Forward from: ☞በወሎ ሐራ☆الدعوة السلفية☜
ኡሙ ዐብዲላህ ዓኢሻህ አልዋዲዒያ ማን ናት?
ኡሙ ዐብዲላህ ዓኢሻ፣ እባላለሁ። የኢማሙ፣ የሱናው አዳሽ፣ የቢድዐው ቆራጭ፣ ሸይኽ ሙቅቢል ብኑ ሃዲ አልዋዲዒ ረሒመሁላህ ልጅ።
የተወለድኩት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከተማ መዲና ሲሆን፣ እዛ ግን አልኖርኩም።
የኖርኩት እና ያደግኩት ሀገሬ ደማጅ ነው። በዒልም ቤት ውስጥ፣ በዲናዊ እና እውቀታዊ ቤት ነው ያደግኩት። ለእውቀት እንጂ ለሌላ ነገር እራሳችንን አናነሳም።
ከልጅነቴ ጀምሬ -ምስጋና ለአላህ የተገባ ሁኖ- እውቀትን መፈለግ ጀመርኩ። ማንበብና መፃፍን ከተከበረው አባቴ እጅ ተማርኩ። እንዲሁም ከግብፅ እና ከሱዳን እውቀትን ለመፈለግ የመጡ አንዳንድ የአባቴ ሴት ተማሪዎች ያስተምሩን ነበር። ቅዱስ ቁርኣንንም ከተጅዊድ መርሆች ጋር ተምሪያለሁ። እንደ ‘ሪያዱ ሷሊሒን’ እና ‘ዑምደቱል አሕካም’ የመሰሉ መትኖችን ሐፈዝኩ።
ከዚያም በአደባባይ የሚሰጡ የአባቴ ትምህርቶች ሄድኩኝ - ረሒመሁላህ። የተገለለ ከሆነው የሴቶች ቦታ ላይ ሆኜ እከታተላለሁ። አንዳንዴ እኔ ብቻ እገኛለሁ። ከኔ ውጭ ሌላ ማንም አይገኝም።
አባቴ ረሒመሁላህ፣ እኔን ስርአት ለማስያዝ፣ ለማስተማር እና ለማመላከት ከፍተኛ ትኩረት ነበረው፣ የተለያዩ ምርምሮችን ያስተዋውቀኛል።
ሐዲሥ እና የሐዲሥ እውቀቶችን በአባቴ እጅ ወሰድኩ፣ “ሙኽተሶሩ ዑሉሚል ሐዲሥ” ኢብኑ ከሢር፣ “ተድሪቡ አርራዊ” ሱዩጢ፣ እና “ጛረቱል ፈስል ዐለል ሙዕተዲነ ዐላ ኩቱቢል ዒለል” የአባቴ ተምሪያለሁ። አልሐምዱ ሊላህ።
እንዲሁም የኢብኑ ሐጀር “ኑዝሃቱ ነዞር”፣ እና የኢብኑ ረጀብ “ሸርሑ ዒለሊ ቲርሚዚ” ደማጅ በሚገኙ መሻይኾች ወስጃለሁ።
ታሪክና ሲራን ከአባቴ ተምሪያለሁ: “አሶሒሑል ሙስነድ ሚን ደላኢሊ ኑቡዋ” በግልም በአደባባይም እከታተላለሁ። “ሶሒሑል ቡኻሪ”ን አባቴ ከቤት ብቻየንና ከመስጂዱ ሚንበር ላይ ሆኖ በሚያስተምረው ደርስ ላይ ተምሪያለሁ።
ተውሒድ እና ዐቂዳን አባቴ በአደባባይ ከሚሰጣቸው ትምርቶች እከታተል ነበር፡ “አልጃሚዑ ሶሒሕ ፊል ቀደር” እና “አሽሸፋዐህ” ሁለቱም የአባቴ ናቸው ረሒመሁላህ። የኢብኑ ኹዘይማህ “ተውሒዱል አስማእ ወሲፋት” እና የዐብዱላህ ብኑ አሕመድ “አስሱና” ተከታትያለሁ። እነዚህ በአደባባይ ለሁሉም የሚሰጡ ትምህርቶች ነበሩ።
“አተድሙሪያህ”፣ “ፈትወል ሐመዊያ”፣ “አልኢማኑል አውሰጥ” የሸይኹል ኢስላም፣ “ሸርሑል ዐቂደቲ ጦሓዊያ” የኢብኑ አቢል ዒዝ እና “ፈትሑል መጂድ ሸርሑ ኪታቢ ተውሒድ” በአንዳንድ የአገሪቱ ሸይኾች ተከታትያለሁ። ...
