‹‹በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?›› 1ኛ ሳሙ 15፡32።
(ከዐቢይ ጾሙ ጋር በተገናኘ በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሠረት በድጋሚ የቀረበ)
ይኽ ጽሑፍ ነፍስ ከሥጋ ስትለይ በፍጹም ደስታ አሊያም በእንዴት ያለ አስጨናቂ መከራ ውስጥ እንደምትገኝ የሚያስረዳ ግሩም ምሥጢርን የተመላ ነውና በጥሞና አንብበነው ለነፍሳችን የሚሆን ስንቅ እንሰንቅ ዘንድ ለኹላችን ተዘጋጀልን! (የጽሑፉ ምንጭ ደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳም ‹‹ሕማማተ መስቀል›› በሚል ርዕስ ካሳተመው ድርሳን ላይ ‹‹ሕይወተ ምእመናን›› የሚለው ንዑስ ርዕስ ነው፡፡)
በርዕሱ ላይ ያለውን ኃይለ ቃል ‹‹በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?›› (1ኛ ሳሙ 15፡32) ሲል የተናገረው በሞት ጣዕር ላይ የነበረው የአማሌቃውያን ንጉሥ አጋግ ነው፡፡ ንጉሥ አጋግ ሃይማኖት የሌለው፣ የብዙ ንጹሐንን ደም በግፍ ሲያፈስ የኖረ ኃጥእ ሰው ነበር፡፡ እርሱም በተራው በሞት አፋፍ ላይ ሳለ ፈራ፣ ተንቀጠቀጠ፡፡ ከጭንቀት ብዛት ጅማቶቹ እርስ በርሳቸው ተለያዩ፤ አጥንቶች ተላቀቁ፡፡
በዓለም ላይ ያለ ማንም ኃጥእ ሰው ንጉሥ ይሁን ሎሌ፣ የተማረ ምሑር ይሁን ያልተማረ ጨዋ፣ ሀብታም ይሁን ድሀ ማንኛውም ሰው በእውነተኛዋ ሃይማኖት ያላመነ ምግባር የሌለው ከሆነ በስተመጨረሻ በሞት አፋፍ ላይ ሳለ እጅግ እፈሪውን መልአከ ሞትን በገሃድ በተመለከተ ጊዜ እንደንጉሥ አጋግ ‹‹ከመዝኑ ሞት መሪር-በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?›› ማለቱ አይቀርም፡፡ ስለዚህ በአጭሩ ምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው ጠንቅቀው ሊያውቁ፣ ምግባር፣ ትሩፋት ሊሠሩ ይገባቸዋል፡፡ ይህስ ስለምንድን ነው? ቢሉ ኋላ በዕለተ ሞት በጌታ ቃል መጠየቅ አይቀርምና ነው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በዚህች ምድር ሳላችሁ ሃይማኖት ተማሩ፣ ምግባር ሥሩ›› ብሎ አዟልና ነው፡፡
ኋላ በዕለተ ሞት ጊዜ በጌታ ቃል ምን ተብሎ ይጠየቃል? ቢሉ የመልካም ሰው ነፍስ እንደሆነች ከሥጋዋ ሳትለይ ገና በፃዕረ ሞቷ ሳለች መላእክተ ብርሃን በቀኝ፣ መላእከተ ጽልመት በግራ ሆነው ይመጡባታል፡፡ መጥተውም ባዩዋት ጊዜ የብርሃን ቀሚስ ለብሳ፣ የብርሃን መጐናጸፊያ ተጐናጽፋ፣ የብርሃን አክሊል ደፍታ፣ የብርሃን ዝውድ ተቀዳጅታ፣ የብርሃን ዝናር ታጥቃ፣ የብርሃን ጫማ ተጫምታ፣ የመስቀል ምልክት ያለበት የብርሃን ዘንግ ይዛ፣ ከፀሐይ 7 እጅ አብርታ፣ ከመብረቅ 7 እጅ አስፈርታ፣ አምራና ሠምራ ጌታዋን ክርስቶስን መስላ ትቆያቸዋለች፡፡
ከዚህም በኋላ መላእክተ ጽልመትን እንደ እሳት ትፈጃቸዋለች፤ እንደ ፀሐይ ታንፀባርቅባቸዋለች፤ እነርሱም ይፈሯታል፡፡ ከፊቷ ርቀው ፈቀቅ ብለው ይቆማሉ፡፡ በዚያው ርቀው በቆሙበት ሆነው ጠርተው ይጠይቋታል፡፡ ምን ብለው ይጠይቋታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በማን ታመልኪያለሽ? የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን ታምኛለሽን? የእግዚአብሔርን እንግዳ ተቀብለሻል? ሰንበትን አክብረሻልን?›› ብለው ይጠይቋታል፡፡ እርሷም እውነተኛ የተማረች ሃይማኖተኛ ናትና ‹‹አዎን የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን አምናለሁ…ነገር ግን እንደ እናንተ ያለ የከፋ የከረፋ አይቼም ሰምቼም አላውቅም›› ብላ ትመልስላቸዋለች፡፡
