Forward from: Semir Jemal
ከምን ጊዜውም በላይ የሰለፊዮችን አንድነት ማጠናከር ያስፈልጋል!
ክፍል 6
በክፍል አምስት ላይ የአል-ዋሊድ፣ ሸይኽ፣ዶኮተር፣ ፕሮፌሰር፣ አል-ዐላመህ፣ አል-ዋሊድ ረቢዕ ብን ሃዲ አላህ ፍፃሜያቸውን ያሳምርላቸውና...ከተለያዩ ከዓለማችን ክፍል፡ ከኢንግላንድ፣ከማልዲቭ፣ ከአሜሪካ፣ ከሲንጋፖር፣ ከሕንድ...በሀገረ መዲና ሸይኹ ጋር በተሰበሰቡበት ድንቅ የሆነን ምክር መለገሳቸውን በጥቂቱ ለማስታወስ ሞክሬ ነበር። ለማስታወስ ያክል ከሸይኹ ወርቃማ ምክሮች እንዲህ የሚል ይገኝበታል፦
❝...በመካከላችሁ (እናንተ ሰለፊዮች ሆይ!) አንድነትን በሁሉም ጉዳዮች ላይ ልታጠናክሩ ይገባል። እጅለእጅ ነው መጓዝ ያለባችሁ!፤በመልካምና በበጎ ተግባራት እንዲሁም አላህን በመፍራት ላይ ተጋገዙ። ከልዩነት፣ ከመከፋፈል... እንዲሁም ሰለፊዮችን ሊከፋፍል ከሚችሉ መንስኤዎችና አመክንዮዎች ራቁ፣ተጠንቀቁ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰለፊዮች ውስጥ የፊትና ማዕበል የሚፈጥሩ፤ይህ ደግሞ የሰለፎች ሚንሃጅ አይደለም። የሶሃቦችም፣ የታቢዒዮችም... ሚንሃጅ አይደለም። ሆን ብለው የሰለፊዮችን መበጣጠስና መከፋፈል የሚፈልጉ፤እንደነኝህ አይነት ሰዎች በእስልምና ውስጥ ክብር የላቸውም፤እንዲሁም በአላህ ዲን ላይ እምነት አይጣልባቸውም። ሰለፊይ ነን ብሎም ቢሞግቱም እነሱ ትክክለኛ "ሰለፍይ" አይደሉም። እንደነኝህ አይነት ሰዎች ትኩረት ተደርጎባቸው "ሰለፊዮችን ለምን ትከፋፍላለህ?" ተበለው ሊጠየቁ ይገባል። እንዲሁም ሰለፊዮችን ለመከፋፈል እነኝህን (ይዟቸው የመጣው የፊትና ወይም እዚህ ግባ የማይባሉ የልዩነት ምክንያቶች) ለምን አላማ ነው ይዘኸቸው የመኸው?! ተብሎ ሊጠየቅ ይገባል...❞ በሚል ድንቅ ምክር ቋጭተን ነበር። የሸይኹ ምክር አላበቃም እንዲህም በማለት ይቀጥላሉ፦
❝...ጥፋት ያጠፋ የሆነ አካል በጥበብ፣በትህትና፣ ለስለስ ባለ ሁኔታዎች ይመከራል። ሪፍቅ ነገራቶችን ያስውባል (ያሳምራል) ሪፍቅ ከሌለ ግን ነገራቶችን ያጎድፋል፤እንዲሁም ሀያእ (ዓይናፋርነትም) ነገራቶችን ያሳምራል።እራሳችሁን በጥበብ፣በሪፍቅ፣በትዕግሥት፣በይቅርታ (አይቶ እንዳላየ)፣...ልታስውቡ (ልታሳምሩ) ይገባል። ይህ በንዲህ እንዳለ፣በሀቅ ላይ ፅናትም ሊኖራችሁ ይገባል። ከፍ ያለው ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡ «ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡» (አሕዛብ:21) እንዲሁም አላህ መልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት አወድሷቸዋል፡ «አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡» (አል-ቀለም:4) የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እጅግ በጣም ባማረና በተሟላ (Perfect) በሆነ የስነምግባር ቁንጮ ላይ ነበሩ። ስነምግባራችሁን እንድታሳምሩ እመክራችኋለሁ።
እነኝህን (ከላይ የተጠቀሱትን) ከአይናችሁ ፊትለፊት አድርጓቸው (ተግብሯቸው) የአላህን ፍራቻ ተላበሱ፣ኢኽላስ ይኑራችሁ፣ ለአላህ ባሪያዎች መልካምን ዋሉ፣ቅን ሁኑላቸው፣እርስበርሳችሁ ወንድማማቾች ሁኑ፣ አንድነታችሁን ጠብቁ፣ ለልዩነት መንስኤ ከሆኑ ነገራቶች ሁሉ ራቁ፣ ትዕግሥትን አሳዩ፣ እርስበርስ በጥበብ፣ በሪፍቅ...ተመካከሩ ከፍ ያለው ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፦
«ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡» (ነሕል:125)
