ስግር፣ ስበላ፣ ስጠጣ፣ ስቀማ፣ ስሰርቅ ነበርሁ እንጂ፣ ሃይማኖት አልተማርሁ፣ ምግባር አልሠራሁ፣ ሰንበትን አላከበርሁ›› ብላ ትመልስለታለች፡፡ ከዚህም በኋላ መላእክተ ብርሃንን ጠርቶ ‹‹ይህቺ ነፍስ አሕዛብ (ያላመነች ያልተጠመቀች) ናትና ኩነኔ እንጂ መንግሥተ ሰማያት አይገባትም፤ ከሥጋዋ ጋር አዋሕጄ ፍጹም ገሃነመ እሳት እስካገባት ድረስ 4 ቀን መንግሥተ ሰማያትን፣ 3 ቀን ገሃነመ እሳትን አዙራችሁ አሳይታችሁ ከኃጥአን ጋራ በሲኦል በርባሮስ አኑሯት›› ይላቸዋል፡፡ መላእክተ ብርሃንም ይዘዋት ወጥተው 4 ቀን መንግሥተ ሰማያትን የባለ ሕጎችን፣ የደናግሎችን ሀገር፣ የመነኮሳቱን ሀገር፣ ማርና ወተት የምታፈስ የተባለችውን አዙረው አሳይው ሽታዋን ጣዕሟን በልቧ አስርፀው፣ አቅምሰው ‹‹አንቺ ነፍስ ሃይማኖት ብትማሪ፣ ምግባር ብትሠሪ ቦታሽ ይህ ነበር…›› ብለው ይዘዋት ወርደው ገሃነመ እሳትን 3 ቀን የእሳቱን ሰንሰለት፣ የእሳቱን አክሊል፣ የእሳቱን ጨለማ፣ የእሳቱን ቁርበት፣ የእሳቱን ዘንዶ፣ የእሳቱን ዝናር፣ የእሳቱን ጫማ፣ ክርፋቱን ግማቱን፣ አዙረው አሳይተው ‹‹አንቺ ነፍስ በእንዲህ ያለ ቦታ ትሉ ከማያንቀላፋ፣ እሳቱ ከማይጠፋ ለዘላለም በዚህ ያኖርሻል›› ብለው ወደ በርባሮስ ይዘዋት ይሔዳሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰኦል ደጅ አድርሰው ለአጋንንት ያስረክቧታል፡፡ አጋንንትም ከጨለማው አግብተው በእሳት ጦር እየወጉ፣ በእሳት አለንጋ እየገረፉ፣ በእሳት መንዶ እየቀጠቀጡ ይወስዷታል፡፡ እርሷም መከራው ሲጸናባት ‹‹ወየው! ወየው!…የእግዝእትነ ማርያም ያለህ!›› ትላለች፡፡ ትማፀናለች፡፡ እመቤታችንም ለሁሉ አማላጅ ናትና መጥታ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ! ማርልኝ›› ትለዋለች፡፡ ጌታም ‹‹ይህች ነፍስ እኔንም አንቺንም የበደለች ከሃዲ ናትና አልራራላትም›› ይላታል፡፡ እመቤታችንም ‹‹ምሕረት ልማድህ ነውና ማርልኝ›› ብላ ትሰግዳለች፡፡ ጌታም ‹‹ስለ እናቴ ጥቂት አሳርፏት›› ይላቸዋል፡፡
ዛሬ በዚህ ዓለም አንድ ሰው በቆላ ሲሔድ ከላይ ፀሐዩ፣ ከታች ረመጫቱ (የመሬቱ ግለት) ሲፈጀው ላብ ላብ ሲለው ጥቂት ጥላ ያገኘ እንደሆነ እርፍ ብሎ እንደሚነሣ ሁሉ አጋንንትም ያችን ነፍስ ጥቂት አሳርፈው እንደገና መከራዋን ሲያሳዩአት ይኖራሉ፡፡ እርሷም ከመንግሥተ ሰማያት መውጧን ገሃነመ እሳት መውረዷን እያሰበች ፀፀት እንደ እሳት ሲፈጃት ሲያቃጥላት እስከ ዕለተ ምጽዓት ድረስ በሲኦል ትቀመጣለች፡፡ የኃጥእ ሰው ነፍስ ሥቃይዋ ይህን የመሰለ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከዚህ መከራ ሁላችንንም ያድነን! አሜን!!!