መላእክተ ጽልመትም መርምረው የእርነሱ ድርሻ አለመሆኗን ካረጋገጡ በኋላ አፍረው ተዋርደው ‹‹አንቺ ነፍስ እኛ ያጣናትን መንግሥተ ሰማያት አንቺ አገኘሻት!...›› እያሉ እያዘኑ እየተከዙ ትተዋት ይሔዳሉ፡፡
ከዚህም በኋላ መላእክተ ብርሃን ከገነት መልካም መዓዛ ያለው የሽቱ አበባ ቆርጠው ይዘው መጥተው ካጠገቧ ከበዋት ይቆማሉ፡፡ ቆመውም ይጠይቋታል፡፡ ምን ብለው ይጠይቋታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በማን ታመልኪያለሽ? የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን ታምኛለሽን? የእግዚአብሔርን እንግዳ ተቀብለሻል? ሰንበትን አክብረሻልን?›› ብለው ይጠይቋታል፡፡ እርሷም ቃሏ እውነት ነውና ‹‹አዎን የሥላሴን አንድነት ሦስትነት፣ ምልዐት፣ ስፋት፣ ርቀት፣ የጌታን ከሰማይ መውረዱን፣ መወለዱን፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም መሆኑን፣ መገፈፍ፣ መገረፉን፣ መሰቀል፣ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ መነሣቱን ማረጉን፣ ዳግም ለፍርድ መምጣቱን አምናለሁ›› ብላ ትመልስላቸዋለች፡፡ ዳግመኛም ‹‹5ቱን አዕማደ ምሥጢር 13ቱን ሕማማተ መስቀል ተምረሻል? ሰንበትን አክብረሻል? የእግዚአብሔር እንግዳ ተቀብለሻልን?›› ብለው ይጠይቋታል፡፡ እርሷም ‹‹አዎን አውቃለሁ እናንተማ ወዳጆቼ ዘመዶቼ አይደላችሁምን? የመከራችሁንኝ ሰምቼ፣ ያዘዛችሁኝን ሠርቼ እኖር የለምን? ብላ ትመልስላቸዋለች፡፡ የጻድቅ ነፍስ መላእክተ የት ታውቃቸዋለችና ነው? ቢሉ የመልካም ሰው ነፍስ የሆነች እንደሆነ ገና በቁመናዋ በዓለመ ሥጋ ሳለች በአካለ ነፍስ ከመላእክተ ብርሃን ጋራ ከሰማየ ሰማያት የእወጣች እየወረደች ጌታዋን ፈጣሪዋን ስታመሰግን ትኖር ነበርና ስለዚህ ‹‹አውቃችኋለሁ›› ትላቸዋለች፡፡ መላእክተ ብርሃንም ያችን ነፍስ መርምረው የእነሱ ወገን መሆኗን ካረጋገጡ በኋላ ‹‹ከቃልሽ እናግኘው ብለን ነው እንጂ አዎን እኛማ እናውቅሻለን›› ብለው ይመሰክሩላታል፡፡
ከዚኽም በኋላ ነቢዩ ዳዊት በገናውን፣ ዕዝራ መሰንቆውን ይዘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አዕላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታትን፣ ደናግል መነኰሳትን አስከትሎ ወርዶ በቁመናዋ የሠራችውን የምግባሯን ዋጋ ቃልኪዳን ሰጥቷት ተመልሶ ያርጋል፡፡ መውጣት መውረዱ ለእኛ ክብር ሲል በለበሰው ሥጋ ነው እንጂ በመለሎትነቱስ በሁሉ የመላ ስለሆነ መውጣት መውረድ የለበትም፡፡
ከዚኽም በኋላ መልአከ ሞት አምሮ ሠምሮ መልአከ ብርሃን መስሎ ይታያታል፡፡ ስለምን መልአከ ሞት መልአከ ሣህል መልአከ ብርሃን መስሎ ይታያታል ቢሉ? እንዳትባባ እንዳትፈራ ነው፡፡ ከዚኽም በኋላ መላእክተ ብርሃን ያንን ከገነት ቆርጠው ያመጡትን የሽቱ አበባ ከአፍንጫዋ ላይ ጣል አድርገው ሲያነሡት በመልካሙ የሽታ መዓዛ ተመስጣ ነፍስ ከሥጋዋ ትለያለች፡፡
ከዚኽም በኋላ መላእክተ ብርሃን በፊት በኋላ፣ በቀኝ በግራ ሆነው ዕዝራ መሰንቆውን፣ ዳዊት መገናውን እየደረደሩ እያመሰገኑ ዳዊት ‹‹የጻድቅ ሰው ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ ክቡር ነው›› (መዝ 115፡6) እያለ፣ ዕዝራም ‹‹የጻድቃን ሞታቸው ሕይወታቸው ነው…›› እያሉ በዝማሬ በይባቤ ይዘዋት ይሔዳሉ፡፡
ከዚኽም በኋላ መላእክተ ጽልመት ከጌታ ቃል ሳይሰሙ ትእዛዝ ሳይቀበሉ አይመለሱምና ራስ ራሷን እየተመለከቱ ሲከታተሏት ከባሕረ እሳት ይደርሳሉ፡፡ የባሕረ እሳት ቦታዋ ስፍራዋ ወዴት ነው? መጠኗስ ምን ያህል ነው? ቢሉ ቦታዋ ከጠፈር በላይ ከሐኖስ በታች ከመካከል በምጽንዓተ ሰማይ ነው፡፡ ልኳም ይህችን ሰው የሠፈረባት ዓለም ታህላለች፤ ቀኝዋ እሳት ግራዋ ባሕር ነው፣ ውስጧ ገደል መንገዷም ከጭራ የቀጠነ ጠባብ ነው፡፡ ዕዝ 5፡8፡፡