በነሕው ደግሞ፦ “አቱሕፈቱ ሰኒያ”፣ “ሙተሚመቱል አጁርሩሚያ”፣ “ሸርሑ ቀጥሪ ነዳ”፣ እና “ሸርሑ ኢብኒ ዐቂል”። ሁሉንም የተማርኩት በአባቴ እጅ ነው - ረሒመሁላህ።
ከቁርአን ማስረጃዎች፣ ምሳሌዎችና ግጥሞች በእኛ ላይ ሲያልፉ ኢዕራብ እንዳደርግ ያዘኝ ነበር። የኢብኑ ማሊክን “አልፊየቱ ብኒ ማሊክ” በቃሌ ሸምድጃለሁ - ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። ከአባቴ ከፍተኛ ትኩረት የተነሳ የነሕው እውቀትን ወደድን።
በፊቅህ እና በሐዲሥ የአባቴን ትምርቶች እከታተል ነበር።
“ሶሒሑል ቡኻሪ”፣ “ሶሒሕ ሙስሊም” “አሶሒሑል ሙስነድ ሚማ ለይሰ ፊ ሶሒሐይን” የአባቴን እከታተል ነበር።
ከፊቅህ መርሆዎች፦ “አልኡሱል ሚን ዒልሚል ኡሱል”፣ “አልወረቃት”፣ “አርሪሳላ” የኢማሙ ሻፊዒይን በአንዳንድ የሀገሪቱ ሸይኾች ላይ ተምሪያለሁ።
ከተፍሲር፦ “ተፍሲሩል ሐፊዝ ኢብኒ ከሢር” እና “አሶሒሑል ሙስነድ ሚን አስባቢ ኑዙል” ከአባቴ የአደባባይ ትምርቶች ይዣለሁ።
“ሙቀዲመቱን ፊ ኡሱሊ ተፍሲር” የሸይኹል ኢስላምን በከፊል የአገሪቱ ሸይኾች ተምሪያለሁ።
አባቴ በእውቀት ፍለጋ ላይ እጅግ በጣም ከማበረታቱ የተነሳ ከሐፊዞች እንደምሆን ይሰማኝ ነበር = ግን አላህ አልወሰነልኝም።
ይህ ከፊል አላህ ያገራልኝ ነገር ነው፤ እውቀትም ቀላል ነው። ጥራት የተገባው ጌታችንም፦ {ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?} ብሏል። [አልቀመር፡ 17]
አባቴም ረሒመሁላህ “አልጃሚዑ ሶሒሕ ፊል ዒልሚ ወፈድሊህ” በሚለው ኪታቤ መግቢያ ላይ እንዲህ ሲል አወድሶኛል፦ “ኡሙ ዐብዲላህ አልዋዲዒያህማ እህቶቿን ዐቂዳ፣ ቁርኣን፣ ሐዲሥ እና ነሕው በማስተማር ላይ የቆመች ናት - አላህ ይጠብቃት። እንዲሁም እህቶቿ ከተለያዩ የየመን ሀገሮች የሚጠይቋቸውን ጥያቄዎች በደረሱላት ደብዳቤ መሰረት በመመለስ ላይ የቆመች ናት።
ከመማር፣ ከማስተማር እና ከመፃፍ በስተቀር አንገቷን አታነሳም። “አሶሒሑል ሙስነድ ፊ ሸማኢል ሙሐመድያ” የተሰኘው መፅሃፏ ሊታተም ነው። አላህ፡ እንዲመራት፣ በነቢያዊ ሱንና አገልግሎት ላይ እንድትቀጥል እንዲያመቻችላት፣ ወደ መልክተኛው ሱናም መጣራትን፣ እንዲያገራላትና፣ ከዱንያ እና ከሞት ፈተና እንዲጠብቃት እለምነዋለሁ፤ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።”
“ነሲሐቲ ሊንኒሳእ” በሚለው ኪታብ መግቢያ ላይም፦ “በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ላይ ተጠቃሚ ነች፣ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስነምግባር የተማረች፣ ጨዋና ጊዜዋን አጥብቃ የምትጠብቅ ናት። በዚህም ምክንያት አላህ እውቀቷን ባርኮላታል። እህቶቿን በማስተማር ላይ ትጉ ናት። አንድን ኪታብ እስከመጨረሻው ታስተምራለች ከዚያም ወደ ሌላ ኪታብ ትዘዋወራለች። የዐቂዳ፣ የፊቅህና የቋንቋ ኪታቦችን ወዳድ ናት።” ሲል አሞካሽቶኛል።
ከልጅነቴ እስከ ትልቅነቴ እያስተማርኩ ነኝ። በልጅነቴ ማንበብን፣ መፃፍን፣ ቁርኣንን እና አንዳንድ መትኖችን በማስሓፈዝ አስተምር ነበር፣ አላህ አድሎን በደማጅ ሴቶችን በማስተማር እስከምቆም ድረስ።
ከአባቴ ከተጠቀምኳቸው መርሆዎችና ስምሪቶች ውስጥ፦
• በሰለፎች አረዳድ መሰረት ማስረጃን ለመቀበል ዝግጁ መሆንና ጭፍን ተከታይነትን ማስወገድ።
• ሐቅ በሰው አይታወቅም፣ ነገር ግን ሰዎች የሚታወቁት በሐቅ ነው።
• ወደ እውቀት ሙሉ ለሙሉ መዞር። ንግስና፣ ዱንያ በጠቅላላዋም ብትሆን ከእውቀት የበለጠ ከፍ ያለ ወይም የሚያስደስት ምንም ነገር እንደሌለ።
• መለያየትንና እና ሒዝቢይነትን መጥላት።
• በማይጠቅም ነገር ላይ ክርክርን መተው።
• በተቻለ መጠን ከሚያባትሉ ነገሮች መራቅ እና እራስን ለእውቀት ፍለጋ መስጠት።
• ጊዜን መቆጠብ፣ ጊዜን እውቀትን በመፈለግና በዒባዳ ማሳመር።
...
ድክመታችንን እና አቅመ ቢስነታችንን፣ ምንም እንዳላደለንም እናውቃለን፣ ቀጣይነት ያለ፞ው ስኬትንና ከችሮታው ማብዛትን፣ እንዲጠቅመንና በረካውንም እንዲለግሰን ጌታችንን እንለምናለን።
🖋 ኡሙ ዐብዲላህ ዓኢሻህ ቢንት ሸይኽ ሙቅቢል ረሒመሁላህ || ጁማደል ኡላ 19/1437
https://t.me/selefyakuta
https://t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed/5341