ማጠቃለያ፡- በዓለም ላይ ያለ ማንም ኃጥእ ሰው ንጉሥ ይሁን ሎሌ፣ የተማረ ምሑር ይሁን ያልተማረ ጨዋ፣ ሀብታም ይሁን ድሀ ማንኛውም ሰው በእውነተኛዋ ሃይማኖት ያላመነ ምግባር የሌለው ከሆነ በስተመጨረሻ በሞት አፋፍ ላይ ሳለ እጅግ እፈሪውን መልአከ ሞትን በገሃድ በተመለከተ ጊዜ እንደንጉሥ አጋግ ‹‹ከመዝኑ ሞት መሪር-በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?›› ማለቱ አይቀርም፡፡ ሃይማኖት ላልተማሩ ምግባር ላልሠሩ ለኃጥአንና ለክፉዎች ሞት እጅጉን መራራ ነው፡፡ ይልቁንም ሁለተኛው ሞት በገሃነም ያለው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዳኝነት ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ፣ ሥቃያቸውም አያልቅም፡፡ ራእ 14፡11፣ 20፡13፡፡ ጌታችንም በቅዱስ ቃሉ ‹‹ትሉ ወደማያንቀላፋበት እሳቱ ወደማይጠፋበት›› የሚገቡ እንዳሉ አስተምሯል፡፡ ማር 9፡44-48፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹እግዚአብሔርን የማያውቁትን፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስንም ወንጌል የማይሰሙትን ይበቀላቸዋል፤ ከጌታችን ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘለዓለም ጥፋት ፍዳቸውን ያገኛሉ›› ብሏል፡፡ 1ኛ ተሰ 1፡9፡፡ ከነቢያትም ነቢዩ ኤርምያስ ‹‹እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፣ ስለዚህ አሳዶቼ ይሰናከላሉ፣ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጉስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ›› በማለት ተናግሯል፡፡ ኤር 20፡11፡፡ ነቢዩ ዳንኤልም ‹‹በምድርም ትቢያ ውስጥ ከአንቀላፉት ብዙዎች እኵሌቶቹ ለዘለዓለም ሕይወት፣ እኵሌቶቹም ለእፍረትና ለዘለዓለም ጉስቍልና ይነሣሉ›› ብሏል፡፡ ዳን 12፡2፡፡
እንግዲህ የነፍስና የሥጋ መለያየት እንደ አጋግ የመረረን ወይም የሚመርረን ሰዎች ሁለተኛው ሞት ሲመጣ ‹‹እንዴት ልንሆን ነው?›› ማለት ይገባል፡፡ ከዚህም ተነሥተን የመጀመሪያውንም የሁለተኛውንም ሞት መራራ የሚያደርገው ሃይማኖትን ከምግባር አስተባብረን አለመያዛችንና ክፋታችን መሆኑን አውቀን ሃይማኖት ተምረን ምግባር ሠርተን ከክፋት ወደ በጎነት መመለስ ይኖርብናል፡፡ ያን ጊዜ ሞታችን እንቅልፍ ወይም እረፍት ይሆንልናል፡፡ 1ኛ ነገ 2፡10፣ ሐዋ 7፡60፣ ራእ 14፡13፡፡
በክርስቶስ ሞት የተሻረ ሞት በእኛ በእውነተኞቹ በክርስቶስ ተከታዮቹ ላይ ሥልጣን አይኖረውም፡፡ 1ኛ ቆሮ 15፡53-57፣ 2ኛጢሞ 1፡10፣ ዕብ 2፡9፣ 14፡15፣ ራእ 18፡፡ ሞት ከክርስቶስ ጋር ለዘለዓለም የሚያኖረን መንገድ ይሆንልናል፡፡ ኢሳ 35፡10፣ 45፡17፣ ዳን 7፡14፣ 12፡2፣ ሉቃ 23፡43፣ ዮሐ 5፡24፣ 1ኛ ተሰ 4፡13፡፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ በክርስቶስም ዘንድ ልኖር እወዳለሁ፤ ይልቁንም ለእኔ ይህ ይሻለኛል፣ ይበልጥብኛልም›› እንላለን፡፡ ፊል 1፡23፡፡ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹እግዚአብሔር የሚመጣበትን፣ ሰማያትም ቀልጠው የሚጠፉበትን፣ ፍጥረትም ሁሉ ተቃጥሎ የሚጠፋባትን ዕለት በተስፋ እየጠበቃችሁ ፍጠኑ፤ እኛ ግን ጽድቅ የሚኖርባቸውን አዲሶቹን ሰማያትና አዲሲቱን ምድር ተስፋ እናደርጋለን›› እያልን በተስፋ መንግሥተ ሰማያት እንኖራለን፡፡ 2ኛ ጴጥ 3፡12፡፡ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ዓለሙንና በዓለም ያለውን አትውደዱ፤ ዓለሙን የሚወድ ግን የአብ ፍቅር በእርሱ የለም፡፡ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት፣ ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም እንጂ ከአብ አይደለም፡፡ ዓለሙ ያልፋል፣ ምኞቱም ያልፈል፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሰው ግን ለዘለዓለም ይኖራል›› በማለት በሕይወት እንተረጉመዋለን፡፡ 1ኛ ዮሐ 2፡15-17፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን! አሜን!!!