነብዩ ﷺ ንግግር ከሁሉም ንግግር በፊት ይቀደማል። እሳቸውም "ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው" ብለዋል።

🔘 የጁሙዓ ኹጥባቸው ላይ " መጤ ነገሮችን አደራችሁን" ብለዋል።

🔘 "ከዚህም በመቀጠል:- ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የالله ንግግር(ኪታብ) ነው፤ ከመመሪያወች ሁሉ በላጩ መመሪያ የሙሀመድ ﷺ መመሪያ ነው፤ ከነገሮች ሁሉ የከፋው ደግሞ አዳድስ ፈጠራወች ናቸው። ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው " ይህ ነው የረሱል ﷺ ፍርድ።

فلا يجوز لمسلم أن يخالف ما شرعه الله، ولا أن يعاند ما جاء به نبي الله -عليه الصلاة والسلام-، بل يجب عليه الخضوع لشرع الله، والكف عما نهى الله عنه من البدع والمعاصي، رزق الله الجميع الهداية، نعم

🔘 ለማንኛውም ሙስሊም الله የደነገገውን መቃረን አይፈቀድለትም

🔘 እንደውም ለالله መመሪያ መተናነስ፣ الله ከከለከለው ነገር መራቅ (ከቢድዓ ከወንጀል) በእሱ ላይ ግደታ ይሆንበታል።

………… ለሁላችንም الله ሒዳያ ይስጠን……………

ምንጭ 👇
https://t.me/abdu_rehim_seid/1625

🎙ታላቁ አሊም ኢማም አብደልአዚዝ  ኢብኑ ባዝ رحمه الله تعالى

✍ أبو نزير الأثري من هارا


🍁 …🚫መውሊድ በታላላቅ ኦለሞች 🚫…🍁 ①

السؤال:
فضيلة الشيخ عبدالعزيز، كنا في لقاء ماض قد استعرضنا رسالة وردتنا من المستمع فلاح السويد، قرية الكوز، محافظة الحسكة منطقة المالكية، وبقي له بعض الاستفسارات والأسئلة التي يمكن أن تغطي حلقة كاملة.
يقول: يا شيخ عبدالعزيز، في الاستفسار الأول:

نسألكم عن مولد النبي الأعظم ﷺ هل هو بدعة؟ وإني قد سمعت في بعض البلدان، ومن بعض العلماء يقولون: إنها بدعة حسنة، والله أعلم. 
وفقكم الله

ጥያቄ:- መውሊድ ቢድዓ ነው ወይንስ አይደለም? አንዳንድ ኦለሞች ጥሩ ቢድዓ ናት ሲሉ ሰምቻለሁ

الجواب:
بسم الله الرحمن الرحيم. 
الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على عبده ورسوله وخليله وأمينه على وحيه نبينا وإمامنا محمد بن عبدالله وعلى آله وأصحابه، ومن اهتدى بهداه، أما بعد:

الاحتفال بالموالد إنما حدث في القرون المتأخرة بعد القرون المفضلة بعد القرن الأول والثاني والثالث، وهو من البدع التي أحدثها بعض الناس استحسانًا وظنًا منه أنها طيبة، والصحيح والحق الذي عليه المحققون من أهل العلم أنها بدعة

📌 መልስ:- መውሊድ ከሦስቱ ክፍለ ዘመን በኋላ የመጣ አድስ ፈጠራ (ቢድዓ) ነው።‼️

📌 ከፊል ሰወች ይች ጥሩ ነገር ናት ብለው አስበው ካመጧቸው ቢድዓወች መካከል አንዱ ነው።

💥 ትክክለኛው እና ትክክለኛው፣ ታላላቅ የኢልም ባልተቤቶች ያሉበት  ይቺ መውሊድ የምትባለው ነገር ቢድዓ ናት የሚለው ነው።

الاحتفالات بالموالد كلها بدعة، ومن جملة ذلك الاحتفال بالمولد النبوي، ولماذا؟

🔘 የመውሊድ በዓላት ሁሉም ቢድዓ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የነብዩ መውሊድ ነው።

ምክንያቱም

لأن الرسول ﷺ لم يفعله، ولا أصحابه، ولا خلفاؤه الراشدون، ولا القرون المفضلة،كلها لم تفعل هذا الشيء

  ♦️ ነብዩ ﷺ አልሰሩትም።

  🔘 ሰሐቦችም አልሰሩትም።

  ♦️የረሱልም ምትኮች አልሰሩትም።

   🔘 ታቢዒዮች አልሰሩትም።

   ♦️ ታቢዒ ታቢዒን አልሰሩትም።

والخير في اتباعهم لا فيما أحدثه الناس بعدهم

« መልካሙ እነሱን መከተል እንጅ ከእሳቸው በኋላ የመጡ ሰወች ያመጡትን መከተል አይደለም »

ነገር ግን ከእነሱ በኋላ ያሉ ሰወች ናቸው ያመጡት

وقد ثبت عنه -عليه الصلاة والسلام- أنه قال:
 « إياكم ومحدثات » الأمور وقال -عليه الصلاة والسلام-: «وشر الأمور محدثاتها، وكل بدعة ضلالة» وقال -عليه الصلاة والسلام-:« من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد،» «من عمل عملًا ليس عليه أمرنا فهو رد»: يعني: مردود

🍁 ነብዩ ﷺ እንድህ ብለዋል
« መጤ ነገሮችን (ቢድአ) አደራችሁን»

وقال
« ሁሉም አድስ ፈጠራ ቢድዓ ነው፤ ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው »
وقال

« የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ  ያ(ስራው) ተመላሽ ነው። (ተቀባይነት የለውም) »
__
فالنبي ﷺ وضح الأمر وبين أن الحوادث في الدين منكرة، وأنه ليس لأحد أن يحدث في الدين ما لم يأذن به الله،

🔘 ነብዩ ﷺ ነገሩን ግልፅ አደረጉ፤  በድን ላይ አዳድስ መጤወች የተወገዙ እንደሆኑ ገለፁ። ማንኛውም ሰው الله ያልፈቀደውን አድስ ነገር ሊያስገባ አይገባውም።
وقد ذم الله من فعل هذا

🔘 በእርግጥም ይህንን ያደረገውን الله አውግዟል።

بقوله سبحانه: «أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ» [الشورى:٢١] 

" ፣ الله ያልፈቀደውን ድን(ሀይማኖት) የደነገጉላችው አጋር አላቸውን?"