በጠላትነት፣በሀይለ-ቃል፣በስድብ...አትመካሩ። ምክንያቱም ይህ የሰለፎች መንገድ (ሚንሃጅ) አይደለምና። ለአላህ ብላችሁ አርበርስ ተፈቃቀሩ፣እርስበርስ ተዘያየሩ፣ ተጠያየቁ... ባረከላሁ ፊኩም!...እነኝህ ወሳኝና አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው፤በሰለፊዮች መካከል ሊተገበሩ፣ሊፈፀሙ የሚገገቡ ናቸው። አብዛኛው ሰው እነኝህን አስፈላጊና አንገብጋቢ ነጥቦች አሳሳቢ ሆነው ሳሉ ችላ በማለት ትቷቸዋል። እየተፈፀሙ አይደለም፣ እየተተገበሩም አይደለም። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
«ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ!፤ ጀነትን አትገቡም እስክታምኑ ድረስ፣ አታምኑም እርስበርስ እስክትዋደዱ ድረሥ...አልጦቅማችሁንምን እርስበርስ ምትዋደዱበትን?! በመካከላችሁ (እርስበርሳችሁ) ሰላምታን አሰራጩ።»
(ሙስሊም:54)
የሸይኹ ምክር እንደቀጠለ ነው...አላህ ፍፃሜያቸውን ያማረ ያድርገውና ከላይ የተጠቀሰውን የመልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐዲስ እንዲህ በማለት ያብራሩታል፦
«ኒያችሁን (Intention) በማስተካከል፣ ጀነተን ፍለጋ፣ ለአላህ ብላችሁ በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ። እንደ ለምድ አድርጋችሁ ሳይሆን ኒያችሁን በማስተካከል ነው መባል ያለበት፤ወደ አላህ እቃረበላሁ፣ ለጀነት ምክንያት ይሆነኛል ብሎ በማሰብ፣ የእንድነትን ዐሻራ (በሰለፊዮች መካከል) ታስቦ ነው ሰላምታው መሰራጨት ያለበት... በጌታዬ ይሁንብኝ! ትክክለኛ "ሰለፍይ" የሆነ ሰው ለሌላኛው የሰለፊዩ ጉዳይ: ያመዋል፣ ይሰማዋል፣ ያሳስቧል... ከአጠቡ የራቀ ቢሆን እንኳ!። እርቆ ያለው ሰለፍይ በሀገረ ጃፓን፣አሜሪካ...የሆነ ቢሆን እንኳ...»
እኛ ኢትዮጵያዊ የሆን ሰለፊዮች ሆይ! ከዚህ ስመጥር ከሆኑት ከሸይኽ፣ዶኮተር፣ ፕሮፌሰር፣አል-ዐላመህ፣ አል-ዋሊድ ረቢዕ ብን ሃዲ አል-መድኸሊይ አላህ ፍፃሜያቸውን ያሳምርላቸውና...ከዚህ ምክራቸው አንፃር የት ነው ያለነው?! እውን እርስበርስ እንዋደደላን? ወይስ....? መልሱን ከራሴ ጀምሮ ሁሉም ሕሊናውን ይጠይቅ! በነገራችን ላይ ባለፉት ጥቂት ጊዚያት ውስጥ ለሰለፊዮች ጉርጓድን ሲቆፍሩ የነበሩ ግለሰቦች አላህ መንጥሮ አውጥቷቸዋል። ይህም ሀገር ያወቀው፣ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ሀቅ ነው። ምን የህል የሞራል ውድቀት እንደደረሰባቸው እራሳቸው ያውቃሉ። ምክንያቱም ከመስመር ውጭ ስለ ተጓዙ። ከነሱ ትምህርት ልንወስድ ይገባል። ዛሬ ደግሞ አንተ ተሰማኒት አለኝ ብለህ፣የፈለከውን ያለማስራጃ ከፍ-ዝቅ የምታደርግ ከሆነ ሁሉም በቁጥጥሬ ውስጥ ነው ብለህ ሴራ፣ ተንኮል፣ እብሪት፣ማን አለብኝነት፣ እንዲሁም ለሰለፊዮች መከፋፈል መንስኤ ምትሆን ከሆነ...እወቅ! የትም አትደርስም። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ። የጥበበኛውና የአሸናፊው የጌታችንን እንዲህ የሚለው ቃል አበከረህ አስተንትን፦
«በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ (ተንኮል) መዶለትንም (እንጂ አልጨመረላቸውም፡፡ ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም፡፡ የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠባበቃሉን? ለአላህ ደንብም መልለወጥን አታገኝም፡፡ ለአላህ ደንብም መዛወርን አታገኝም፡፡» (ፋጢር:43)
@semirEnglish
https://t.me/semirEnglish