والاحتفال أمر محدث لم يأذن به الله، ولا رسوله-عليه الصلاة والسلام-، والصحابة أفضل الناس بعد الأنبياء، وأحب الناس للنبي ﷺ
وأسرع الناس إلى كل خير،ولم يفعلوا هذا، لا أبو بكر ولا عمر ولا عثمان، ولا علي ولا بقية العشرة ولا بقية الصحابة، وهكذا التابعون، وأتباع التابعين ما فعلوا هذا، وإنما حدث من بعض الشيعة الفاطميين

📨  ኢኽቲፋል  መጤ የሆነ ነገር ነው።( اللهም ሆነ መልዕክተኛው ያልፈቀዱት ጉዳይ ነው።)

☄ ሠሐባወች ከነብያቶች ቀጥሎ ከሰወች በላጮቹ ናቸው።

☄ ነብዩ ﷺ ዘንድ ከሰወች ሁሉ የተወደዱ ሰወች ናቸው።

☄ ከሰወች ሁሉ ወደ ኸይር የሚቻኮሉ ሰወች ናቸው።

☄ ይህንን አቡበክርም ይሁን፣ ኡመርም ይሁን ፣ ኡስማንም ይሁን፣ አልይም ይሁን ፣ የቀሩት አስሮቹም በጀነት የተመሰከረላቸው ይሁሙ ሌሎችም ሰሐቦች በአጠቃላይ አልሰሩትም።

☄ እንድሁም ታቢዒዮች፣ ታቢዒ ታቢዒንም ቢሆኑ አልሰሩምትም።

☄ነገር ግን የመጣው ከከፊል ሽዓወች ማለትም ከፋጢምዮች ነው።

في مصر في المائة الرابعة كما ذكر هذا بعض المؤرخين، ثم حدث في المائة السادسة في آخرها أو في أول السابعة من ملك إربل ظن أن هذا طيب ففعل ذلك،

💥 በግብፅ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንዳንድ የታሪክ ምሁራን እንደተናገሩት ከዚያም በስድስተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ወይም በሰባተኛው ክፍለ ዘመን የኤርቢል ንጉሥ መጀመሪያ ላይ ተከሰተ እና ይህ መልካም ነው ብሎ ስላሰበ ይህንን ሰራ።

والحق أنه بدعة؛ لأنها عبادة لم يشرعها الله ، والرسول ﷺ ،قد بلغ البلاغ المبين ، ولم يكتم شيئًا مما شرعه الله، بل بلغ كل ما شرعه الله وأمر به

📌 እውነታው ግን ይህ አድስ ፈጠራ(ቢድዓ) ነው

📌 ይህ (መውሊድ) الله ያልደነገገው ኢባዳ ነው። መልዕክተኛው ﷺ ጥሩ የሆነን ማድረስ አድርሰዋል። الله የደነገገውን ነገር ምንም አልደበቀም። ( ሁሉንም الله የደነገገውን ነገር አድርሷል።)

وقال الله سبحانه: الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ [المائدة:٣]

📌« የዛሬን ቀን ድናችሁን ሞላሁላችሁ »

فالله قد أكمل الدين وأتمه، وليس في ذلك الدين الذي أكمله الله الاحتفال بالموالد، فعلم بهذا أنها بدعة منكرة، لا حسنة، وليس في الدين بدعة حسنة، بل كل البدع ضلالة كلها منكرة،

▪️ ፣الله በርግጥም ድኑን ሙሉ አድርጎታል።

◽️ በእዚህ ድን ውስጥ(الله ሙሉ ባደረገው ድን ውስጥ) መውሊድ የሚባል ነገር የለም።

◽️ በእዚህ ይህቺ የተወገዘች ቢድዓ እንጅ ጥሩ ቢድዓ አለመሆኗን እወቅ።


🌔 ሐቅ🌒

=> ሀቅ ብሎ ማለት ብዙ ሰወች የሄዱበት ወይንም ብዙ ሰወች ያሉበት ወይንም ብዙ ሰወች ትክክል ነው ብለው የመሰከሩለት አይደለም።

🔘 ሐቅ ብሎ ማለት በእሱ ላይ የቁርዓን እና የሐድስ መረጃ ያለበት ነገር ነው። 

▪️ ሀቅ ብሎ ማለት የጥንት የጧቶቹ የሄዱበት መንገድ ነው።

▫️ ሰወች በሀቅ ይመዘናሉ እንጅ ሀቅ በሰወች አይመዘንም።

◾️ ሀቅ ምንጊዜው ትኖራለች
……ሀቅ የበላይ ናት……

መንሀጅ ፊርቀቱ ናጅያ

http://t.me/Abdu_rehim_seid


‏كان الصحابي الجليل #أبوموسى_الأشعري رضي الله عنه يقول إذا فرغ من صلاته :

اللهم اغفر لي ذنبي

ويسر لي أمري

وبارك لي في رزقي

[ مصنف ابن أبي شيبة٢٩٨٦٥ ]


ዝም ያለ ነፃ ወጣ

20 last posts shown.